Get Mystery Box with random crypto!

#አትፍረድ ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) Part ➋➍ እሁድም ስለሆነ ብዙም ከቤት ለመ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#አትፍረድ

ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➋➍


እሁድም ስለሆነ ብዙም ከቤት ለመውጣት አላሰኘኝም። እናቴ በጠዋት እድር ለመክፈል ወጥታለች፡ ከበረንዳው ላይ ሆኜ ጊቢውን በዝምታ እየቃኘሁ ሳለ የጊቢው በር ይንኳኳ ጀመር፡ ከሰራተኛዋ ቀደም ብዬ ወደ በሩ በመሄድ የተዘጋውን የጊቢ በር ያለምንም ንግግር ከፈትኩት ሀኒምና ሰአዳ ከፊት ለፊቴ ይታዩኝ ጀመር። ነገሩ ህልም መስሎ ታየኝ፡ ከሀኒም የደስታ ስሜት ከራቀ ወራቶች እንደተቆጠሩ ከፊቷ ማወቅ ይቻላል።

ልቤ በነገሩ ቢደነግጥና ምንም ፍራቻ ውስጥ ቢገባም፡ ምላሴ ደፈር ብሎ። ኮስተር ብዬ። ምን ልትሰሪ መጣሽ አልኩ በአንደኛው እጄ በሩን ገርበብ አድርጌ እንደያስኩ፡

ሀኒም በንግግሬ ግር ተሰኝታ ከቀኝ በኩል አብራት የቆመችውን ሰአዳን አየት አድርጋ መልሳ የእኔን አይኖች ተመልክታ፡፡ ወዲያው ምንም አይነት ምላሽ ከአፏ ትንፍሽ ሳታደርግ አንገቷን ወደመሬት አጎንብሳ እንባዎቿን ዱብ ዱብ ታደርግ ጀመር፡ የሚወዱት ሰው ሲያለቅስ ማየት ምን ያህል ህመም እንዳለሁ እየተረዳው ነው።

ለሚወርዱት እንባዎቿ እያዘንኩ።

አታልቅሺ፡ ይሄ እኔ የሰራሁት ድራማ እንጂ ፍቅር አይደለምም አልነበረምም፡ ልክ እንደዚህ ነው ፋሪስ የተባለው ወንድምሽ ናዲያን ያስለቀሳት። አሁን ከሱ ተደብቀሽ አልቅሺ ምክንያቱም ናዲያ የትኛውም ቤተሰቧ ምን እንደተፈጠረ ሳያውቅ እሷ ከጀርባ እንዲህ ታነባ ነበር።

ምላሴ የጨከንኩ አስመስሎ ቢያወራም ልቤ ግን በጣም እያዘነና እየፈራ ነው።
ከንግግሬ አንፃር አትኩሮት ሰቶ ለሚመለከትም ሆነ ለሚሰማ ሌላ ሰው ምን ብትበድለው ነው የሚል ጥያቄ ሳያስነሳበት የሚቀር አይመስለኝም።

ስለፋሪስና ናዲያ ስለተባለችው እህቴ ምንም የሰማችው ነገር የለም መሰለኝ ነገሩ ጥያቄ ፈጥሮባት በድጋሚ አጎንብሳ ከምታነባበት ቀና ብላ እኔን እና ሰአዳን ተመለከተች። ግን ማናት ናዲያ? ስትል አልጠየቀችም።
በንግግሬ ላይ አሁንም ለመጠንከር እየሞከርኩ ነው ምንም አይነት የሀዘኔታ ምልክት ከፊቴ ላይ አይነበብም አክቲንጉን በብቃት እየተወጣሁት እንዳለሁ እራሴ ለእራሴ ምስክር መሆኑ በቂ ነው።

