Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2015 ዓ.ም. ለት/ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2015 ዓ.ም. ለት/ቤቱ የሚከተሉትን እቃዎች በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

•አላቂ የትምህርት ዕቃ
•አላቂ የቢሮ ዕቃ
•ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
•የደንብ ልብስ እስከነማሰፊያው
•የፅዳት ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመወዳደር የሚችሉት፡_
•በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
•የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
•በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
•ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ
•ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 3000 (ሦስት ሺህ) እና ለሎት 2 ብር 2000 (ሁለት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
•ለአነስተኛና ጥቃቅን መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት በሚፈቀድላቸው ዘርፍ ብቻ እንድትሳተፉ ያበረታታል።
•አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርበታል።
•ጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
•ማንኛውም ተጫራች የመሸጫ ዋጋውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያዩ በሰም በታሸı ኢንቨሎፕ አዘጋጅቶ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 10 በግንባር በመኘት ማስገባት ይኖርበታል።

•ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

•አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ውስጥ ድረስ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርበታል።

•አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ወደ ሰባተኛ በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ላይ ይገኛል።
ስልክ 011 277 5609/10/011 868 5356

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/6309d3ab0c0f047716a75773?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች አጠቃላይ በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።