Get Mystery Box with random crypto!

ስኬታማ ህይወት

የቴሌግራም ቻናል አርማ kci12 — ስኬታማ ህይወት
የቴሌግራም ቻናል አርማ kci12 — ስኬታማ ህይወት
የሰርጥ አድራሻ: @kci12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 597
የሰርጥ መግለጫ

ሳይኮሎጅ አዘል ቁምነገሮች አንዲሁም ትምህርቶች የሚስተናገዱበት መድረክ ነው።
Share the link
https://t.me/kci12 ስኬታማ_ህይወት
ዉድ የቴሌግራማችን ቤተሰቦች እኛን ስለመረጣችሁ እናመሰግናለን::
ውድ ደንበኞቸ ያላችሁን መጽሀፎች; ጥቅሶች እና ሳይኮለጅወች በዚህ ሊንክ ይላኩልን።
@kci21

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-02 07:00:14 #የተጋበዝከውን_ሁሉ_አታግበስብስ

የሆነ ሰው በምክንያትም ይሁን ያለ ምክንያት ሊያበሳጭህ ወይም ሊያናድድህ ቢጀምር ልክ በዚያ ቅፅበት የተቀበልከውን ነገር በአይነት መመለስ እንደማይገባህ አስታውስ፡፡ ምክንያቱም ላናደደህ ሰው እንደዚያው አይነት ምላሽ ስትሰጥ ወደ ሰውዬው ሃሳብ ተወሰድክ ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው ሲያበሳጭህ ተረጋግተህ እና ራስህን ተቆጣጥረህ እሱ እንዳደረገው አይነት ምላሽ ከመስጠት ከተቆጠብክ የሰውነቶችህን አካላት ሁሉ በመደበኛ ስራቸው ላይ ሳይረበሹ እንዲቆዩ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ይህም በምክንያት እንድትመራ የሚያስችልህ የዘወትር ተፈጥሮህ ነው፡፡

ስለዚህ ሁልጊዜ ሌሎች ባቀረቡልህ ግብዣ በመወሰድ ራስህን በሌሎች ቁጥጥር ስር ላለማዋል ተጠንቀቅ፡፡ ይልቁንም ግብዣውን አንተ ለማድረግ ሞክር፡፡ ሰዎች ብዙም በማያውቋቸው መሳሪያዎች አማካኝነት የመጋበዙን ቅድሚያ ውሰድ፡፡ ያን ጊዜ ሌሎችን የምትቆጣጠረው አንተ ትሆናለህ፡፡

ሁሉም ነገር የሚስበው የሚመስለውን ነው፡፡ ይህ መቼም የማይካድ ሃቅ ነው፡፡

#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ
ናፖሊዮን ሂል

*
ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት
@kci21
1.6K views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 06:51:14 #የሰው_ልጅ_ትልቁ_ፍርሀት

በህይወት መኖር በራሱ ትልቅ ፍርሃት ነው። ትልቁ ፍርሃት ሞት አይደለም፤ በሕይወት የመኖርን አደጋ (risk) መጋፈጥ እንጂ፡፡ የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት እራሱን የመሆን ፍርሃት ነው።

ከልጅነታችን ጀምረን የተማርነው የሌሎች ሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት መኖርን ነው። ተቀባይነት ማጣትን እና በሌሎች አይን በቂ ሆኖ አለመታየትን አምርረን ስለምንጠላ፣ በሌሎች ሰዎች አመለካከት ታስረን መኖር እጣ ፈንታችን ሆኗል፡፡

ትልቁን ፍርሀት ለማስወገድ ደግሞ የሕይወት ፍልስፍና መጽሐፍ ይረዳናል።

#የሕይወት_ፍልስፍና መጽሐፍ
1.6K views03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 13:56:19 ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
≈ዶ/ር ምህረት ደበበ

1. ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።

6. አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ።ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው።ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመስግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመስግን።

9. ያለስስት አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን
ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ-ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው
ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።

16. ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው።ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ።
1.6K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-30 18:07:25 ቃልህን የማትጠብቅ ከሆነ ፈፅሞ ቃል አትግባ

በአንዲት በረዶአማ ምሽት አንድ ቢሊየነር አንድ ምስኪን ከቤቱ ውጪ ይመለከትና እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል። "በዚህ ቅዝቃዜ እዚህ ስፍራ ተቀምጠህ አይበርድህም! ኮት እንኳ አለበስክም?" አዛውንቱ ሰውዬም "ኮት እንኳ የለኝም ቀድሞ ነበረኝ ግን" አሉት። ቢሊየነሩ በመገረም "ጠብቁኝ ወደቤት ልሂድና ይዤሎት እመጣለሁ" ሲል ቃሉን ሰጥቷቸው ተጓዘ።

