Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) አ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

አትቀልጂ አለኝ በፍቅር አይን እያየሁት ድምፄን ቀንሼ እየቀለድኩ አይደለም አልኩት እዛው መሬቱ ላይ እንደተኛው አንገቱን ዝቅ አድርጎ ወደ ከንፈሬ ተጠጋ አይኖቼን ጨፈንኳቸው በስሱ ከን........

Part ❶➏

አትቀልጂ አለኝ በፍቅር አይን እያየሁት ድምፄን ቀንሼ እየቀለድኩ አይደለም አልኩት እዛው መሬቱ ላይ እንደተኛው አንገቱን ዝቅ አድርጎ ወደ ከንፈሬ ተጠጋ አይኖቼን ጨፈንኳቸው በስሱ ከንፈሬን ሳመኝ ሌላ የማላውቀው አለም ሄጃለሁ በዚህ መሀል ስልኬ ጠራ ሁለታችንም ወደራሳችን ተመለስን ወዲያው ዳኒ ከላዬ ላይ ተነሳ ስልኩ ጠርቶ ሳይጨርስ ለማንሳት ተጣደፍኩ ስመለከት ሀያት ናት አላነሳሁትም አሁንም ደግማ መደወል ጀመረች ከቤቱ እየወጣሁ ስልኩን አነሳሁት እናንተ የት ሄዳችሁ ስትል ጠየቀችኝ የትም መጣን ስል መለስኩላት

ከነ ዳኒ ቤት ወተን ወደትምህርት ቤት መሄድ ጀምረናል ከ ዳኒ ጋር ከቤት ከወጣን ጀምሮ ምንም ንግግር በመሃላችን አልተፈጠረም ለምን እንደሆነ አላውቅም ምናልባት ተፋፍረንም ሊሆን ይችላል

እ.. እሮጥ እሮጥ አለ የጊቢው በር ላይ የቆመው ጥበቃ ሰአቱ ትንሽ እረፈድ ብሏል ዱብ ዱብ እያልን ወደ ውስጥ ገባን ዳኒ ቻው በቃ ብሎ ሲሮጥ ወደ ክፍሉ ሄደ ባለፈው የያዘን ዳይሬክተር ጊቢ ውስጥ እየተንጎራደደ ስለተመለከተው እንጂ ሰላም ሳይለኝ እንደዚህ ሲርጥ አይሄድም ነበር እኔም ቀልጠፍ ብዬ ወደ ክፍል አመራው ወደ ውስጥ ለመግባት በሩ ላይ ቆሜ ውስጥ ካለው መምህር ለመግባት ፍቃድ ጠይቄ ወደ ውስጥ ገባው ቦታዬ ላይ እንዳረፍኩኝ ሀያት ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብላ የት ሄዳችሁ ነው ስትል ጠየቀችኝ የትም እዚሁ ነበርን ከጊቢ ውጪ ነበርን አልኳት ምሳ በላሽ እሺ ስትል ሌላ ጥያቄ አነሳች አንገቴን በመነቅነቅ አዎ አልኳት ፈገግ ብላ ጠቀሰችኝ ፈገግ ብዬ ላት ትኩረቴን ወደ ሚሰጠው ትምህርት አደረኩ።

ዛሬስ ከትንሿ ሀናን ዘግየት ብዬ ነው ከኡስታዝ ጋር የተገናኘሁት ሀናን በጣፋጭ አንደበቷ ቁርአን አንብባ ጨረሰች ተራው የኔ ነው አርፍጄ መምጣቴ ሳያንስ ከቀልቤ አለመሆኔ ያስገርማል እ.. ሀሊማ ጀምሪያ አሉ ምኑን አልኳቸው ፊታቸውን ኮስተር አድርገው ቁርአኑን ነዋ አንቺው ቀልብሽን ምን ሰለበው አሉኝ ትንሽ ፈገግ ብዬ ላቸው በውጤቴ ዙሪያ የተፈጠረውን ነገር ከባድ ጭንቀት እንደሆነብኝ ነገርኳቸው አብሽር ይሄማ እኮ ይስተካከላል ለዚህ ነው ጭንቀትሽ አብሽር እንዴ አንዳንዴ ነገሮች እንደዚህ ነው በሰብር በዱአ መጠንከር ነው ከኛ የሚጠበቀው ሲሉ እንደ አባትም እንደ ኡስታዝም ሆነው መከሩኝ የነበርኩበትን ሱራ አንብቤላቸሁ ተለያየን።

ሁሌም እንደማደርገው አባቴ ወደ ክፍሉ ሲሄድ ተከትዬው ወጣሁ ከበረንዳው ላይ ስደርስ ባባ ብዬ በመራመድ ላይ የነበሩ እግሮቹን አስቆምኳቸው ስለውጤቴ የተፈጠረውን እንባዬን እያፈሰስኩ ነገርኩት እሱም እንደ አባትነቱ ተረዳኝ አቅፎ አንባዬን እየጠራረገልኝ ያጋጥማል እኮ የኔ ልጅ ደግሞ ምነው ችግር አለ እንዴ ሲል ጠየቀኝ ከ ዳኒ ጋር የጀመርኩትን ጉድ ደብቄ ወደ ላይ ቀና ብዬ አይን አይኑን እያየሁት የለም አባ የራሴ ክፍተት ነው አልኩት በቃ በቀጣይ አሪፍ ውጤት አምጥተሽ ታስደስቺኛለሽ ደግሞ አልተከፋውብሽም ብሎ ግንባሬን ሳመኝና በቃ የምን ማኩረፍ ፈገግ በይ አለኝ ፈገግ ብዬለት እሺ ለአክስቴ ንገርልኝ አልኩት እንዴ ንገሪያት ምን አስፈራሽ ብትቆጣሽ ነው ብሎ አሳቀኝ ሳቄን ከጨረስኩ ቡሃላ እረ ባባ ንገርልኝ ትቆጣኛለች አልኩት በተፈጠረው ነገር እንዳልከፋበት በሚመስል መልኩ እየሳቀ እሺ ነግርልሻለሁ አለኝ ከመለያየታችን በፊት ግን አባ ተሽሎሀላ አልኩት አዎ ዛሬ ያው ስራም ወጣሁ አይደል አለኝ እሱማ አዎ በቃ ሁሌም ደህና ሁንልኝ ስል ተሰናብቼው ወደ ክፍሌ ተመለስኩኝ

የአንደኛው መንፈቅ አመት አጋማሽ ትምህርት ተዘግቷል ያመጣሁትን ወጤት አክሴ ሰምታለች ትንሽ ቶቆጥታኝ ብዙ ምክር ለግሳኛለች ከሀዩ ጋር አልፎ አልፎ እንደዋወላለን ከዳኒ ጋር የፍቅር ቃላትን በቴክስት እንቀባበላለን አመቺ ቦታ ላይም ስሆን ደውዬ ለት አወራዋለሁ እንደሚወደኝ ደጋግሞ ይገልፅልኛል እኔም እንደዛው ነኝ ምን እንዳስነካኝ ሊገባኝ ግን አልቻለም

ሁለተኛው ሴሚስተር.....


PART ❶❼ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi