Get Mystery Box with random crypto!

ጨረታ ! ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2015 ዓ.ም. ለወረዳ አገ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ጨረታ !

ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2015 ዓ.ም. ለወረዳ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ፡-
• አላቂ ዕቃ
• ቋሚ ዕቃ
• የፅዳት ዕቃ
• የሰራተኞች የደንብ ልብስ
• መስተንግዶዎች እንዲሁም
• የፓርትሽን /የጥገና/ ስራዎችን እና
• የትራንስፖርት አገልግሎት

በ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው እና ለሚመለከተው ስራ በኮንስትራክሽን ዘርፍ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት /VAT/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. ቲን ነምበር /TIN NO/ ምዝገባ ማቅረብ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፍል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

5. ጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በCPO ማስያዝ አለባቸው/ዎት/።

6. የጨረታው ማስታወቂያ የሚያበቃበት በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ሲሆን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታው ሳጥን ይታሸጋል። በዚሁ እለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥን ይከፈታል።

አድራሻ የካ አባዶ ገደራ ገዛኸኝ ህንፃ አራተኛ ፎቅ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 893 1825/011 893 1228/ ይደውሉ
ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/630362f0dcdb02191617e541?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።