Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2015 በጀት አመት የተለያዩ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2015 በጀት አመት የተለያዩ አይነት ፈርኒቸሮች መግዛት ይፈልጋል።

•በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት
•የተፈረመ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል መግቢያ ቅፅ
•የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሠርተፍኬት
•የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት
•በ2014/15 የታደሰ የንግድ ፍቃድ
•የአገር ውስጥ ገቢ የታክስ ክሊራንስ ይሆናል።

1 ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡

2 አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለክፍያ በነጻ ይሰጣቸዋል።

3 የጨረታው ሰነድ የሚላከው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር (ዋናው መ/ቤት) ፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 6166 አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ ወይም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር (ዋናው መ/ቤት) ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል።

4 ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) አያይዘው ያቀርባሉ።

5. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም እና የጨረታው አይነት ተጠቅሶ የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም። በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቁጥር 7 «ሐ» በተጠቀሰው አድራሻ ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. 8:10 ሰዓት ይከፈታል።

6. ሀ/ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ (ዋናው መ/ቤት) ቁጥር 9
ለ/ ጨረታው የሚቀርብበት አድራሻ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 9
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 6
7. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሠረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ +251-11 155 3400
ፖስታ ሣጥን ቁጥር 6166 አዲስ አበባ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/63035a9edcdb02191617e531?lang=am ይመልከቱ።
ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።
ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።