ምስኪኑ አዛውንትም በደስታ ተሞልተው እንደሚጠብቁት ነገሩት። ይህ ቢሊየነር ወደቤቱ ይገባና በራሱ ጉዳይ ተጠምዶ አዛውንቱን ይዘነጋል። በነጋታው ማልዶ ከእንቅልፉ ሲነቃ እኚሁ ምስኪን አዛውንት ትውስ ይሉትና ሊፈልጋቸው ወደስፍራው ሲያቀና በቅዝቃዜው ሳቢያ ህይወታቸው አልፎ ከስፍራው ያገኛቸዋል።

በስፍራው ግን አንዲት ወረቀት ትተው ነበር ያረፏት እንዲህም ይላል "የሚያሞቁ ልብሶች በሌሉኝ ቀናት ብርዱን የመቋቋም ጥንካሬው ነበረኝ ፣ ነገር ግን ልትረዳኝ ቃል በገባህ ወቅት ለቃልህ ተምበረከኩ እናም ጥንካሬዬን አጣሁ።"

"ቃልህን የማትጠብቅ ከሆነ ፈፅሞ ቃል አትግባ። ላንተ ላያስፈልግ ይችላል ነገር ግን ለሌላው ሁሉ ነገሩ ነው።"
1.6K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 20:11:38 #ራስህን_ጭንቅላት_እንደሌላት_ዶሮ_አታድርግ

“ምንም ያለማድረግህን ዝቅ አድርገህ አትመልከተው። ምንም ባለማድረግህ ሰምተኸው የማታውቀውን አእምሮህን ትሰማዋለህ፤ እና ስክነት ውስጥም በመግባት ሰላምህን ታገኛለህ”
#ዊኒ_ዘ_ፑ

“እንዴት ነህ?” ለሚለው ጥያቄ ምን ያህል ጊዜ “ኑሮ ሊያሳብደኝ ነው፣ በዚህ ስራ፣ በዚህ ቤተሰብ … ወጥረው ይዘውኛል” ብለህ መልሰሃል?

ለመጨረሻ ጊዜስ መቼ ነው የምታውቀው ሰው

“እንዴት ነህ?” ሲልህ፣

“ኑሮ ተመችቶኛል። ፈታ ብያለሁ፤ ምንም ስራ እየሰራሁ አይደለም” ብለህ የምታውቀው?

ሁሉም ሰው ይጣደፋል - ስራ፣ ስራ፣ ስራ
ግን መጨረሻው የት ነው?ለምንስ ነው እንሰራቸዋለን ብለን እቅድ ያወጣንላቸውን ነገሮች ጨርሰን ፈታ የማንለው?

ሰዓታቶቻችንን ገቢ በሚያስገኝ ወይም ስኬታማ ያደርገናል ብለን በምናስበው ነገር ላይ ካላዋልናቸው የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማናል። ለሆነ ያህል ጊዜ ምንም ነገር ካልሰራህ እንደምትወድቅ ታስባለህ። መዝናናት እና እረፍት መውሰድ የቅንጦት ይሆንብሃል። ሰዓታችንን መቆጠቢያ ቴክኖሎጂዎች፣ መሳሪያዎች እና መገልገያዎች ቢፈጠሩልንም፣ ያገኘነውን ትርፍ ጊዜም ምንም ባለመስራታችን በሚፈጠርብን ሽብር - ጭንቀት ውስጥ በመግባት እናሳልፈዋለን።

በ ዘኢኮኖሚስት ዘገባ መሰረት “‘የግለሰባዊነት ባህል' ከማህበረሰባዊ ትስስር ይልቅ የግለሰቦችን ስኬታማነት ያገናል፤ ‘ጊዜ ገንዘብ ነው' የሚለውን አስተሳሰብም በሁሉም ሰው ጭንቅላት ውስጥ እንደመርህ እንዲቀመጥ ሆኗል። ይህም እያንዳንዷ ቅጽበታችንን ወደ ገንዘብ ለመቀየር እንድንጣደፍ አደረገን።”

ራስህን ጭንቅላት እንደሌላት ዶሮ ከዚህ እዚያ ሲሮጥ አግኝተኸው ታውቃለህ? ስኬታማ ያደርጉልኛል የምትላቸውን ነገሮች ለሟሟላትስ እዚህ እዚያ ስትል ትውላለህ? ወይንስ ምንም ስራ እየሰራህ ስላልሆነ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብለህ ትራወጣለህ?

