Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ጽህፈ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ጽህፈት ቤት ስር ላሉት ጽህፈት ቤቶች በ2015ዓ.ም. በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን።

•የደንብ ልብስ
•የጽህፈት መሳሪያ
•የህትመት ስራ
•የጽዳት እቃዎች
•ትራንስፖርት
•ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
•ጭነት
•ቋሚ እቃዎች
•መስተንግዶ--

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ፡-
1.በጨረታው ለመወዳር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2.ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በየሎቱ ሲፒኦ በማሰራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት 2ኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4.ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.የጨረታ ሳጥኑ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ሰአት ታሽጎ በነጋታው ጠዋት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡oo ሰአት ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት 2ኛ ፎቅ ይከፈታል። የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/6308889cdcdb02191617e742?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።