Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi) | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi)

ሀሉዬ አይዞሽ አለ እንደበርበሬ የቀሉትን አይኖቼን እየተመለከተ ተነሽ ብሎ እጁን ዘረጋልኝ ከክፍል ባልወጣ ደስ ይለኝ ነበር ግን ያው በሱ ላይ ልቤ አልጨክን ብሏል....

PART ❶➎

ሀሉዬ አይዞሽ አለ እንደበርበሬ የቀሉትን አይኖቼን እየተመለከተ ተነሽ ብሎ እጁን ዘረጋልኝ ከክፍል ባልወጣ ደስ ይለኝ ነበር ግን ያው በሱ ላይ ልቤ አልጨክን ብሏል እጁን ይዤ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ አብሬው ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ በእረፍተ ሰአት ላይ የኔን ውጤት ለማወቅና እነደ አምናው አብረን ደስታችንን ልንከፋፈል አስበው መተው አፅናንተው የተመለሱት ኢልሃምና ሲትራ ወደ እኔ ሲመጡ ከደረጃው ላይ ተገጣጠምን አመጣጣቸው አምና በአንድ ላይ ስንበላ የነበረውን ምሳ ዛሬ ለትውስታ እንድንደግመው የፈለጉ ይመስለኛል ሁለቱም በእጃቸው የምሳ እቃቸውን ይዘዋል እግረ መንገዳቸውንም በተፈጠረው ነገር አፅናንተወኝም ሊመለሱ ይመስለኛል፡

እንዳዩኝ ከዳኒ ጋር የተጀመረው ነገር ያ ወዛገባቸው ይመስለኛል ሀሊማ አለችና ቀደም ብላ ጉንጬን ሳም ሳም አደረገችው ሲትራ ቀደም ብሎ ዳኒ ትቶኝ ወደታች ወርዶ እኔን መጠበቅ ጀመረ ኢልሃምም እንደ ሲትራ ጉንጮቼን ስማ ወዴት ነው ስትል ጠየቀችኝ ከነጋ ያልተ
ታየው ፈገግታዬን እያሳየውሃት እኔንጃ ወዴት እየወሰደኝ እንደሆነ አልኳቸው ምን እየሰራሁ እንደሆነ እንደኔው ግራ የገባቸው ይመስለኛል ሲትራ እሺ ቶሎ ትመለሻለሽ አለችኝ እኔንጃ ቆይ እስኪ ብዬ ዳኒን ጠርቼ ጠየኩት አዎ እንመለሳለን አለ በቃ እስክትመጪ እንጠብቅሻለን አብረን ምሳ እንድንበላ ነው የመጣነው አሉኝ ወይኔ በአላህ ውዶቼ እኔ ዛሬ መብላት አላሳኘኝም በቃ እናንተ ብሉ ምናልባት ልቆይባችሁም እችል ይሆናል ብያቸው ሀሳቤን ተቀብለውኝ አብሬያቸው ከደረጃው መውረድ ጀመርን

ዳኒ ወዴት ነው የምንሄደው አልኩት የትምህርት ቤቱ የጊቢው በር ጋር ስንደርስ ከፍቶሻል ደብሮሻል ምሳ አልበላሽም ይሄን ሁሉ እያየሁ እንዴት ዝም እላሻለሁ ፈታ ብለን አሪፍ ምሳ ጋብዤሽ እንመለሳለን አለ ደስ ብሎኛል በሃሳቡ ተስማምቻለሁ ጊቢውን ለቀን ወጣን፡