በል ቶሎ ጭንቅላትህን አጽዳ

#ጭንቅላትህን_አጽዳ መጽሐፍ

@kci21
1.8K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 07:08:05 #ዛሬ_ውብ_ቀን_ነው_እኔ_ግን_አላየውም!

"ማየት የተሳነኝ ነኝ እባካችሁ እርዱኝ" የሚል ጽሑፍ ከፊት ለፊቱ አስቀምጦ በፈጣሪ ስም ይለምናል። አልፎ አልፎ ሳንቲም ቅጭል ይላል የምፅዋት መጣያ ባርኔጣው ውስጥ። ረፋዱ ላይ አንድ መንገደኛ ተመፅዋች የፃፈውን ጽሑፍ ካነበበ በኋላ ብዕር አውጥቶ ጽሑፉን ቀይሮት ሄደ።

ብዙም ሳይቆይ ባርኔጣው በሳንቲሞች ሞልቶ መፍሰስ ጀመረ።

ከሰዓት በኋላ ያ ሰው ውጤቱን ለማየት ተመልሶ ሲመጣ ተመፅዋች በኮቴው ለየውና "አንተ ነህ አይደል ፅሑፌን የቀየርከው? ለመሆኑ ምን ብለህ ፅፈህ ነው የሳምንቱን ገቢ በሶስት ሰዓት ያንበሸበሽከኝ?" አለው በመደነቅ ስሜት።

አስተዋዩም ልጅ:-

"በአንተ ሃሳብ ላይ ትንሽ ለውጥ ነው ያደረኩት። ምን ብዬ መሰለህ ፡-

"ዛሬ ውብ ቀን ነው እኔ ግን አላየውም!" ብዬ ነው የፃፍኩት።

"አየህ! ያንተ ጽሑፍ ያንተን አለማየት ብቻ እንጂ ማየት መቻል መታደል መሆኑን ለሰዎች አያስተምርም። ሰዎች ምስጋናቸውን ለፈጣሪ፣ ምጽዋት ላንተ በመስጠት የገለፁልህ ለዚህ ነው።"

ምን እንማር ከዚህ? ጥቂት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚፈጥረውን ተአምር ወይስ ምስጋናን?

ዛሬ ውብ ቀን ነው... እናንተ ግን እያያችሁት ነው?

@kci21
1.6K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 13:46:32 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላቹ

• በሌላ ሰዉ ትተካለህ አለቀ! ምንም ያህል ጎበዝ ብትሆን ቦታህን 'ከለቀክ' ካንተ የሚሻል ወይም ተመጣጣኝ ችሎታ ያለዉ ሰዉ ይተካሃል

• ሰዎች በልባቸዉ መኖርህን ከቁብም አይቆጥሩት

• የሆነ ሰዉ መልእክት ልከህለት ካልመለሰልህ ለምን አልመለሰልኝም ብለህ ሌላ አተካራ ዉስጥ አትግባ፡፡ በግድ የሆነ ጓደኝነትና የፍቅር ግንኙነት የትም አይደርስም

• ለነገሮች ትንተና አትስጥ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ሰአት ብቻ እንጂ ስለእያንዳንዱ ነገር ገለፃ የምታደርግ ከሆነ እራስህን ታደክማለህ

• ሰዎችን መቼም ቢሆን ለመለወጥ አትነሳ፡፡ ማንም ቢሆን ላንተ ብሎ እራሱን አይቀይርም፡፡ ሲጋራ የሚያጨሰዉን ሰዉ 'አታጭስ' ስላልከዉ ማጨሱን አያቆምም ይልቅስ ለምን ማጨስ እንደማያስፈልገዉ የሚረዳበትን ፍንጭ አሳየዉ...እምቢ ካለ አፈግፍግ

• ከራስህና ከሚቀርቡህ ሰዎች ምረጥ ብትባል እራስህን ምረጥ፡፡ ይሄ እራስ ወዳድ መሆን ሳይሆን በከባዱ የህይወትህ ሰአት የራስ ማንነትህ ከሌሎቹ በተለየ መንገድ እንዴት እንዳሳለፈ ያዉቀዋል

