Get Mystery Box with random crypto!

የኮንስትራክሽን ጨረታ! ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከዚህ በታች የተዘ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

የኮንስትራክሽን ጨረታ!

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ግብዓት በግልጽ ጨረታአወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ብቁእና ዝርዝር መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግብዓቶች ለማቅረብ መወዳደር ይችላሉ።

1.ሬንጅ (Bitumen) 60/70 እና 8o/1oo
2.ጥራቱን የጠበቀ የወንዝ አሸዋ በሜትር ኩብ
3.ገረጋንቲ ማቴሪያል (Selected material) በሜትር ኩብ
4.ትራይካቲክ ድንጋይ (Trachytic stone) ድንጋይ በሜትር ኩብ
5.የመስተሻታ ድንጋይ (Basaltic stone) ድንጋይ በሜትር ኩብ
6.ጠጠር ከ0 እስከ 5 ሚሊ ሜትር በሜትር ኩብ
7.ጠጠር ከ5 እስከ 10 ሚሊ ሜትር በሜትር ኩብ
8.ጠጠር ከ10 እስከ 20 ሚሊ ሜትር በሚትር ኩብ
9.ጠጠር ከ20 እስከ 30 ሚሊ ሜትር በሚትር ኩብ
10.የተፈጨ ቤዝ ኮርስ ጠጠር (Base course) በሜትር ኩብ
11.የተፈጨ ሰብ ቤዝ ኮርስ (Sub base course) በሜትር ከብ
12.ቀይ አፈር በሜትር ኩብ
13.አጠና እንጨት ባለ 6 ዲያሜትር በቁጥር
14.አጠና እንጨት ባለ 8 ዲያሜትር በቁጥር
15.አጠና እንጨት ባለ ıo ዲያሜትር በቁጥር
16.አጠና እንጨት ባለ 12 ዲያሜትር በቁጥር

ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ግብዓት በጥራትና በሚገባ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች የሚያቀርቡበትን ዋጋ የትራንስፖርትና ተያያዥ ወጪዎች ጨምሮ ከላይ በተዘረዘረው መለኪያ ዋጋ በመሙላት በግልጽ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በነዚህ የሥራ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስባት ይችላሉ። በ15ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ 4፡30 በድርጅቱ ቅጥር መቻሬ ሜዳ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሱት ግብዓት አቅርቦት በከፊል ወይም በሁሉም መጫረት ይችላሉ። የተጠቀሱት ግብዓት የሚቀርቡበት ቦታ ቃሊቲ ከሸገር ዳቦ ጐን በሚገኘው ዋናው መጋዘን እና ድርጅቱ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚሠራቸው ፕሮጀክቶች ይሆናል።

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ከሚድሮh ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር ግዥና ሎጂስቲክስ ቢሮ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

በተጨማሪም አቅራቢዎች ማያያዝ ያለባቸው ዶክመንቶች
1.የታደሰ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የንግድ ፍቃድ
2.የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ኮፒ
3.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው ሰርተፊኬት
4.የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ካለ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል
አድራሻ፡
መቻሬ ሜዳ በሚገኘው የሚድሮh ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር ቢሮ ቁጥር 202 ፕሮኪዩርመንትና ሎጂስቲhስ ዳይሬከቶሬት

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/630c7b754e36341cd43079a1?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።