Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) የ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

የአንደኛ ሴሚስተር የመጨረሻውን ፈተና የምንወስድበት ቀን ነው ከ ዳኒ ጋር ያለንን ቅርርብ ከጊዜው እኩል እየጠነከረ ሄዷል እያፈቀር.......

PART ❶❷

የአንደኛ ሴሚስተር የመጨረሻውን ፈተና የምንወስድበት ቀን ነው ከ ዳኒ ጋር ያለንን ቅርርብ ከጊዜው እኩል እየጠነከረ ሄዷል እያፈቀርኩት ያለው ይመስለኛል ወዴት እየተጓዝኩ እንደሆነ አላውቅም

መምህሩ በየ ፊትለፊታችን የወረወረልን የፈተና ወረቀት ላይ የቻልኩትን ያህል ሰርቼ ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ ብዙም ባይባልም፣ ፈተናውን ተዘጋጅቼ ለመጠበቅ ሞክርያለሁ ከክፍል እንደወጣሁ የመጀመሪያ ስራዬ ብዬ የያስኩት ወደ ዳኒ መደወል ነበር በነገራችን ላይ የሆነ ጊዜ በማታ ደውሎ ሲያዝገኝ የነበረው እሱ መሆኑን ከራሱ ማረጋገጥ ችያለሁ ከዛ ቡሃላ ከነገሮች መቀያየር ጋር በተያያዘ እቤት ማንም በሌለበትና ምሹቱን ተገን በማድረግ ወደ ክፍሌ ስገባ ተደዋውለን እናወራለን
ዳኒ በደንብ እስኪቀረብ ድረስ ሲበዛ ዝምተኛ ተቀርቦ ሲታይ ደግሞ ተጨዋች ደግ ደስ የሚል መልከመልካም ልጅ ነው ሰሞኑን ደግሞ አንደሚያፈቅረኝ ነግሮኛል አይግረማችሁ እኔ እሱን ካፈቀርኩት ሰንበትበት ብሏል በልበ ሙሉነት ስለዳኒ ማሰብ ጀመሪያለሁ ህመሜን ማጋራው አንድም ሰው የለም ለብቻዬ መቆዘም ከሀያት ስልክ ላይ የወሰድኳቸውን የፍቅር ቀስቃሽ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ እረ ብዙ አዳዲስ ባህሪያቶችን ማሳየት ጀምሪያለሁ

ዳኒ እንደደወልኩለት ብዙም ሳይቆይ ስልኩን አነሳው ሀሉሻዬ ወጣሽ አለ አዎ" አልኩት መቼም ወግ ወጓን ለመጠበቅ ስል ኮራ ብዬ በተቀናጣ ድምፅ እሺ እኔም የጊቢው በር ላይ ቆምያለሁ፡ እሺ ጠብቀኝ እየመጣሁ ነው ብዬ ወደሱ መጓዝ ጀመርኩ ያለኝ ቦታ ላይ እንደተገናኘን አቀፈኝ እና እንዴት ነበር ፈተና ሲል ጥያቄ አነሳብኝ አይ አሪፍ ነበር አንተስጋር አልኩት እ.. ምንም አይልም ነበር አለ፡

ወዴት ይዞኝ እየሄደ እንደሆነ አላውቅም ብቻ ትከሻዬ ላይ በስፖርት ያፈረጠመውን እጁን ጣል አድርጎ ይዞኝ ይጓዛል በንግግሮቹ አስምጦኛል ዳኒ አልኩት በመሀል የምንሄድበትን ቦታ በመናፈቅ ወዬ አለ አይኖቹን አይኖቼ ላይ ተክሎ ፍቅር በተሞላበት አስተያየት እየተመለከትኩት ወዴት ነው እየሄድን ያለነው ስል ጠየኩት ምነው ደከመሽ ወይንስ ፈራሽ ሲል ጠየቀኝ እየሳኩኝ አይ ሳይሆን እንዲሁ ለማወቅ ነው አልኩት እ.. ደርሰናል በቃ አሁንማ ታይዋለሽ ሲል ምላሽ ሰጠኝ

በአረንጎዴ ሳርና ዙሪያም በፅድ ከታጠር ውብ ከሆነ ጊቢውስጥ ተገኝተናል ቦታውን በጣም ወድጄዋለሁ አንገቴን ወደ ዳኒ ትከሻ ዘንበል በማድረግ ተደግፌው ጣቶቹን ከ ጣቶቼ ጋር ቆላልፌያቸው ለብቻችን ተቀምጠን የሆድ የሆዳችንን እያወጋን ነው ሀሉ አለ የጀመረልኝን ደስ የሚል ጨዋታ አቋርጦ ከትከሻው ቀና ብዬ ፊት ፊቱን እያየሁት ወዬ አልኩ ለምንድን ነው ላቀረብኩልሽ የፍቅር ጥያቄ ምላሽ ማትሰጭኝ አለ ትንሽ ዝም ካልኩ ቡሀላ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ አሳውቅሃለሁ አልኩት ዝምታን መርጧል ግን ስለ ምንድን ነው ማሳውቀው እንደማፈቅረው ባልነግረውም አፈቅሬዋለሁ ግን ፈርቻለሁ ጥያቄውን የምቀበለው አይመስለኝም ምክንያቱም ብዙ ነገሮች አንድ አያደርጉንም ብቻ በብዙ ሀሳቦች ተጨናንቄያለሁ ፡ሰአቱ ሄዷል አክስቴ እንደዚህ ቆይቼ እንደማላቅ ስለምታቅ እንዳትቆጣኝ ስል ከዚ በላይ መቆየት እንደሌለብን ነግሬው ጊቢውን ለቀን ወጣን

ትንሽ ጫን እያለኝ ነው አለ ምናልባት የስኳሩ መጠን ከፍ እያለ ይሆን እንዴ አለ ከ ባባ አጠገብ የተቀመጠው የአክስቴ ባል እኔንጃ ብቻ ሰሞኑን መድሃኒቱን ወስጄ አላውቅም ነገ ሄጄ እታየዋለሁ አለ ከተቀመጠበት ቦታ እየተነሳ እላዬ ላይ ተቀምጣ ስትጫወት የነበረችውን ሀናንን ከላዬ ላይ አውርጃት ባባን ተከተልኩት.....

PART ❶➌ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi