Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) አ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

አፍ..... ስል በረጅሙ ከተነፈስኩ ቡሃላ ወደ ዲኒ ጉንጮች ተጠጋሁ ዳኒ አንዳች ነገር ለመናገር ፈልጎ ከመቅስፈት ወደ እኔ ዞር ሲል ከን.........

PART ❶❶

አፍ..... ስል በረጅሙ ከተነፈስኩ ቡሃላ ወደ ዲኒ ጉንጮች ተጠጋሁ ዳኒ አንዳች ነገር ለመናገር ፈልጎ ከመቅስፈት ወደ እኔ ዞር ሲል ከንፈሮቼ ከከንፈሩ ጋር ተጋጩ በተፈጠረው ነገር ደንግጫለሁ በፍጥነት ወደውኃላ ሸሸሁ ሃያት በተፈጠረው ነገር ቅንጣትም አልደነገጠችም ይባስ እንደው በሳቅ እየፈረሰች ነው፡ የሆነውን ነገር ከሌላኛው ህናፃ ላይ ሆኖ ሲክታተል የነበረው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ሲጋልብ ወደ እኛ መጣ እንደተመለከትነው ከነበርንበት ወንበር በፍጥነት ወረድን ሀያት አሁንም መሳቋን አላቆመችም ዳይሬክተሩ አጠገባችን እንደደረሰ ምን እየሰራችሁ ነበር አለ፡ ደንግጬም የለ ቀደም ስል ምንም አልኩ ሀያት ሲቃ በተሞላበት ድምፅ መሳቋን አላቆመችም ዝም በይ አለ ከእግሬ ጫፍ አንስቶ እየገላመጠኝ ምንድን ነው ስታደርጉ የነበረው ብሎ አይኑን ዳኒ ላይ አፈጠጠ ዳኒ የሆነውን ነገር ለማስረዳት የከበደው ይመስላል አይኖቹን ከመሬት ላይ ሊነቅላቸው አልቻለም እኔም ወደ ዳኒ ከንፈሮች አይኖቼን ጥዬ የሚያወጣውን ቃል በመጠባበቅ ላይ ነኝ፡

ግን አንዳችም ነገር ከአፉ ፍንክች አላለም፡ እሺ ለማንኛውም እናንተ እታች ወርዳቹህ ቢሮ በር ላይ ጠብቁኝ አንቺ ደግሞ ነይ ወደ ሜዳ ሂጂ ሲል ለኛም ለሀያትም ቀጠን ያለ ትህዛዝ ሰጠንና ሄደ

እኔና ዳኒ የቢሮው በር ላይ ቆመን የዳይሬክተሩን መምጣት መጠባበቅ ጀመረን እኔ የተፈጠረውን ነገር በማሰብ ይዞ የሚመጣውን ጣጣ እያውጠነጠንኩ ፊቴን በእንባ አራስኩት የተደገፍኩትን ግርግዳ እየታከኩ ወደ መሬት ወረጄ ተቀመጥኩ ዳኒ ከቆመበት በርከክ ብሎ ፊት ፊቴን እያየ እየደጋገመ በተፈጠረው ነገር ላይ ይቅርታ ጠየቀኝ የሱ ጥፋት አለመሆኑን ነገርኩት አይ የኔ ነው ብሎ እየተሟገተ እንባዎቼን በጣቶቹ ዳበስ ዳበስ እያደረገ ጠረገለኝ በቃ ተነሽ ምንም አይለንም አለና ከተቀመጥኩበት እንድነሳ አደረገኝ

ተማሪው የሰንደቅ አላማ ፕሮግራሙን ጨርሶ ከሜዳ ወደ ክፍል መመለሰ ጀምሯል ሀያት እኛ ወዳለንበት መታለች ዳይሬክተሩን ተጨቃጭቀነው አንድናሳምነው ነግራን ወደ ክፍል ሄደች ወይኔ ሃያት ባለውቅሽ ምንኛ ደስ ባለኝ እያልኩ በሆዴ ሀሳቧን ተቀበልኳት፡ በዚህ መሃል የአምና ጎደኞቼ ኢልሀምና ሲትራ ወደ ክፍል አብረው ሲገቡ ተመለከቱኝ በፍጥነት ወደ እኔ መተው ሀሉ ምንሆነሽ ነው ሲሉ ጠየቁኝ እኔንም ዳኒንም ደጋግመው እየተመለከቱን አንድምቀን አስቀይሜያቸውም ሆነ ዋሽቻቸው ማላቃቸውን ዛሬ ልዋሻቸው ተገድጃለሁ ፡እ" እናንተ እኮ ወደ ሜዳ ስትወጡ እኛ ክላስ ውስጥ ሆነን አስቸኳይ አሳይመንት ነበረብን እሱን እየሰራን እያለ ዳይሬክተሩ መቶ ያዘን ከዛ ያው እንደምታዩት እዚህ አስቁሞን ጠፋ ስል ዋሸዋቸው ፡ወይኔ በአላህ አለች ሲትራ እንደማዘን እያለች ፡በሆዴ ጉዴን ብትሰሙ ከዚህ በላይ ባዘናችሁልኝ ነበር እያልኩ በቃ መምህር እንዳይገባባችሁ ቡሃላ እደውላለሁ ወደ ክፍል ሂዱ ብዬ ሸኘዋቸው

ዳይሬክተሩ መቷል ወደ ቢሮ አስገብቶ እያወራን ነው ወላጅ አምጥተን ፈርመን እንደምንገባ እየነገረን ነው እኔ እንባዬን እንደጉድ አፈሳለሁ ዳኒ ለማስረዳት እየሞከረ ይማፀነዋል እኔ በሀዘን ውስጥ ሆኜ የተፈጠረውን ነገር በደንብ አስረድቼው አጋጣሚ እንደነበርና ሁለተኛ እንደማይደገም እየተማፀንኩ ነገርኩት

ይሄን ሁሉ እንባ ካፈሰስኩ ቡሃላ የርህራሄ መንፈስ የተጠናወተው ይመስለኛል የተቀመጠበትን ተሽከርካሪ ወንበር እያዟዟረ የጊቢው ጎበዝ ተማሪ ስለሆንሽ ምህረት አደርግልሻለሁ ሁለተኛ ባያችሁ ግን ዋ.. አለና ቢሮውን ለቀን እንድንወጣ እጁ ላይ በያዛት እስክሪብቶ ምልክት ሰጠን ዳኒ ከመቀመጫው ተነስቶ ስለተረዳህን እናመሰግናለን ብሎ የቢሮውን በር ከፍቶ ወጣ እኔም ተከትዬው እንደጎርፍ የወረደውን እንባዬን እየጠራረኩ ወጣሁ ወደ ክፍሌ የሚያሶጣው ደረጃ ጋር ስደርስ ዳኒ ፈገግ ብሎ አየኝና ይቅርታ ብሎ ከእቅፋ ውስጥ አስገባኝና በይ በቃ አሁንም እንዳይዘን ብሎ ትንሽ ፈገግ አስብሎኝ ወደ ክፍሉ ሄደ።

እቤት ገብቻለሁ አልሃምዱሊላህ ሀናን አሁን በመልካም ጤንነት ላይ ነች ጠዋት ያለቀስኩበት ነው መሰለኝ እራሴን ወጥሮ ይዞኛል አክስቴ እንዳመመኝ ስለተረዳች እረፍት እንዳደርግ ነግረችኝ ወደ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ጋደም አልኩ እነ ኢልሃም ከዛ ቡሃላ ስላላገኘዋቸው አሁን እየደወሉ ነው ላነሳው ግን አልፈለኩም።

ጊዜያቶች ወራቶች ሁሉም ጊዜያቸውን በመጠበቅ ተጉዘዋል ዛሬ የአንደኛ ሴሚስተር የመጨረሻውን ፈተና የምንወስድበት ቀን ነው ከ ዳኒ ጋር ያለንን ቅርርብ ከጊዜው እኩል እየጠነከረ ሄዷል እያፈቀር.......

PART ❶➋ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi