Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ201 | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2014 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የተማሪዎች ሻይ ቤት ለውጭ ድርጅቶች አወዳድሮ outsource ለማድረግ ይፈልጋል።

ማንኛውም - ተጫራች
(ሀ) የታደሰ የንግድ ፈቃድ
(ለ) የግብር ከፋይ የምስክርነት ወረቀት
(ሐ) የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት
(መ) የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክርነት ወረቀት
(ሠ) ወቅታዊ የሆነ የታክስ ክሊራንስ
(ረ) ላለማጭበርበር ቃል የሚገባበት ቅጽ ፈርሞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

2. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ከፍያ ዋስትና ምትክ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል።

3. የጨረታው ሰነድ የሚላከው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል።

4. የጨረታ ሠነዱን በተመለከተ
ሀ/ ሰነዶቹ የሚወስዱት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ግዥ hፍል ቢሮ ቁጥር 001
ለ/ ጨረታው የሚገባው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚhስ ኮሌጅ ዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 001
ሐ/ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በግዥ hፍል ይሆናል።

5. ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/63035abcdcdb02191617e532?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://%E1%89%A02merkato.com) (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።