Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ የመድኒት ፣ ጤና ክብ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ የመድኒት ፣ ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል።

1- የሆቴል አገልግሎት (ለአንድ ዓመት ኮንትራት)
2- የህትመት አገልግሎት
3- የተሽከርካሪ እጥበትና ግሪስ (ለአንድ ዓመት ኮንትራት)
4- የመስኮት መጋረጃ ከነሙሉ አክሰሰሪው
5- መስተንግዶ ውሃ ቆሎ (ለአንድ ዓመት ኮንትራት)

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።

1.ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
2.አነስተኛና ጥቃቅን ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3.የመንግሥት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው።
4.ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5.ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 601 ማግኘት ይችላሉ።
6.ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን 10፡30 ታሽጐ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ለአላቂ ዕቃዎች ተጫራቾች ከጨረታው በፊት ሣምኘል ማቅረብ አለባቸው።

አድራሻ :-ቦሌ መንገድ ፍላሚንጐ ጐን ቶሚ ታወር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/62ff3ae765fcad7e9432d8b5?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።