Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! ሐምሌ 19/67 የመጀደት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

ሐምሌ 19/67 የመጀደት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በመደበኛ በጀት እና ከድጎማ በጀት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል።

1. የደንብ ልብስ እና የስፌት
2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
3. ህትመት ሥራዎች
4. አላቂ ትምህርት መርጃ (ዕቃዎች)
5. የፅዳት ዕቃዎች
6. ቋሚ ዕቃዎች
7. የህንፃ፤ (ኤሌክትሪክ የቧንቧ እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች)
8 ማሽነሪ ጥገና(ኮምፒውተር ፤ ፕረንተር ፤ ፎቶ ኮፒ፤ ማባዣ ማሽን) መግዛት እን ማስጠገን አንዲሁም
9. አሮጌ ቆርቆሮ ለመሸጥ በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የምዝገባ ምስክት ወረቀት

2.በዘርፉ የተሰማሩበት ፍቃድ በዕቃ አቅራቢነት እና አገልግሎት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገበ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) & የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ።

3.ጨረታውን መወዳደር የሚችሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢ/ፕራይዝ እሴት የሚጨምሩ (አምራች) ሲሆን አደራጅ ተቋሙ በሚፅፍላቻው ደብዳቤ ያለከፍያ መወዳደር ይችላሉ።

4.ተወዳዳሪዎች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ከጨረታ መከፈቻ ቀን በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

5.ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የሚቆይ ሆኖ ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን በእለቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 102 ይከፈታል።

አድራሻ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከስዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ወረዳ 7ስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ ሆኖ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ: በስልክ ቁጥር 011-127-53-72/011-154-69-29 ይም 011-127-08-96 ደውሎ
መጠየቅ ይቻላል።

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/63060de9dcdb02191617e699?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://%E1%89%A02merkato.com) (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።