Get Mystery Box with random crypto!

ሞክረው እስቲ ! ስራህን መቀጠል ከብዶሀል ? ማወላወል ህይወትህ ላይ ከበድ ያለ ተፅዕኖ አየፈጠረ | ስኬታማ ህይወት

ሞክረው እስቲ !

ስራህን መቀጠል ከብዶሀል ? ማወላወል ህይወትህ ላይ ከበድ ያለ ተፅዕኖ አየፈጠረብህ አስቸግሮሀል ? ከሰዋች ጋር ባለህ ግንኙነት እየረካህ አይደለም ? ጓደኝነትህን ማስቀጠል ከብዶህ እየሸሸህ ተቸግረሀል? ሰዋችን ማመን ከብዶሀል ? ስራህ ላይ እምነት አጥተሀል ?

ስለዚህ ወንድሜ አንድ በህይወትህ ያጎደልከው ነገር አለ ማለት ነው ፤ ይቅርታ ያላደረግህላቸው ሰዋችና አጋጣሚዋች በህይወትህ አሉ ማለት ነው ፤ እንዴት ሊሆን ይችላል ብለህ እያሰብክ ይሆናል እመነኝ ወንድሜ ይቅርታ አለማድረግ ከምንም በላይ የሚያደክምና ወደፊት ለመሄድ በፍፁም የሚከለክል መሰናክል ነው ሞክረውና እየው እመነኝ ለውጡን እኔ እንዲህ ነው ከምልህ በላይ አይተህ የምትረዳው ይበልጣል!

መልካም ቀን ተመኘን