ከትምህርት ቤቱ ትንሽ እራቅ ካልን ቡሃላ፡ መጨረሻው ነው አለ እረዳቱ ዳኒ የት ነው ይዘኸኝ የመጣከው አልኩት የታክሲውን ሂሳብ ከፍሎ ወደ እኔ እንደተጠጋ እንዴ ከቤት ወተሽ ስለማታቂ ላስጎበኝሽ እኮ ነው ብሎ ትንሽ ቀለደብኝ እየሳኩለት እጄን ወደ ክንዱ ወስጥ አስገብቼ መጎዝ ጀመርኩ ሰማዩ ጠዋት እንደታየው የኔ ፊት ጠቆርቆር ብሏል ንፋሱም በመጠኑ ይነፍሳል ዝናብ ሊጥል መሆኑን በደንብ ያስታውቃል ዳኒ ዝናብ መጣ ብዬ ንግግሬን ሳልጀምር ማካፋት ጀመረ ነይ ደርሰናል በደንብ ሳይዘንብ ዱብ ዱብ እንበል አለኝ እሺ እሩቅ ነው እንዴ አልኩት አይ ደርሰናል አለ ሀሊማዬ ሲል ጠራኝና እኔኮ አፈቅርሻለሁ አለኝ ከሶምሶማ በማያንስ እሩጫ ከጎኔ ሆኖ እየተከተለኝ እኔም ዝምታን መርጬ ከጎኑ ሆኜ እየተጓዝኩኝ ነው

ከጥቂት ደቂቃዎች ቡሃላ በዛ ያሉ ኮንዶሚኔዬሞችን በውስጡ ከያዘ ውብ ጊቢ ደረስን ሀሳባችን ከዝናቡ ለማምለጥ ስለነበር ቀጥታ ወደ ጊቢው ገብተን ወደ አንዱ ብሎክ በፍጥነት ተከታትለን አመራን በፍጥነት እየተነፈስኩ የት ነው ግን ይዘከኝ የመጣኸው ስል ጠየኩት ከፎቁ ውስጥ እንደገባን ፡እቤት አለኝ ማለት አልኩት እኛ ጋር እቤት ነዋ አለኝ ከኮሪደሩ ላይ እንዳለን ጠቋሚ ጣቱን ቀስሮ የሀያት ቤት ያኛው ብሎክ ላይ ነው ሲል አሳየኝ ዞሬ ከተመለከትኩ ቡሃላ እሺ የኛ እዚህ መምጣት ለምን አስፈለገ ስል ጠየኩት ምነው ቅር አለሽ እኔ አሪፍ ምሳ በልተን ትንሽ ፈታ ብለን እንሄዳለን ብዬ ነው ቅር ከተሰኘሽ እንመለስ አለኝ አይ አላለኝም ና እሺ እስኪ ምሳህን ልቅመሰው አልኩት እሺ ስላልኩት ደስ ያለው ይመስለኛል

ከእቤቱ እንደገባን ቆንጆ ምሳ እራሱ ሰርቶ ሊያበላኝ መንጎዳጎድ ጀምሯል እኔ ከሶፉው ላይ ቁጭ ብዬ የከፈተውን ቴሌቭዥን እመለከታለሁ ዝናቡ በሀይል እየጣለ መሆኑን ከውጪ የሚሰማው ድምፅ በጣም ያስታውቃል

ቆንጆ ምሳ ሰርቶ አቀረበ እጄን ታጥቤ ከጎኑ ተቀመጥኩና አስተያየት የምሰጥህ በልቼ ስጨርስ ነው አልኩት እየሳቀ ችግር የለውም አለኝ እኔ ምልህ ቤተሰቦችህስ ስል ጠየኩት የምኖረው ከታላቅ እህቴ ጋር ነው ማታ ነው ከስራ የምትገባው ሌላ ቤተሰብስ ማለቴ እናትና አባትህ አልኩት በእጄ የያስኩትን እየጎረስኩ እነዛው ከቴሌቭዥኑ ጎን ወደተደረደሩት ፎቶዎች እጁን ቀስሮ ቆይ በልተን ስንጨርስ አያቸዋለሁ አልኩት እሺ ችግር የለውም እንዴ ደግሞ በደንብ ብይ እንጂ አይጣፍጥም እንዴ አለ እረ በጣም ቆንጆ ነው ጎበዝ ነህ ሳላደንቅህ አላልፍም አልኩት አመሰግናለሁ ለማንኛውም ብይ ብሎ በትልቁ አንስቶ ሊያጎርሰኝ እጁን ወደ አፌ ዘረጋ እ. እ. ስል ተግደረደርኩ እሱም ትንሽ ቀንሶ አጎራረሱን አስተካክሎ አጎረሰኝ እኔም አንድ አጎረስኩት እንዲህ እንዲህ እያልን የቀረበውን ምግብ ጥርግ አድርገን ጨረስን ላደረገልኝ ሁሉ ምስጋና አቀረብኩለት ለብርዱ ይሆነናል ብሎ አሪፍ ሻይም አፍልቶ አጠጣኝ

