Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi) | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi)

ከዳኒ ጋር የፍቅር ቃላትን በቴክስት እንቀባበላለን አመቺ ቦታ ላይም ስሆን ደውዬ ለት አወራዋለሁ እንደሚወደኝ ደጋግሞ ይገልፅልኛል እኔም እንደዛው ነኝ ምን እንዳስነካኝ ሊገባኝ ግን አልቻለም
ሁለተኛው ሴሚስተር.....

PART ❶❼

ከዳኒ ጋር የፍቅር ቃላትን በቴክስት እንቀባበላለን አመቺ ቦታ ላይም ስሆን ደውዬ ለት አወራዋለሁ እንደሚወደኝ ደጋግሞ ይገልፅልኛል እኔም እንደዛው ነኝ ምን እንዳስነካኝ ሊገባኝ ግን አልቻለም

ሁለተኛው ሴሚስተር ላይ ነን ትምሀርት ከጀመርን፣ ያውም በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች አልፈዋል፡ ሁሉም ነገር በዛውም ልክ አልፎአል ለቀጣይ ውጤቴን ወደ በፊቱ ቦታ ለመመለስ በደንብ አቅጃለሁ ለቀሪው ተማሪ የውጤት መግለጫ ወረቀት ተሰጥቷል ብዙም አልተጎዳሁም አስራ አንደኛ ቤት ውስጥ ነው ያለሁት ሃያት ከ ሰላሳ አምስት ተማሪ ሰላሳኛ ነው የወጣችው ግን ምንም ነገር አላስገረማትም ይሄ ነገሯ አስገርሞኛል ምክንያቱም እንዴት ቅር አልተሰኘችም እንደኔ ብዬ ነው

የገባው መምህር ጊዜውን ጠብቆ እንደወጣ ሰማሽ ሀሉዬ ቀጣይ ሳምንት ከለር ደይ እናከብራለን አለች እና ስል ጠየኳት አትመጪም አለችኝ ሀዩ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም እንደማይመቸኝ ስንቴ ነገርኩሽ አልኳት እሷም የዋዛ አይደለችም ደካማ ጎኔን ተጠቅማ ዳኒም እኮ አለ አለች እየተቅለሰለሰች፡ ትንሽ ዝም ከተሰኘሁ ቡሃላ

እሺ እመጣለሁ አልኳት ግን ሀዩ እቤት እንደዛ ሆኜ ብገባ አክስቴ ታብድብኛለች ስል ዋነኛው ስጋቴን ነገርኳት እሺ እንደዚህ ብናደርግስ ስትል የመጣላትን ሀሳብ አጋራችኝ እኔ ተቀያሪ ልብስ ለራሴም ላንቺም ላምጣ፡ ከዛስ፡ ከዛማ በቃ እሱን ለብሰሽ ከኛ ጋር ፈታ ትያለሽ ዳኒም እኮ ከኛ ጋር ነው ከኛ ክፍል ተማሪዎች ውጪ ሌሎችም ይሳተፋሉ አብረሽን ብትሆኚ ደስ ስለሚለኝ ነው እኮ ሀሉ ከደበረሽ ይቅር አለች፡ እስኪ ላስብበትና እናወራለን ስል ገለፅኩላት

ዛሬ ከለር ደይ ይከበርበታል የተባለበት ቀን ነው ዳኒ እናዳልቀር አሳስቦኛል እኔም በሀያት ሀሳብ ተስማምቻለሁ

ከ አባቴ ጋር ትንሽ እረፈድ አድርጌ ከቤት ወጣሁ ግማሽ መንገድ አብሬው ከሄድኩ ቡሃላ ታክሲ አሲዤው ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩኝ ክፍል ተገብቶ ነበር የደረስኩት፡ ወደ ውስጥ እንደገባሁ ሃያትን ከቦታችን ላይ ላያት አልቻልኩም የት ሄዳ ነው እኔን እንዳትቀሪ ብላኝ መቼም ቀርታ አይሆንም እያልኩ ከራሴ ጋር መነጋገር ጀመረኩ ጥቂት እንደቆየ ሀያት የክፍሉን በር አንኳክታ ወደ ውስጥ ገባች በእጇ ጠቆር ያለ ፌስታል ይዛለች በግምት አመጣለው ያለችው ልብስ ይመስለኛል አጠገቤ እንደተቀመጠች ወደ ፌስታሉ ተመለከትኩ ግምቴ ትክክል ስለነበር የሀያትን ፊት አይቼ ፈገግ አልኩኝ

የከሰአቱን ክፍለ ጊዜ ክፍል አልገባንም ከዚህ በፊት ዳኒ ይዞኝ ወደ ሄደው ደስ የሚለው ያ ነፋሻማ መዝናኛ ውስጥ ነበርን ደስ የሚል ኘሮግራም ነበር ብዙ ተማሪዎች ተሳትፈዋል እኔም ሀያት ያመጣችልኝን እጁ ትልትል ተደርጎ ለማሳመር በተሞከረው ነጭ ቲሸርትና ከስር ጥቁር ከለር ባለው አጠር ብሎ ጠበብ ባለው ቀሚስ ፏ ብያለሁ ሁሉም ፊቱ በተለያዩ ቀለማት ከነ ልብሱ ተጨመላልቋል ሰአት እየሄደ ነው አየሩ ብርዳማ ነው ሰማዩ በደመናው ጨለምለም ብሏል በቃ ዳኒ እኔ ልሂድ አልኩት የአክስቴን ነገር ስለሚያውቅ እሺ በቃ እኛ ጋር ሄደሽ ሻወር ውሰጂና ልብስ ቀያይረሽ ወደ ቤት እሸኝሻለሁ አለኝ እሺ አልኩት ምክንያቱም እቤት እንደዚህ ሆኜ መግባት ስለማልችል ሀያት ከቀሪ ተማሪዎች ጋር ፎቶ ቤት ሄደው ፎቶ ተነስተው ወደየ ቤታቸው እንደሚበታተኑ ነገረችኝ ያን ለማድረግ ሰአት እንደሌለኝና ከዳኒ ጋር ያሰብነውን ነገርኳት እሺ የኔ ውድ በቃ ጥሩ የኔን ልብስ እዛው ዳኒ ጋር አስቀምጪልኝ እኔ እራሴ እወስዳለሁ ብላኝ ጉንጬን ስማኝ ተለያየን

እንደዚህ እብድ መስለን ከ ዳኒ ጋር ታክሲ ይዘን ወደ እነሱ ቤት አመራን እየተቀላለድን የፎቁን ደረጃ ወጣን ከቤቱ ውስጥ እንደገባን ቦርሳዬን ተቀብሎኝ በቃ በዚህ ብርድ ቻይው አለኝ ወደ ሻወር ቤቱ እጁን ዘርግቶ ቶሎ በይ ደግሞ መክሰስ በልተን ዝናብ ሳይጥል እንድሸኝሽ ብሎ ቦርሳዬን ከ ሶፋው ላይ አሰቀመጠው

የሻወር ቤቱ ውስጥ ገብቼ እንዳለሁ ዳ....

PART ❶❽ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi