Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ ! የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለው በጀት የጥገና እቃዎች | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ !

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለው በጀት የጥገና እቃዎች
1የቧንቧ እቃዎች
2 የኤሌከትሪክ እቃዎች
3 የግንባታ እና የአናጺ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል።

1.ከላይ በተጠቀሰዉን ግዥ ለማቅረብ (ለማቅረብ) ብቃት ያለቸው አቅራቢዎች በታሸ የጨረታ ሰነድ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን (ዋናው መ/ቤት) እንድታቀርቡ ትጋበዛላችሁ። ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞhራሲያዊ ሪፑብሊ መንግሥት የመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸዉ በግልጽ የጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል። ከላይ የተጠቀሱት ግዥዎች ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የዘመኑን የታደሰ ጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለሆናቸው የምስhር ወረቀት፤ የተፈረመ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃለ መግቢያ ቅፅ የግብር ከፋይ መለያ(TIN) ሠርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታስ ምዝገባ ሰርተፍኬት በ2014/2015 የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአገር ውስጥ ገቢ ታስ ክሊራንስ ይሆናል።

2. አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለክፍያ በነጻ ይሠጣቸዋል።

3. ጨረታው ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በ8:00 ሰዓት ጠዋት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ማስገባት ይሆናል፡፡

4. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትከ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም እና የጨረታው አይነት ተጠቅሶ የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታዉ ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም በ4:10 ሰዓት ጠዋት ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/62f244c72562a546f6cfc295?lang=am ይመልከቱ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።