• አንተ ጋር ብቻ ያለ ፍቅር ከምትወደዉ ሰዉ ዉስጥ ከሌለ እራስህን እያጎሳቆልክ ነዉና አሁኑኑ አቁም

• የመጥፎ ባህሪ ድግግሞሽ የህይወት መርዝ ነዉ

• ለማንም ቢሆን እራስህን ግልጥልጥ አድርገህ አታሳይ ምክንያቱም 90 ፐርሰንት የሚሆነዉ ሰዉ ማንነትህን እስከጥጉ ካወቀ በደካማዉ ጎንህ መጫወት ይጀምራል

• ሰዎች እንደሚወዱህ ቢነግሩህና ጥሩ ለመሆን ብትሞክርም አንተ ላይ መፍረዳቸዉን አያቆሙም

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን
1.5K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-18 20:30:04 #ዓላማህን_ለማሳካት_ያለህን_አቅም_ሁሉ_ተጠቀም

አባትና ልጅ በጫካ ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ፤ ልጁ አባቱን ጥያቄ# ይጠይቀዋል፦

"አባቴ ይህን ዛፍ ብገፋው ቅርንጫፎቹን ማነቃነቅ አልችልም?" አለው። "እንዴታ! ሙሉ አቅምህን ተጠቅመህ ከሞከርክ የማትችለው ነገር የለም!" ሲል መለሰለት።

ልጁም ሙከራውን ጀመረ። ይሁንና ግን ዛፉ ትልቅ በመሆኑ ቅርንጫፎቹን ሊወዘውዝ አልቻለም። "አባቴ ተሳስተሀል! እኔ ይህን ማድረግ አልችልም!" አለው።

"እንደገና ሞክር!" አለው አባቱ። ልጁ የቻለውን ያህል ቢገፋም ቅርንጫፎቹ አልተነቃነቁም። ብዙ ሞከረ ግን አልሆነም። "አባቴ አልችልም!" አለው ተስፋ በመቁረጥ!

አባቱም፦ "ልጄ አቅምህን በሙሉ ተጠቀምና ሞክር ነበር፤ ያልኩህ ግን አላደረከውም!" ሲል መለሰለት። "ከዚህ በላይ?" ልጁ ግራ ተጋባ። "አዎ! እኔን መቼ ለእርዳታ ጠየከኝ?" ሲል ልጁ ያልጠበቀውን ምላሽ መለሰለት።

ቁምነገር

በዙሪያችን ያሉትን አማራጮች፣ እድሎች፣ ድጋፎች፣ ተስፋዎች፣ ብርታቶች...ወዘተ ሳንጠቀም አንድ ነገር "አልተሳካልኝም!" ብለን ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። ማንም በራሱ ሙሉ አይደለም፤ ድጋፍ እና እርዳታ ይፈልጋል።

በሌላው ተስፋ አለመቁረጥ ውስጥ፣ በሌላው ብርታት ውስጥ፣ በሌላው መጽናናት ውስጥ ሀይላችንን ልናገኘው እንችላለን።

እርዳታ የጠየቅናቸው ሰዎች ባይተባበሩን የተሳሳተ ሰው መጠየቃችንን ወይም አጠያየቃችንን መለወጥ እንዳለብን አልያም በሌላ ጊዜ መጠየቅ እንዳለብን እንጂ፤ እርዳታ መጠየቃችን ነውር ነው ማለት አይደለም!

በዙሪያችን ያለውን እድል ሁሉ አሟጠን መጠቀም ለህልማችን መሳካት መሰረት ነው። መረዳዳትን እንደ እምነት፣ ባህል፣ ስልጡንነት አድርገን እናስብ

(Abebayehu Aseffa Tkursew እንዳጋራው)

: @kci21
1.4K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 07:04:26 #ህልምህ_የሀሳብ_ኩሽና_ሲሆን

ሀብታም ለመሆን ከሚያስችሉህ ስጦታዎች አንዱ ህልም ነው። ህልም የሃሳብ ኩሽና ሲሆን ሁለት አይነት እምነቶችንም ታበስልበታለህ -

ከምታውቀው እና ከከባቢህ ከምታገኛቸው ግብዓቶች የሚዘጋጅ -

“እንደ ኃይሌ ገ/ስላለሴ አይነት ቤት ውስጥ ስኖር ይታየኛል”

“የምወልደውን ልጄን በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያድጋል”

