Get Mystery Box with random crypto!

ኡዱሂያ ➾ ኡዱሃያ መልዕክተኛዉ ካስተማሯቸዉ እና ከተገበሯቸዉ ጥብቅ ሱናዎች አንዱ ነዉ፡፡ ኡዱሂያ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

ኡዱሂያ

➾ ኡዱሃያ መልዕክተኛዉ ካስተማሯቸዉ እና ከተገበሯቸዉ ጥብቅ ሱናዎች አንዱ ነዉ፡፡ ኡዱሂያ
ማለት በኢድ አል-አድሀ አረፋ የሚደረግ እርድ ነዉ፡፡

➾ መልዕክተኛዉ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ
እንዲህ ብለዋል (የዙልሂጃን ጨረቃ ያያችሁ ጊዜ እርድ ማረድ ከፈለጋችሁ ፀጉራችሁን እና
ጥፍራችሁን ከመቁረጥ ተቆጠቡ)፡፡

➾ ለኡዱሂያ እርድ የተወሰኑ አማራጮች አሉ እነሱም ግመል፣ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ ናቸዉ አንድ ግመል ወይም በሬ ለሰባት መከፋፈል(ቅርጫ) ይቻላል የሚታረዱ እርዶች አይብ የሌለባቸዉ መሆን አለባቸዉ ፡፡ ለምሳሊ ቀንደ ሰባራ፣እግረ ቆማጣ እነዚህን የመሳሰሉት ለአረፋ አይታረዱም

➾ የዓረፋ ቀን ዱዓ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

የዐረፋ ቀን ከሚፈፀሙ ትላልቅና ወሳኝ ዒባዳዎች ውስጥ አንዱ ዱዓ ነው!!

የእዝነቱ ነብይ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በተከበረው ሐዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
" خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي : لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ".
*
<< በላጭ ዱዓ ማለት የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔንም ከእኔ በፊት የነበሩት ነብያቶችም ከተናገርነው ንግግር በላጩ ' ላኢላሃ ኢልለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ ፤ ለሁልሙልኩ ወለሁል ሓምዱ ወሑው ዓላኩሊ ሸይኢን ቀዲር ( ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም ብቻውን ነው ተጋሪም የለውም ንግስናም የእሱ ነው፣ ምስጋናም የእሱ ነው እሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።) ' የሚለው ንግግር ነው። >>


➾ ተዉሂድ ማለት ምን ማለት ነዉ?

➾ ተዉሂድ ማለት አዘልይ (ጂማሬ የሌለዉን ፈጣሪያችንን አላህን ከፍጡራኖች ለይቶ ማወቅ ነዉ ሲሉ ኢማም አል ጁነይድ መልስ ሰጥተዉበታል

➾ ጌታችን አላህ ፍጡራኖችን አይመስልም በፆታም ሆነ በከለር በቦታም ሆነ በአቅጣጫ በመሳሰሉት በፍጡራን ባህሪያቶች አይገለፅም

➾ አላህ በተቀደሰ ቁርዐኑ እንዲህ ይላል አላህን የሚመስል ምንም ነገር የለም፡፡ ሱረቱል ሹራ

ሁላችንም ሊላህ ብለን ሼርርርርር እናድርገው

ኢድ ሙባረክ በአሉን የሰላም የፍቅር የደስታ የአንድነት አሏህ ያድርግልን

ወሰላሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ተአላ ወበረካቱሁ


╔═══════════════╗
                @Eslmnachin99 
╚═══════════════╝