Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi) | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi)

እላዬ ላይ ተቀምጣ ስትጫወት የነበረችውን ሀናንን ከላዬ ላይ አውርጃት ባባን ተከተልኩት.....

PART ❶➌

እላዬ ላይ ተቀምጣ ስትጫወት የነበረችውን ሀናንን ከላዬ ላይ አውርጃት ባባን ተከተልኩትና ወጣሁ በጭንቀት ላይ ሌላ ጭንቀት ሆኖል ነገሩ ከክፍሉ ካደረስኩት ቡሃላ የቤቱ በረንዳ ላይ የቆመውን አባቴን ህመሙ ካገረሸበት በፍጥነት ወደ ሆስፒታል እንዲሄድና እንዲታከም አሳሰብኩትና እንደለመደው ግንባሬን እንዲስመኝ ወደ ከንፈሮቹ ተጠጋሁ።

ዛሬ ቅዳሜ ነው የእረፍት ቀኔን ልብስ በማጠብ ጀምሬአለሁ ጆሮዬ ላይ የሰካሁት ኤርፎን በድብቅ የከፈትኩትን ዘፈን ለማዳመጥ እንደ መፍትሔ እየተጠቀምኩበት ነው ዳኒ ጋር ነው ልቤ ያለው ልቤን ሙሉ ለሙሉ እንዴት ሊወስደው እንደቻለ ባላውቅም በመሀል የማሸውን ልብስ እያቆምኩ ቀልቤን ወደ ዳኒ ጋር እሰደዋለሁ ልቤ" እሱጋር ነው ከመጠቢያው ማሽን ውስጥ የከተትኳቸው ወፋፍራም ልብሶችን እስኪያሽልኝ ብዬ ሰፋ ብሎ በቀይ ቀለምና በጥቃቅን የአበባ ምስሎች ዙሪያው ባጌጠው መዘፍዘፊያ ውስጥ ያደረኳቸውን ልብሶች በማሸት በሀሳብ ተጉዣለሁ ከውሃላዬ መቶ ትከሻዬን ባባ ነካ ነካ እስኪያደረገኝ ድረስ፡

ሳለስብው ስለነበር ከወሃላዬ የመጣው ትንሽ የመደንገጥ ስሜት ታይቶብኛል ጆሮዬ ላይ የሰካዋቸውን ኤርፎኖች ከንግግሬ በፊት ቀደም ብዬ ነቀል ነቀል ካደረኳቸው ቡሃላ ፈገግ ስል ባባ እኔኮ ትተኛለህ ብዬ ነው ያልመጣሁብህ እንዴት ነህ ተሻለህ ስል ጠየኩት እጆቼ ላይ ያለውን አረፋ ከመሬት ላይ ባነሳሁት የዩኒፎርም ሹራብ እየጠራረኩ ፡ አልሃምዱሊላህ አሁን ምንም አልልም አለ ከእግሩ አንስቼ የለበሰውን ከተመለከትኩ ቡሀላ አሁን ወዴት ልትሄድ ነው ታዲያ ስል ጠየኩት ምላሽ ሳይሰጠኝ እኔ የምለው.. ስትል ንግግሯን ጀምራ ወደ እኛ ለመጣችው አክስቴ ሙሉ ነገሩን ሰጣት እ እንሂድ አይደል አለችው ከፀጉሩ ላይ ያየችውን ነገር በጣቶቿ እያነሳች.. አዎ እንሂድ አለ

የት እንደሆነ ለመጠየቅ ፈልጌያለሁ አክስቴ ወዴት ነው አልኳት ደላላው ጋር ደርሰን እንመጣለን ሰራተኛ ካገኘን እስኪ እንሞክር እስክመጣ ካልጨረሽ አግዝሻለሁ ደግሞም እህትሽን እያየሻት አሁን ያ የፈረደበት ቴሌቭዥን ላይ ተሰክታለች ስትል የሀናን ሁኔታ ገልፃልኝ ከአባቴ ጋር ተያይዘው ወጡ፡

የእግራቸውን እቤቱን ለቆ መውጣት ተከትዬ የማጥበውን ልብስ ትቼ ወደ ሳሎኑ በረንዳ ላይ በመሄድ ተቀምጬ ስልኬን አውጥቼ ወደ ዳኒ ጋር ደወልኩኝ
መስመሩን በተደጋጋሚ ብሞክርም እየተነጋገረበት እንደሆነ ለማውቅ ችያለሁ ከማን ጋር እያወራ ይሆን ይሄ ሁሉ ደቂቃ ስል ለራሴ ጥያቄ አነሳሁ ብዙ ጥርጣሬዎችን መፍጠር ጀምሪያለሁ ግን በአንዱ ለመወሰን ከብዶኛል ምናልባት ስላፈቀርኩትም ይሆናል

የሳሎኑን በር ከፍቼ ወደ ውስጥ ገባሁ ሀናንዬ ስል ከመጅሊሱ ላይ ተቀምጣ አይኖቿን የቴሌቭዥን መስኮት ላይ የተከለችውን ቆንጅዬ ልጅ ጉንጯን ለመሳም በርከክ አልኩኝ፡ ዳኒ ንግግሩን ጨርሶ ነው መሰለኝ መደወል ጀምሯል የቤቱን በር ከፍቼ ወጣሁና ከበረንዳው ላይ ተቀምጬ ስልኩን አነሳሁት

ቀደም ብሎ ሀሊማዬ አለ
፦ ዳኒዬ እንደምን ነህልኝ
፦ አለሁልሽ ፍቅር ቅዳሜ እንዴት ናት
፦ ምንም አይልም አንተስ ጋር
፦ ያው ደባሪ ነው ምክንያቱ ደግሞ ያንቺ ከጎኔ አለመገኘት ይመስለኛል
፦ እርግጠኛ ነህ አልኩት ፈገግ እያለኩ
፦ አዎ ነኝ አንቺ ባልናፍቅሽም እኔ ግን አንቺን እናፍቃለሁ ምክንያቱም አፈቅርሻለሁ አለ
፦ አይ ዳኒ ይሄን ቃል ግን ለጨዋታ እየተጠቀምከው እንዳይሆን
፦ እኔ እንደሌሎቹ ወንዶች አይደለሁም
፦ አምንሃለሁ
፦ እና ጥያቄዬን ተቀበልሽ
፦ ተረጋጋ እሱን ስንገናኝ እናወራለን በል በቃ ደህና ዋል
፦ እሺ አሚን ደህና ዋይልኝ ደግሞ እወድሻለሁ እሺ አለ
፦ አመሰግናለሁ
በዚሁ ሁኔታ ስልኩ ተዘጋ

ክፍል ገብቻለሁ ከአንደኛ ሴሚስተር ፈተና ቡሃላ ያለው የእረፍት ጊዜ ከመግባቱ በፊት ውጤት የሚነገርበት ቀን ነው የፈተና ወረቀት አልወሰድኩም ምክንያቱ ደግሞ አባቴን እቺን ሁለት ቀን አሞት ስለነበር ነው

ከፍል ውስጥ ያሉት የክፍሉ ሀላፊ ቲቸር ሽመልስ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ መጥራት ሊጀምሩ በእጃቸው የተማሪውን ሰትረፍኬት ይዘው ከፊት ለፊት ቆመዋል

እ.. የምናገረው ከ አንድ እስከ አስር የወጡትን ብቻ ነው አሉ የክፍሉ ተማሪ በሙሉ ድምፅ የተስማማ ይመስላል ዝምታን መርጧል

እሺ ከታች እጀምራለሁ አስረኛ....


PART ❶➍ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi