Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) እ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

እቤት ገብቻለሁ ከትላንትና ምሽት ጀምሮ የተዘጋችውን ስልክ አሁን ገና ከፈትኳት የመጀመሪያው ደዋይ አባቴ ነው ስልኩን አንስቼ ቀደም ብዬ ሰላምአለይኩም ስል ሰላምታ አቀረብኩለት........

Part ❶0

ቀደም ብዬ ሰላምአለይኩም ስል ሰላምታ አቀረብኩለት ወአለይኩም ሰላም ሀሊማዬ እኔ ምልሽ አለ ወዬ ባባ አልኩት ከክፍሌ ውስጥ ሆኜ የቀየርኩትን ዩኒፎርም ለማስቀመጥ በአንድ እጄ እያጣጠፍኩት መጡ እንዴ አለኝ አልገባኝም እቤት ስገባ ግን ማንንም አለማግኘቴን አውቃለሁ እነ ማን ስል ጠየኩት እነ ሙና አለ እነ ሙና.. ማለት እንዴ እነ ሙና በዚህ ሰአት ከስራ ገብተው ያውቃሉ እንዴ አባዬ ምን ነክቶት ነው ግራ ገብቶኛል እንዴ ባባ እነ ሙና በዚህ ሰአት ከስራ ገብተው ያውቃሉ እንዴ ስል ጠየኩት እንዴ አክስትሽ እኮ በሙና ስልክ ደውላልኝ ሃናን አሞት ሆስፒታል መሆናቸውን ነግራኝ ነበር፡ አለ ትንሿ ሀናንን ምን እንደነካብኝ አላውቅም በጣም ስለምወዳት ነው መሰለኝ በንግግሩ በጣም ደንግጫለሁ እንዴ ጉድ መቼ ስል ጮህኩበት አይ ትንሽ ቆየት ብለዋል አልደወሉልሽም ነበር እንዴ አለ፡ ስልኬን ትምህርት ቤት ይዤ አለመሄዴን ነገርኩት እሺ በቃ ስደውልላቸው እኮ ሙና አታነሳም ለአክስቴ አልሞክርም እኔ ልደውልላት አልኩ ንግግሬን ጣደፍ ጣደፍ እያረኩ አይ የሷም አይሰራም በቃ ለማንኛውም የሰማሽ ከሆነና እቤት ከተመለሱ ብዬ ነው በቃ ተረጋጊና ጠብቂያቸው እንደመጡ ደውይልኝ አለና ስልኩን ዘጋው የማደርገው ጠፍቶብኛል እንዴት ኡስታዝ የጊቢውን በር ሲከፍቱልኝ አልነገሩኝም እንዴ፡ ስቻኮል ክፍሌን ለቅቄ ወጣሁና ወደ ጊቢው በር አመራው

ትንሽዬዋ የኡስታዝ ቤት ጋር ስደርስ ኡስታዝ ከውስጥ ሲወጡ በራቸው ላይ ተገጣጠምን አይኖቼ እንባን እንዳቀረሩ ኡስታዝን ወደ ላይ ቀና ብዬ እየተመለከትኩ የተፈጠረው ምን እንደሆነና ለምን እንዳልነገረኝ ጠየኳቸው፡ በመጀመሪያ ተረጋጊ የኔ ልጅ ሲሉ መናገር ጀመሩ.......

ምንም እኮ አትሆንም አሉ በሸሽ ያለ ፊታቸው ላይ ፈገግታን እየጨምረው ንግግራቸውን እየቋጩ ፈገግ ብዬላቸው ከአይኔ ሲወርድ የነበረውን እንባ የለበስኩትን ሹራብ እጁን ጉትት አድርጌ ጠራርጌ ወደ ሳሎን ተመለስኩ ወደ ውስጥ እንደገባሁ እራሴን ለማረጋጋት እያሰብኩ ከመጅሊሱ ላይ ልቀመጠ ስጠጋ የአክስቴን ስልክ ተመለከትኩ ሲጣደፋ እንደወጡ አሁን ያነሳሁት ስልክ ብትንትን ማለቱ ያስታውቃል አንስቼ ሁሉንም በቦታው በቦታው ሰክቼ ስልኩን ከፈትኩት በዚህ መሃል የሚከፈት በር እንዳለ ተረዳሁ ስልኩን ካነሳሁበት ቦታ መልሼ ስጣደፍ ከቤት ወጣሁ ኡስታዝ የጊቢውን በር ከፍተው የመጣውን መኪና ወደ ጊቢ እንዲገባ አደረጉ፡ ፈጠን ብዬ ወደቆመው መኪና ተጠጋሁ ሙናም አክስቴም ከመኪናው ወረዱ አይኖቼን አነጣጥሬ ሚጢጢዬዋ ሀናን ላይ ጣልኳቸው ከመኪናው እንደወረደች እሷም ወደ እኔ ተጠጋች የአይኖቿ መደፍረስ አንዳች በሽታ ሽው እንዳለባት በደንብ ያስታውቃል አቀፍኮትና ደጋግሜ ጉንጮቿን እያገላበጥኩ ሳምኳቸው ስለ ደህንነቷ ደጋግሜ እየጠየኳት አቅፌ ወደ ውስጥ ይዣት ገባሁና ከመኝታ ክፍሏ አስገባዋት

የተደረደረው ሲኒ ዛሬ በእኔ እጅ
የተፈላውን ቡና ለወዳጆቼ ሊያደርስ የቡናውን ማፍላት በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስላል እኔም በያስኩት ማራገቢያ እሳቱን አፋፍመዋለሁ..

ነጃት ከመኝታ ቤቱ ወታ ቤተሰቡ ዘወትር ምሽት ወደሚሰበሰብበት ቦታ ለመቀላቀል መጣች እንዴትናት ሲል ከ ባባ አጠገብ የተቀመጠው የሀናን አባት ጥያቄ አነሳባት አይ ትንሽ በልታ ሾሮፗን አጠጥቻት ተኝታለች አለችው አይ ምንም አትልም ብርድ እኮ ነው አባ አትጨነቅ አለ ከአክስቴ በስተቀኝ በኩል የተቀመጠው የሀናን ወንድም አልሃምዱሊላህ አሁንማ ደህና ናት ብላ ሙናም ከምንጣፉ ላይ ተደላድላ ተቀመጠች....

ሀናንን እዛው መኝታ ክፍል ውስጥ እንዳለች ጠይቄያት ትንሽ አጫውቻት ግንባሯ ላይ ሳም አድርጊያት ወደ ትምህርት ቤት ወጣሁ አባቴ ቀድሞኝ ስለወጣ ብቻዬን ለመሄድ ተገድጃለሁ

ጊቢ እንደገባሁ ሀያትን እዛው ዘወትር ከምትቀመጥበት ቦታ ላይ አገኘውኋት ሀዩ ሰላምአለይኩም ስል ወደ ጉንጮቿ ጠጋ ብዬ ሳም አደረኳትና ቦርሳዬን ከክፍል ውስጥ አኑሬ ተመልሼ ወደ ሀዩ መጣው ሰአት ገና ስለሆነ ከሀያት አጠገብ ተቀመጥኩ ስለ አንዳንድ ነገሮች እያወራን መጫወት ጀመርን በዚህ መሀል ዳኒ ተብዬው ወደ እኛ ሲመጣ ተመለከትኩ አይቼው እንዳላየ ሆንኩ ሃያትን ሰላም አላትና እጁን ወደ እኔ ዘረጋ ያለምንም ማመናታት ፈገግ ብዬ እጄን ዘረጋሁለት፡ ለምን ለወንድ ዘርግቼ አላውቅም ምን ሆኛለሁ እያለኩ ከራሴ ጋር መነጋገር ጀመርኩ ወዴት እየሄድኩ ነው፡ ጨበጠኝና ከበስተጀርባችን ዞሮ ተንጠልጥለን ከተቀመጥንበት ወንበር ላይ ወቶ ከእኔ አጠገብ ተቀመጠ አንዳንድ ጨዋታዎችን እያነሳ በጣም እያሳቀን ነው እንዴ አለች ሀያት በመሃል ምነው አልኳት አንገቴን ወደሷ አዙሬ ከተቀመጠችበት ወንበር ወረደችና የህንፃውን የኮሪደር ብረት ደገፍ ብላ የትላንትናው የተቋረጠው ትህዛዝ አለች በፍጥነት አንገቴን ወደ ዳኒ አዞርኩኝ ምንም መስሎ የታየው አይመስለኝም እንዴ ሀዩ ደግሞ የሌለ አልኳት ደግሞ አብረውን የነበሩት የሉም እኮ አልኳት እንዴ አይኑሩ አ" እኛ አይደል እንዴ ጨዋታውን የጀመርነው እ" አይደል ዳኒ አለችው አይኖቿን አፍጣበት እሱ ዝምታን መርጧል እኔ አይኖቼን አንዴ ሀዩ ላይ ሲቀጥል ዳኒ ላይ አመላልሳቸዋለሁ ሀዩ ድርቅ የምትለው ነገር ደግሞ አለ በቃ እ ፈፅሚያ ትላንትና እኔ ስታዘዝ እንዴት ነበር ስትሆኚ የነበረው በይ አፍጥኝው አለች ኡፍ..... ስል በረጅሙ ከተነፈስኩ ቡሃላ ወደ ዲኒ ጉንጮች ተጠጋሁ ዳኒ አንዳች ነገር ለመናገር ፈልጎ ከመቅስፈት ወደ እኔ ዞር ሲል ከን.........

PART ❶❶ ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi