Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi) | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi)

እ.. የምናገረው ከ አንድ እስከ አስር የወጡትን ብቻ ነው አሉ የክፍሉ ተማሪ በሙሉ ድምፅ የተስማማ ይመስላል ዝምታን መርጧል

እሺ ከታች እጀምራለሁ አስረኛ....

PART ❶➍

እሺ ከታች እጀምራለሁ አስረኛ ብለዉ መጥራት ጀምረዋል ስሙን ለጠሩት ተማሪ ያመጣውን ውጤት እንዲመለከት የያዙትን ሰትረፍኬት ቦታው ድረስ እየሄዱ የሰጣሉ በተማሪውና በመምህሩ መሃል የውጤት መግለጫው እርክክብ ሲፈፀም ተማሪውም ክፍሉን በጭብጨባ ያሞቀዋል በዚህ ሁኔታ አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ተማሪ ስም ላይ ደርሰዋል እስካሁን የኔ ስም አልተጠራም ምናልባት አምና ካመጣሁት የተሻለ ደረጃ በእቅዴ መሰረት አምጥቼ ደረጃዬ ከፍ ብሎም ሊሆን ይችላል፡

እሺ የመጨረሻው አንደኛ የወጣችው ወይንም የወጣው ተማሪ ተባለ እኔ እንደምሆን እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም ደረጃዬ ከ አንድ እስከ አምስት ነው እስከዛሬ ድረስ አጋጥሞኝ የሚያውቀው ከአምስተኛ አልፌም አላውቅም ስለዚህ ከአምና ተሻሽያለሁ ማለት ነው ዘንድሮ፡ የመጨረሻውን ስም መምህሩ ጠሩ በጣም ገርሞኛል እንዴት ይሄ ሊሆን ቻለ ከመቀመጫዬ ተነሳሁ መምህሩ አይናቸውን ወደ እኔ አዞሩ ሀያትን ያለምንም ንግግር ገፈታትሪያት ተነሳሁ የክፍሉን በር ከፍቼ ልወጣ ስል ሀሊማ ሲሉ ተጣሩ ምንም ምላሽ ሳልሰጣቸው ክፍሉን ለቅቄ ወጥቼ ወደ መውረጃው ሄድኩ በጣም ከፍቶኛል ውጤቴ ትክክል አይደለም የተሰራው እንዴት ከ አንድ እስከ አስር ውስጥ መካተት አቃተኝ እንዴ ይሄማ አይሆንም እያልኩኝ ከአይኔ እየተንቆረቆረ የሚወርደውን እንባ ለማስቆም በሰልፍ ወደ ተደረደረው ቧንቧ አምርቼ ፊቴን ታጠብኩኝና ወደ ክፍል መመለስ ጀመርኩ በጣም ከፍቶኛል ሆድ ብሶኛል መበለጤ አስቆጭቶኛል ያውም በአስር ተማሪ መምህሩን መረበሽ ስላልፈለኩኝ ሁሌ ከነ ሀያት ጋር ከምቀመጥበት ክፍላችን ፊት ለፊት ያለው ወንበር ላይ ተቀምጬ አንገቴን ደፍቼ ማንባቴን ቀጠልኩ ለቤተሰቤ ምን ብዬ እንደምናገርም ጭንቅ ብሎኛል

