Get Mystery Box with random crypto!

'በመኖር ላይ ሳለ ሞተ' ይህ አባባል ከ30 በላይ የሚሆኑ መፃህፍትን ፅፎ፤ ከ55 በላይ በሆኑ የአ | ስኬታማ ህይወት

"በመኖር ላይ ሳለ ሞተ"
ይህ አባባል ከ30 በላይ የሚሆኑ መፃህፍትን ፅፎ፤ ከ55 በላይ በሆኑ የአለማችን ቋንቋዎች ተተርጉመው፤
190 ሚሊዮን በላይ ቅጂ የተሸጠለት የታዋቂው ብራዚላዊ ደራሲ #ፖውሎ_ክዌሎ ነው፡፡
ክዌሎ በአንድ ወቅት ከአንድ ጋዜጠኛ "ስትሞት አለም እንዴት ቢያስታውስህ ትመርጣለህ?" ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡
"እኔ ከሞትኩ በኀላ አለም እንደፈለገው አድርጎ ቢያስታውሰኝ ግድ የለኝም፤ ነገር ግን ስሞት መቃብሬ ላይ "በመኖር ላይ ሳለ ሞተ" ተብሎ እንዲፃፍ እፈልጋለው" ነበር ያለው፡፡
ክዌሎ ለምን እንዲህ እንዳለ ሲጠየቅ "ብዙዎች በስጋ ከመሞታቸው በፊት በመንፈስ ሙተዋል፤ ልዩነቱ በሳጥን ተደርገው ጉድጓድ አለመግባታቸው ነው፡፡ እኔ ግን እየኖርኩ ነው፤ የልጅነት ህልሜ የሆነውን ደራሲ መሆን አሳክቻለው፡፡ በእየቀኑም አዳዲስ ነገርን ለመመልከት እሞክራለው" በማለት መልሷል፡፡
እኛስ እየኖርን ነው ያለነው ወይስ ሞተናል ? ሁሉም ለራሱ ሊጠይቀው ይገባል፡፡፡፡፡፡

@kci21
@kci21