ለማንኛውም ሰአዳ አልኩ በተራ ደግሞ ሰአዳን ለማናገር በማሰብ የት ጠፍተሽ ነው ዛሬ የተገኘሽው ያውም እህቴን አደጋውስጥ ከቶ ከነጠቀኝ ያ ፋሪስ ተብዬ እህት ጋር። መቼም እቤታችንን እንዴት አወቅሽው ብዬ አልጠይቅሽም። ግን ጎበዝ ነሽ አንዴ ነው የመጣሽው ይመስለኛል እሱም ናዲ የሞተች ጊዜ፡ ቤት አትረሺም ማለት ነው አልኩ። እንደማላገጥ እየሰራኝ።
ጉብዝናዬን አውቃለሁ ስትል የመጀመሪያውን ቃል ሰአዳ ተነፈሰች ንገግሯ ዛቻ የተሞላበት ነበር፡ በምሰራው ስራም የተቆጣች ይመስላል።
እማዬ ሳትመጣ ነገሩን በዚሁ መቋጨት እንዳለብኝ ታወቀኝ።

እሺ ጓደኛሞች ሆናችኀል ጥሩ አደረጋችሁ እና ለምን ፈለጋችሀኝ?
የምናወራህ ጉዳይ አለ። ሰአዳ ነበረች።

ሀኒም አንደበቷ ተቆልፏል፡ ከማልቀስ ውጭ ምንም አትናገር አትጋገር።
ለሰአዳ አዲሱን ስልኬን፡ ቁጥሩን ልሰጣት፡ ስልኬን ያዢ በስልክ እናወራለን አልኩ። ስልክህ አለኝ፡ አላለችኝም አዲስ ቁጥር እንዳወጣሁ የሰማች በሚመስል መልኩ ስልኳን ክንዷ ላይ ካንጠለጠለችው ቦርሳ አውጥታ አዲሱን ስልክ ቁጥር ከተቀበለችኝ በኋላ በአካል እንጂ በስልክ የምናወራው ጉዳይ አይደለም አለች።በንግግሯ ደረቷን ነፋ አድርጋ።

ከሰአዳ ጋር መቀያየም ስለማልፈልግ አካባቢው ላይ ያለ ካፌ ውስጥ እንዲጠብቁኝ ነግሬያቸው ልብስ ለመቀየር ወደ ቤት ውስጥ ገባሁ።

ወደ ተባባልንበት ካፌ እንደደረስኩ ከአንድ ጠረጴዛ ዳር ላይ ሀኒምና ሰአዳ ተቀምጠው አየኋቸው አጠገባቸው እንደደረስኩ ትርፋን ወንበር ከጠረጴዛው ስር ስቤ ከተቀመጥኩ በኋላ አይኔን ወደ ሰአዳ ወርውሬ እ ምንድን ነው ጉዳዩ አልኳት። ሰአዳ ንግግሯን ጀመረች

አብዲ አንተ ጥሩ ሰው ነህ ናዲያም የምትነግረኝ የነበረው ስለመልካም በሀሪነትህ ነበር፡ ካወኩህ ጊዜ ጀምሮ እኔም በሀሪህን ወድጄው ነበር፡ ሀኒምን እንደምትወዳት አውቃለሁ አብዲ ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው ፋሪስን ለመበቀል ከሆነ በጣም ተሳስተሃል።
እንዴት?
ምን እንዴት አለው። ሀኒምን መጠቀሚያ አደረካት፡ ያው እኮ ነው "አልሸሹም ዞር አሉ" ለሴት እህትህ ብለህ እንዴት በሌላ ሴት እህትህ ላይ እንደዚህ ታደርጋለህ እኔም ሀኒምም እዚህ ምድር ላይ ያሉ ሴቶች በጠቅላላ እህቶችህ ነን፡ ከመሀከላቸው እናት ሚስት ምናምን ይወጣል ፡እኔ አብዲ እየሆነ ያለውን ነገር አምኖ ለመቀበል ይከብደኛል። ኮስተር እንደማለት እያልኩ
ሰአዳ ወዴት እየሄድሽ ነው ፋሪስ ምን አለሽ አንቺም ነገሩ ላይ እጅሽ አለበት እንዴ?
ሰአዳ ፊቷ ቀልቶ አፍንጫዋ በንዴት ሲነፋፋ ታየኝ
አቁም። ብላ በመጮህ የካፌውን ጠረጼዛ በመዳፏ መታች።
ይቺ ምስኪን ስለተፈጠረው ነገር የምታውቀው ነገር የለም እኔም እሷን ያወኳት በአንተ ስልክ ቴክስት ሳደርግ መልሳልኝ ነበር፡ እንደምታገባትና እንደምትወዳት አየነገርካት ስለነበር ስለ እኔ ማንነት ለማጣራት ስትል የዛኑ ቀን ስልኬን ወስዳ በራሷ ስልክ ታወራኝ ጀመር።

