Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ እና የሚያበረታታ ጨረታ! በቂርቆስ ክ/ከ/አስተዳደር ፐብሊከ ሰ/ሀ/ል | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ እና የሚያበረታታ ጨረታ!

በቂርቆስ ክ/ከ/አስተዳደር ፐብሊከ ሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል።

ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ

1 የቢሮ አላቂ መገልገያ ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 5,000
2 የተለያዩ የህንፃ መገጣጠሚያ ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 5,000
3 ኅትመት አገልግሎት ሲፒኦ ብር 4,000
4 ጫኝና አውራጅ አገልግሎት ሲፒኦ ጥቃቅን
5 የፅዳት ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 9,000
6 የጭነት መኪና አገልግሎት ሲፒኦ ብር 5,000
7 የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶች ሲፒኦ ብር 10,000
8 የመድረክ ማስዋብና ቅስቀሳ አገልግሎት ሲፒኦ ብር 4,000
9 ድንኳን ወንበርና ጠረጴዛ ኪራይ አገልግሎት ሲፒኦ ብር 3,000
10 ቋሚ ዕቃዎች እና የባህል አልባሳት ሲፒኦ ብር 15,000

በመሆኑም ተጫራቾች:

1.የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN No/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡

2.የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴhኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴኒካል ሰነድ ኮፒ፣ 1 ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሻል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባን የተረጋገጠ ለብቻ በታሸı ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡

3.በጨረታው ላይ ጥቃቅን አነስተኛ ይበረታታሉ ሆኖም ግን የጨረታ ሰነዱን በነፃ ማግኘት የሚችሉት ካቋቋማቸው አካል ተገቢውን እና የተሟላ ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ነው::

4.ወቅታዊ የሆነ የመልካም ሥራ አፈጻጸም የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፡፡

5.የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 6 ፎቅ የፐብሊ ሰ/ሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 15 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ሰነዱን ሙግዛት ይችላሉ፡፡

6..ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር ለ10 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚከፈተው ደግሞ 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡

7.አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት ::

አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊትለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አስ/ አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ስል 0115-58-28-71

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/63088e5ddcdb02191617e750?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።