Get Mystery Box with random crypto!

ቃልህን የማትጠብቅ ከሆነ ፈፅሞ ቃል አትግባ በአንዲት በረዶአማ ምሽት አንድ ቢሊየነር አንድ ምስ | ስኬታማ ህይወት

ቃልህን የማትጠብቅ ከሆነ ፈፅሞ ቃል አትግባ

በአንዲት በረዶአማ ምሽት አንድ ቢሊየነር አንድ ምስኪን ከቤቱ ውጪ ይመለከትና እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል። "በዚህ ቅዝቃዜ እዚህ ስፍራ ተቀምጠህ አይበርድህም! ኮት እንኳ አለበስክም?" አዛውንቱ ሰውዬም "ኮት እንኳ የለኝም ቀድሞ ነበረኝ ግን" አሉት። ቢሊየነሩ በመገረም "ጠብቁኝ ወደቤት ልሂድና ይዤሎት እመጣለሁ" ሲል ቃሉን ሰጥቷቸው ተጓዘ።

ምስኪኑ አዛውንትም በደስታ ተሞልተው እንደሚጠብቁት ነገሩት። ይህ ቢሊየነር ወደቤቱ ይገባና በራሱ ጉዳይ ተጠምዶ አዛውንቱን ይዘነጋል። በነጋታው ማልዶ ከእንቅልፉ ሲነቃ እኚሁ ምስኪን አዛውንት ትውስ ይሉትና ሊፈልጋቸው ወደስፍራው ሲያቀና በቅዝቃዜው ሳቢያ ህይወታቸው አልፎ ከስፍራው ያገኛቸዋል።

በስፍራው ግን አንዲት ወረቀት ትተው ነበር ያረፏት እንዲህም ይላል "የሚያሞቁ ልብሶች በሌሉኝ ቀናት ብርዱን የመቋቋም ጥንካሬው ነበረኝ ፣ ነገር ግን ልትረዳኝ ቃል በገባህ ወቅት ለቃልህ ተምበረከኩ እናም ጥንካሬዬን አጣሁ።"

"ቃልህን የማትጠብቅ ከሆነ ፈፅሞ ቃል አትግባ። ላንተ ላያስፈልግ ይችላል ነገር ግን ለሌላው ሁሉ ነገሩ ነው።"