Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ኘሮጀክት ማንዋል | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ኘሮጀክት ማንዋል ክለሳ የአማካሪ (Consultancy) በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል

1.ከላይ የተጠቀሰውን ግዥ ለማቅረብ ብቃት ያላቸው አቅራቢዎች የታሸገ የጨረታ ሰነድ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን (ዋናው መ/ቤት) እንድታቀርቡ ትጋበዛላችሁ።
ከላይ የተጠቀሱት ግዥዎች ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ፤
•በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት፤
•የተፈረመ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል መግቢያ ቅፅ፤
•የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሠርተፊኬት፤
•የ2014 የታደሰ የንግድ ፈቃድ
•የአገር ውስጥ የታhስ ከሊራንስ ይሆናል።

2. ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

3 አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለከፍያ በነጻ ይሠጣቸዋል።

4. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትከ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም እና የጨረታው አይነት ተጠቅሶ የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም ።

ጨረታው ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ነሃሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት አድራሻ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ (ዋናው መ/ቤት) ቁጥር 9
ጨረታው የሚሸጥበት አድራሻ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 9
ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/63037313dcdb02191617e561?lang=am ይመለክቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።