Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ ! በጉለሌ ክ/ከተማ የአዲስ አበባ ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ !

በጉለሌ ክ/ከተማ የአዲስ አበባ ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1፡-አላቂ የጽሕፈት መሳሪያ
2፡- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
3፡- የደንብ ልብሶች
4፡- የደንብ ልብስ ስፌት
5፡- የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
6፡- የላብራቶሪ ዕቃዎች
7፡- የስፖርት ዕቃዎች
8፡- ህትመት
9፡- ቋሚ ዕቃዎች
10፡- ጥገና የኮምፒውተር ፤ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማባዣ ማሽን

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፦

1.በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ ሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።

2.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

3.በጨረታው የሚወዳደር የግዥው ጠን ከ100,000 በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው።

4.በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የራሳችሁን እሴት ያልጨራችሁ እና አምራች ያልሆናችሁ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ 100 ብር በመክፈል እና ሲፒኦ በማስያዝ መወዳደር ትችላላችሁ።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አአቁ1, የመጀ ደ.ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋናውንና ቅጅውን በጥንቃቄ በታሸ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10/ለአሥር] ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ዋጋ በመሙላት ማስገባት አለባችሁ።

7 .በአስረኛው ቀን 11:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአሥራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸO በተገኙበት አ/ቁ//የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁ.3 የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 3 00 ሰዓት ይከፈታል።

8.አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አዲስ አበባ ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ከፍል ማቅረብ አለባቸው።

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/62fdf1ef65fcad7e9432d859?lang=am ይመልክቱ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።