“ስፖርት ባር ውስጥ ላሉት ሰዎች በሙሉ ቢራ ስገዛ ይታየኛል” ወዘተ


ካልተፈጠሩ እና በሃሳብ ካለ ዓለም ስበህ ከምታመጣቸው ግብዓቶች የተሰራ - የመጀመሪያውን የጨረቃ ጉዞ ማሰብ፣

የመጀመሪያው ሰማይ ጠቀስ ህንጻን መስራት፣ በባትሪ የሚሰራ የቢራ ጠርሙስ መክፈቻ መስራት ወዘተ

ህልም ስናልም በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶቻችን አንገደብም ወይም ቤተሰቦቻችን፣ ማህበረሰቡ እና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ያስቀመጡልንን ገደብ ማለፍ እንችላለን። ህልምህ ውስጥ አሁን የምትኖረው “እውነታ” የለም። እንደፈለግክ፣ እንዳሻህ ማሰብ ትችላለህ። ሁሉም ነገር ልብህ እንደፈቀደው እና ህልምህ እንደመራህ ይሆናል።

ሕይወትህን ለመቀየር ትልቅ ህልም ማለምህ ወሳኝ ነው፤ ራስህን አሁን ካለህበት ሁኔታ የተሻለ ቦታ ሆኖ እንዲያልም ፍቀድለት።

“እሺ፣ ሃምሳ ስምንት አመቴ ነው፤ ጫማ ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥሬ እሰራለሁ፤ በማገኘው ገቢም ሚስቴን እና ሁለት ልጆቼን አስተዳድራለሁ፤ እና በባህር ዳር ደሴቶች ላይ የራስህን ሆቴል መገንባት ትችላለህ እያልከኝ ነው? በተአምር ይሄ ይሆናል ብዬ በእውኔም በህልሜም ማሰብ አልችልም መቼም!”

ትልቅ ህልም ለማለም አንሞክርም፤ ምክንያቱም ሃሳቡ የእብደት ይመስለናል። ያው ቀኑን ሙሉ ሚልዮን ገንዘቦችን ባገኝ ይህን አደርጋለሁ፣ ይህን እገዛለሁ እያሉ መዋል ቀላል ነው፤ ሆኖም የእውነት የምር ስለ አንድ ሚልዮን ብር ማለም ይከብዳል።

አንድ ሚልዮን ብር ባገኝ ስትል፣ ሃሳብህ ውስጥ “አላገኝም እንጂ” የሚል ድምጸት አለ። ራስህን ልክ አንደ አንድ ሚልዮን ብር እንዳለው ሰው አስበህ ማለም ይጠበቅብሃል፤ ህልምህ ውስጥ “ቢሆን…” የሚል ቃል መኖር የለበትም - በቃ ሆኗል!!


#ተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ
1.3K views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-19 21:41:20 "በመኖር ላይ ሳለ ሞተ"
ይህ አባባል ከ30 በላይ የሚሆኑ መፃህፍትን ፅፎ፤ ከ55 በላይ በሆኑ የአለማችን ቋንቋዎች ተተርጉመው፤
190 ሚሊዮን በላይ ቅጂ የተሸጠለት የታዋቂው ብራዚላዊ ደራሲ #ፖውሎ_ክዌሎ ነው፡፡
ክዌሎ በአንድ ወቅት ከአንድ ጋዜጠኛ "ስትሞት አለም እንዴት ቢያስታውስህ ትመርጣለህ?" ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡
"እኔ ከሞትኩ በኀላ አለም እንደፈለገው አድርጎ ቢያስታውሰኝ ግድ የለኝም፤ ነገር ግን ስሞት መቃብሬ ላይ "በመኖር ላይ ሳለ ሞተ" ተብሎ እንዲፃፍ እፈልጋለው" ነበር ያለው፡፡
ክዌሎ ለምን እንዲህ እንዳለ ሲጠየቅ "ብዙዎች በስጋ ከመሞታቸው በፊት በመንፈስ ሙተዋል፤ ልዩነቱ በሳጥን ተደርገው ጉድጓድ አለመግባታቸው ነው፡፡ እኔ ግን እየኖርኩ ነው፤ የልጅነት ህልሜ የሆነውን ደራሲ መሆን አሳክቻለው፡፡ በእየቀኑም አዳዲስ ነገርን ለመመልከት እሞክራለው" በማለት መልሷል፡፡
እኛስ እየኖርን ነው ያለነው ወይስ ሞተናል ? ሁሉም ለራሱ ሊጠይቀው ይገባል፡፡፡፡፡፡

@kci21
@kci21
1.4K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