Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ የኮንስትራክሽን ጨረታ! የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ 2015 በጀት | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ የኮንስትራክሽን ጨረታ!

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ 2015 በጀት አመት የሚከተሉትን የግንባታ ስራዎችን ለማሠራት ይፈልጋል

1. የችሎት አዳራሾችን እድሳትና ምቹ የማድረግ ሥራ

2. ከፍርድ ቤቱ ውጪ እና ውስጥ ያሉ ቦታዎች ላይ የምድረ ግቢ የማስዋብ ስራ እና አዲስ የግቢ መግቢያ በር ግንባታ ሥራ

3 የአስተዳደር ህንጻ፤ የአቃቤ ህግ ህንጻ ጥገና የመፀዳጃ ቤት እድሳት እንዲሁም የአስተዳደር ህንጻ መግቢያ የሚገኝ የምድረ ግቢ የማስዋብ ሥራ

4 የፍርድ አፈፃፀም የተሽከርካሪ ማቆሚያ ይዞታ ላይ ለህንፃ ግንባታ የሚያስፈልገውን የዲዛይን ስራና የአማካሪ ቅጥር ማከናወን ስራ ማሰራት ይፈልጋል።

ከላይ የተጠቀሰውን ግዥ ለማቅረብ (ለማቅረብ) ብቃት ያላቸው አቅራቢዎች

በታሸ የጨረታ ሰነድ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን (ዋናው መ/ቤት) እንድታቀርቡ ትጋበዛላችሁ ጨረታው ቦሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት የመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸው በግልጽ የጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል ከላይ የተጠቀሱት ግዥዎች ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ

1. ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለመግዛት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

2. አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለከፍያ በነጻ ይሠጣቸዋል።

3 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ወይም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር (ዋናው መ/ቤት) ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል።

4. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ከፍያ ዋስትና ምትከ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም እና የጨረታው አይነት ተጠቅሶ የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም በጨረታ ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በ4:10 ሰዓት ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/6300ab9665fcad7e9432d911?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።