"ሀኒምን ቤቴ ያስገባኋት ቀን ሻይ እስኪፈላ ኪችን ውስጥ ቆይቼ ስወጣ ከእጇ ላይ ደንገጥ ብላ ስልኬን ያስቀመጠችበት ጊዜ ታወሰኝ"።

እኔ የእህትህ ጓደኛ እንደነበርኩ አስረዳኋት። በቴሌግራም ስለነበር ስታወራኝ የነበረው የወንድሟን ፎቶ ፕሮፋይል ላይ ለጥፋ አየሁ፡እኔም ለሷ ስትል ፋሪስን እያወከው ዝም ያልከኝ መስሎኝ፡ ስልክህን ወዲያው ውሎ ሳያድር ብሎክ አደረኩት ፡ግን እንደዛም ሆኖ ከሷ ጋር እያወራን ቀጠልን እሷ ከአንተ ጋር ማውራት እንዳቆምን አታውቅም ነበር ፡ሰፈሯን በጫዎታችን መሃል ስጠይቅ ያንተ ቤት አካባቢ እንደምትሰራና ሰፈሯም ከዛ ጥቂት እራቅ እንደሚል ነገረችኝ። እሷ ባታውቅም ነገሩ በደንብ ግልፅ እንዲሆንልኝ በማሰብ እኔ ገዢ መስዬ ቦታው ላይ መጣሁ ሀኒምን በአካል አየኋት እራሷ ናት ከዚ በፊት አንተ መኪና ውስጥ ሆኜ ያየኋት ልጅ።ስለዚህ አንተን መራቁን ምርጫዬ አደረኩ።
መግባባታችን ሲቀጥል፡ ሀኒም ሲጨንቃት ስለተፈጠረው ነገር ለኔ አወራችኝ አብዲ እንደዚህ አያደርግም ብዬ፡ ቤት ብትቀይርም እዚ ይዣት መጣሁኝ እና ልልህ የፈለኩት እየወሰድክ ያለው እርምጃ አግባብነት የሌለው ነው፣ጊዜው ሳይረፍድ ቆም ብለህ ብታስብ መልካም ይመስለኛል?።

ይህን ካለች በኋላ ለሀኒም ወንድሟ በእህቴ ላይ የፈፀመውን በደል ከ ሀ እስከ ፐ ዘርዝራ አስረዳቻት ሀኒም ነገሩን ለማመን ቢከብዳትም፡ በወንድሟ ላይ ከንፈሯን ነከሰች።

ብዙ ከሰማሁ በኋላ።
በሉ በቃ ከዚህ በላይ መቆየት ያለብኝ አይመስለኝም፡ ብዬ ከመቀመጫው ተነሳሁ ሀኒም በመማፀን እጄን ያዘችኝ የያዙኝን እጆች አመናጭቄ አስለቀኩና ሄድኩ፡
ሰአዳ ተከትላኝ መታ እጄን ይዛ ካስቆመችኝ በኋላ፡

አብዲ ልጅቷን ካለችበት ችግር እናውጣ ወንድሟ በስራ ምክንያት ከ አዲስ አበባ ከራቀ ቆይቷል እመነኝ እንደመጣ ይዘነው ማስረጃ አሰባስበን እንከሰዋለን፡ ይታሰራል አዎ እንደውም ይታሰራል ግን ልጅቷ አታሳዝንም።

አንቺ አትፍረጂ መፍረድ የሚችለው የተበዳዩ መበደል በደንብ የተረዳ ሰው ብቻ ነው። ስል መንገዴን ቀጠልኩ።

ጥቂት እራቅ እንዳልኩ የነ ሰአዳ መሄጃ ላይ ተደብቄ እመለከታቸው ጀመር። ሀኒም ታለቅሳለች ሰአዳ አባብላት ፊትለፊታቸው ወደቆመው ታክሲ ተያይዘው ገቡ። ሀኒም ግን ምንም የማይጨከንባት ፍጡር ናት፡ ስለማፈቅራት ይሆን ሰው በመኋና አሳዝናኝ ይሁን ነገሩን ባላውቅም በምሰራው ስራ እራሴን ጠላሁት።