መምህሩ ያበቃው የሳቸውን ክፍለ ጊዜ ተከትለው ክፍሉን ለቀው ወጡ የተቀመጥኩት ክፍሉ ፊት ለፊት ስለነበር ቀጥታ ወደ እኔ መጡ ካቀረቀርኩበት ቀና እንድል ካደረጉኝ ቡሃላ ሀሊማ ችግር አለ እንዴ ሲሉ የውጤቴ እንደዚህ በአንዴ ማሽቆልቆል ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቁኝ ምላሽ ሳልሰጣው እየተሰቀሰኩ ማልቀሴን ቀጠልኩ አምናም አንድ ክፍል ውስጥ ስለነበርን የውጤቴ ነገር በጣም አስገርሞቸዋል በቃ ነይ ተነሽ በቀጣይ ታስተካክያለሽ ገና ብዙ ጊዜ አለሽ አሉ እንደ አባትም እንደመምህርም ቆጣ እያሉ፡ ምክራቸውን ተቀብዬ ተቀምጬ ሳለቅስበት ከተበረው ወንበር ተነሳሁ ወደ ክፍል ተመልሰው ወደ በሩ በመጠጋት አሁን የገባውን መምህር ይቅርታ ጠይቀው ሀያትን አስጠሯት፡ ክፍሉን ለቃ ወታ እኔ ጋር እንደደረሰች ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ሀሉ ምነው አለችኝ ዛሬ ማውራትም አልፈልግም በቃ አብራችሁ ሂዱ እና ፊትሽን ታጥበሽ ተመለሱ አሉ ቲቸር ሽመልስ እኛ ወደ ቧንቧው ጋር ሄድን እሳቸውም ሌላ ክላስ ስላለባቸው ወደዛው አቀኑ

እዛው ቧንቧው ጋር እንዳለሁ የተፈጠረውን ለሀያት አስረዳዋት እንዴ ለዚህ ነው ይሄ ሁሉ እንባ እንዴ ይስተካከላል እኮ ሀሊማዬ እያለች አቀፈችኝና ማባበል ጀመረች ደግሞ ምነው ችግር አለ እንዴ እንዴት በአንዴ ውጤትሽ እንደዚህ ሊወርድ ቻለ ግን እኮ ሀሉ በፊት እንደተዋወቅን ጥሩ ተሳትፎ ታደርጊ ነበር ከሆነ ጊዜ ቡሃላ ግን ቀዘቀሽ ችግር ካለ ንገሪኝ እስኪ አለች

አዎ ችግር አለ አልኳት ምን ስትል ጠየቀችኝ ዳኒ አልኳት ዳኒ ዳኒ ታዲያ እዚህ ጉዳይ ውስጥ ምን ያደርጋል ስትል ጠየቀችኝ ዳኒን አፍቅሬዋለሁ ስል ነገርኳት ብዙም የተገረመች አይመስልም እና አልነገርሽውም ስትል ጠየቀችኝ አዎ አልኳት ለምን ፈርተሽው አለችኝ አዎ ሀያት እሱ እንደሚያፈቅረኝ ደጋግሞ ይነግረኛል እኔ ደግሞ ህመም ሆኖብኛል ቢጎዳኝስ ሲቀጥል ካላገባኝ ምን ያደርግልኛል እሱ ደግሞ እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም ገና ተማሪዎች ነን እኔ ብዙ እቅዶች አሉኝ በዛ ላይ ደግሞ ሃይማኖታችን የተለያየ ነው ተረዳሽኝ ሀዩ አልኳት ፊቴን ታጥቤ ጨርሼ ወደ ክፍል እያመራን

የእረፍት ሰአት ነው ኢልሃምና ሲትራ ወደ ክፍላችን መተዋል ሁለቱም የአምና ተፎካካሪዎቼ ነበሩ አሁን ሁለቱም አሪፍ ደረጃ አስመዝግበዋል በኔ የተከሰተው ነገር ግር አሰኝቷቸዋልም

የምሳ ሰአት ላይ ዳኒ ከሀያት ጋር መጣ የተፈጠረውን ነገር የነገረችው ይመስለኛል ሀሉዬ አይዞሽ አለ እንደበርበሬ የቀሉትን አይኖቼን እየተመለከተ ተነሽ ብሎ እጁን ዘረጋልኝ ከክፍል ባልወጣ ደስ ይለኝ ነበር ግን ያው በሱ ላይ ልቤ አልጨክን ብሏል....


PART ❶➎ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi