Get Mystery Box with random crypto!

#ሰውየው አንድ ትልቅ በሬ አርዶ የብረት ምድጃውን ለኩሶ ለልጁ እንዲህ አለው 'የምንወዳቸውንና የም | ስኬታማ ህይወት

#ሰውየው አንድ ትልቅ በሬ አርዶ የብረት ምድጃውን ለኩሶ ለልጁ እንዲህ አለው "የምንወዳቸውንና የምናከብራቸውን ጎረቤቶቻችንን #አብረውን እንዲበሉ ሄደህ ጥራቸው ።”

#ልጁ ወደ ጎዳና ወጥቶ እንዲህ ሲል መጮህ ጀመረ “እባካችሁ የአባቴ ቤት በእሳት ስለተያያዘ ለማጥፋት እርዱን ድረሱልን!" ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጥቂት ሰዎች መጡ ሌሎቹ የእርዳታ ጩኸቱን እንዳልሰሙ ሆነው ቀሩ ። የመጡ ሁሉ ግን በሉ ጠጡ ።

#ባየው ነገር የተደናገጠው አባት ወደ ልጁ ዞሮ እንዲህ አለ "የመጡትን ሰዎች እኔ አላውቃቸውም ከዚህ በፊትም አይቼአቸው አላውቅም ስለሆነም ወዳጆቻችን ቤተሰቦቻችንና የሥራ ባልደረቦቻችን የት አሉ?"

#ልጁም "ከቤታቸው ወጥተው የመጡት ሰዎች ቤታችን ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ጩኸት ሰምተው ሊረዱን እንጂ በቤታችን የተዘጋጀውን ፓርቲ ሊካፈሉ አይደለም ። ግብዣችንና እንግዳ ተቀባይነታችን የሚገባው ለእነዚህ ዓይነቶቹ ነው" አለ ።

#ሁሉም የምትወዷቸውና የምታከብሯቸው ሰዎች እውነተኛ ወዳጆቻችሁ ላይሆኑ ይችላሉ ። እውነተኛ ወዳጅ ማለት በተቸገራችሁና የእነርሱ ድጋፍ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ፈጥነው ከጎንዎ የሚገኙ ናቸው ። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ስለእርስዎ የሚጨነቁትን እውነተኛ ሰዎች ለማወቅ ጥረት ያድርጉ ።

ሰናይ ቀን