በመስኮቱ በኩል ወደ ውጭ ተመልክቶ በቃ ዝናብ አባርቷል ሰአት ሳይረፍድ ወደ ጊቢ እንሂድ አለኝ እሺ ብዬ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ እሱም ቴሌቭዥኑን አጥፍቶ ሻይ የጠጣንበትን ብርጭቆዎች ወደ ኪችኑ ይዞ ገባ በዚህ መሃል ቅድም በእጁ ወደ ጠቆመው ፎቶ ተጠግቼ ማየት ጀመርኩ ከውስጥ ተመልሶ ወጣና በሩን ዘግቶ ወደ እኔ መጣ እረስቼው ሳላሳይሽ ልንሄድ ነበራ ብሎ ከላይ የተሰቀለውን ፎቶ ከነ ፍሬሙ አውርዶ እነዚህ እናትና አባቴ ናቸው አሁን እዚህ የሉም በስራ ምክንያት ከሀገር ውጪ ናቸው ሲመጡ አስተዋውቅሻለሁ አለኝ ቀጣይ ፎቶውን አንስቶ ይቺ የመጀመሪያዋ እህቴ ናት አግብታ ከ አዲስ አበባ ውጪ ነው የምትኖረው ሁሉንም ፎቶ አብራርቶ እያሳየኝ የመጨረሻው ጋር ደረስን ይቺ ከኔ ጋር ያለችው ሁለተኛዋ እህቴ ነች አለኝ ቆንጆ እህት አለችህ አልኩት ፈገግ ብሎ ያነሳውን ፎቶ ወደ ቦታው ሊመልሰው ሲል በዚሁ ፎቶ ተከልሎ የነበረ አንድ ፎቶ አየው ቀደም ብዬ አነሳሁትና አይቼው ሳቄን ለቀኩት ዳኒ በልጅነትህ እንደዚህ ነበርክ ብዬ እያሳየሁት ሳኩ በእጁ የያዘውን ፎቶ አስቀምጦ ፈገግ አለ ይሄንንማ ለሀያት አሳያታለሁ አልኩ እንዴ ቀልድ አለ የያስኩትን ሊቀማኝ ወደ እኔ ተጠጋ እኔም ፎቶው እኔን እንዲህ ካሳቀ ሀያትን ስያታለሁ ፎቶውን እንዳይቀማኝ በሳቅ ውስጥ ሆኜ እየለመንኩት በጠረጴዛው መሽከርከር ጀመርኩ በዚህ መሃል ጠረጴዛውን ዘሎት ወደ እኔ ሲመጣ እግሩ እረዘም ያለው ቀሚሴ ላይ አረፈ ላመልጠው አልቻልኩም ይባስ ጠልፎኝ ወደኩ ዳኒም አልቀረለትም ከላዬ ላይ ተደረበ ፎቶው ከእጄ ወቶ ወደቀ ዳኒ ከላዬ ላይ ወድቋል ቅድም በሳቅ እንደዛ የቀወጥኩት ቤት ፀጥ አለ አንገቴ የዳኒ ጡንቻን ተንተርሷል ከላዬ ሆኖ አይን አይኔን ያየኛል ጥቂት ቆይቶ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ አፈቅርሻለሁ አለኝና ቀና አለ እኔም አፈቅርሃሉ ስል ህመሜን አወጣሁት ዳኒ ያመነኝ አልመስለኝም አሁንም ጠጋ ብሎ አትቀልጂ አለኝ በፍቅር አይን እያየሁት ድምፄን ቀንሼ እየቀለድኩ አይደለም አልኩት እዛው መሬቱ ላይ እንደተኛው አንገቱን ዝቅ አድርጎ ወደ ከንፈሬ ተጠጋ አይኖቼን ጨፈንኳቸው በስሱ ከን........


PART ❶➏ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi