Get Mystery Box with random crypto!

#የአባቴ_ገዳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ! ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi) | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#የአባቴ_ገዳይ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ !

ፀሀፊ፦ ካሊድ (kalido ye umi)

ቦታሽን ያስኩብሻ ይቅርታ አለኝ ፈገግ ብሎ አይ ችግር የለውም እንደውም ሲደወል እንቀሰቅስሃለን ተኛ አልኩት አይ.....

Part ❾

ቦታሽን ያስኩብሻ ይቅርታ አለኝ ፈገግ ብሎ አይ ችግር የለውም እንደውም ሲደወል እንቀሰቅስሃለን ተኛ አልኩት አይ ይብቃኝ እቺ አዝግ እኮ አላዋራ ስትለኝ ነው ዝም ብዬ ጋደም ስል እንቅልፍ የወሰደኝ፡ እኔን ብቻ ባልሆነ እየወቀስክ ያለከው አልች ሀያት አሁንም በድጋሚ የምታነበውን መፅሐፍ ከድና አንገቷን ወደ ዳኒ ተብዬው መዘዝ አድርጋው እንዴ በቃ እርሱት አልኳቸው ከመሃከላቸው እንዳለሁ በእኔ መምጣት ምክንያት ሊነሳ የተፈጠረውን ችግር በማሰብ።

ዳኒ ትንሽ ሳቀና ዝምታን መረጠ፡ እኛ ከተቀመጥንበት ውጪ ግማሹ የሆድ የሆዱን ያወራል ግማሹ መስኮት ላይ ተሰክቶ ወደውጭ ያያል ከፊሉ ደብተሩን ገልፆ ያነባል ፡እኔ ምላቹህ" አለች ሀያት የዳኒን አይኖች ለማየት እንዲመቻት በተቀመጠችበት ወደ ጎን ዞር ብላ፡ የሆነ ነገር ልታወራ መሆኑን ስለተረዳን ጆሯችንን ሰጠናት፡ ለምን ከሚደብረን ትእዛዝ ነገር አንጫወትም አለች

አይ እንግዲህ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር አይመቸኝም አልኩ ቀደም ብዬ እረ" ሀሊማ ሙድሽ ምንድን ነው አለች አይ እንደውም ሁለታችሁ ብቻ ተጫወቱ ብዬ በሀያትና በ ዳኒ ማሃል እንዲቀር ለማድረግ ሞከርኩኝ ሃያት ለማኩረፍ እየቃጣት አየሃት" አይደል ዳኒ አትገርምም አለችው አይ መብቷ እኮ ነው አለ የባስ ሀያት ፊቷን ከሰከሰችው እንደሙዳቹህ ብላ ወንበሩ ላይ ተደፍታ ተኛች ዳኒ አንዳንድ ቃላቶችን እየወረወረ ነው ትንሽ ሊያናዳት የፈለገ ይመስላል እኔም በንግግሮቹ እስቃለሁ ሀዩ እንደከፋት በደንብ ተረድቻለሁ ምክንያቱ ደግሞ እኔው ነኝ፡

ወደ ሀዩ ጆሮ ጎንበስ ብዬ ሀዩ በቃ ነይ ተነሽ እንጫወት መቼም ችክ ካልሽ ችክ ነው ደረቅ ተነሺ በቃ አልኩ" ፈገግ እያለች ካጎነበስችበት ቀና አለች የቦርሳዋን ዚፖች በመክፈት ከኪሱ ውስጥ እስኪሪቢቶ አውጥታ እ ከማን ይጀመር ስትል ጠየቀችን እኔና ዳኒ እራስ በራሳችን ተተያየን ደስ እንዳለሽ ሲል ዳኒ ሀሳብ አቀረበ እ አንቺስ አለች እኔም ከ ዳኒ ጋር የሚመሳሰል ምላሽ ሰጠዋት በቃ እኔ ልጀምረው ብላ እስኪሪቢቶውን በሁለቱ ጣቶቿ መሀል አኑራቸው ወንበሩ ላይ እንዳለ አሽከረከረችው ልቤ በጣም ፈርቷል ያሽከረከረችው እስክሪብቶ ምልክቱ ዞሮ ዞሮ እራሷ ላይ ቆመ ሁላችንም ሳቅን ከ ዳኒ ጋር ተመካክረን ቀለል ያለ ትህዛዝ ሰጠናት እሷም ምንም ሳትጨቃጨቅ ፈፀመች ጨዋታችን ደርቷል ብዙ የክፍሉ ተማሪዎች ተቀላቅለውናል እኔ እስካሁን አልወጣብኝም ሀያትም ዳኒም ሌሎችም አዲስ ጨዋታውን የተቀላቀሉ ተማሪዎችም ደርሷቸዋል የአሁኑን ተራ አዲስ ጨዋታውን ከተቀላቀሉት ውስጥ አንዷ እስኪሪብቶውን እሷ እንድታሽከረክረው ተደረገ ገና ከመጀመሯ እኔ ላይ ወጣ ሀያት ከት ብላ ሳቀች ቀለል ያለ ነገር ያዙኛል ብዬ ስላሰብኩ ከቁምነገርም አልቆጠርኩትም ወደ ልጅቷ ጆሮ ሀያት ጠጋ ብላ አንሾካሸከች ልጅቷ ልታዘኝ ተዘጋጀች ከአጠገቤ የተቀመጠውን ዳኒን ስሙን ስለማታውቀው ጣቶቿን ወደ እሱ ቀስራ ፈገግ እያለች ሳሚው አለች በጣም ደንግጫለሁ ምናለ ባልተጫወትኩ ማለት ጀመርኩ በሆዴ ትህዛዙ ከባድ ነው ይቀየርልኝ ስል ስሞታ አቀረብኩ እንደማይቻል ገለፁልኝ ሀያትማ ምን አስባ እንደሆነ አላውቅም እንደይቀየር በዋነኝነት የተሟገተችው እሷ ናት አማራጭ እንደሌለኝ ሳውቅ ለመሳም ፊቴን ወደ ዳኒ አዞርኩኝ

የመጀመሪያዬ ነው የማላውቀውን ሰው ስስም ያውም ወንድ ፈራ ተባ እያልኩ ወደ ጉንጮቹ ከንፈሮቼን አሹዬ ተጠጋሁ..
በዚህ መሀል በከፍተኛ ድምፅ የክፍሉ በር ተንኳካ መምህር መሆኑ ያለምንም ጥርጥር ያስታውቃል ተማሪው ቦንብ የተወረወረበት በሚምስል መልኩ ወደየ ቦታው ተበታተነ እኔም ያልፈለኩትን ከመፈፀም የተገላገልኩ ይመስለኛል በሩ እስኪከፈት እንደኔ የጓጋ ያለ አይመስለኝም በሩ ተከፈተ እንዳሰብኩት መምህር ነው ኡፍ..... ስል በረጅሙ ተነፈስኩ ዳኒ ወደ ክፍሉ ለመሄድ ተነሳ በፍጥነት ላሳልፈው ቆምኩ ሀያት ትእዛዙን ነገም ቢሆን ትፈፅማታለች አለችው ፈገግ ብሎ ቻው በሉ አለና ክፍሉን ለቆ ወጣ

እቤት ገብቻለሁ ከትላንትና ምሽት ጀምሮ የተዘጋችውን ስልክ አሁን ገና ከፈትኳት የመጀመሪያው ደዋይ አባቴ ነው ስልኩን አንስቼ ቀደም ብዬ ሰላምአለይኩም ስል ሰላምታ አቀረብኩለት........

Part ❶0 ይቀጥላል !

any comment @kaludi_bot

join
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi
@kalidoyeumi