Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ ! በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሠላም ቅድመ አንደኛና | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ !

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሠላም ቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2015 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ ዕቃዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ሕጋዊ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድረን በቴክኒክና በዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ከሆኑ ድርጅቶች ለመግዛት የምንፈልግ መሆኑን እናሳውቃለን።

1 አላቂ የጽህፈትና የቢሮ መሣሪያዎች፣
02. የጽዳት ዕቃዎች፣
3. የመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
4. የሕትመት ሥራዎች፣
5. ቋሚ ዕቃዎች፣
6 የጥገና ሥራ ዕቃዎች፣
7 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣
8. አላቂ የህክምና ዕቃዎች

ተጫራቾች

የ2014 ዓ.ም ግብር የከፈሉና ለ2014 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ መሆኑን የሚገልጽ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

1.ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም ማለትም ሠላም በር ቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በሚል አጽፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡ 30-6፡30 ከሰዓት 7፡30-11፡30 ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በሰላም በር ቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ክፍያና ሂሳብ አስደጋፊ የሥራ ሂደት በመቅረብ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይኖርባቸዋል። እስከ 10 ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ዝርዝር ዋጋ እና አይነት በመግለጽ በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ በግዢ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ፖስታው ካልታሸገ አይከፈትም ወይም ለውድድር አይቀርብም።

3.የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11 ኛው ቀን 4፡oo ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4:30 ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።

4.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት፣ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመበት የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ሕጋዊ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።

5.ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚያቀርቡት ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ፣ የፕሪንተር እና የኮፒ ቀለሞች ኦሪጅናል /ትክክለኛነት, የማረጋገጫ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም በተወዳደሩት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚ አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውል መሠረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው።

7.አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተዋዋለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።

8.ት/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ከመረጠ በኋላ በሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስክ 20% የመቀነስ ወይም የመጨር መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁን ሲሞላ 15% ቫትን በማካተት ይሆናል። 15% ቫትን ያላካተተ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም።

አድራሻ፡-በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሉካንዳ ታክሲ ማዞሪያ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም በሚወስደው አስፋልት በስተቀኝ በኩል ሰዋሰው ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/630cdc794e36341cd4307a2c?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።