Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ሻሸመኔ ‘’ዛፍ ላይ ወጥቼ ነው ምደውልላችሁ’’ - የሻሸመኔ ምእመን ሕገ ወጥ ቡድኑ የሻሸመኔ | JUSTIN APOLOGETICS]

ዜና ሻሸመኔ
‘’ዛፍ ላይ ወጥቼ ነው ምደውልላችሁ’’ - የሻሸመኔ ምእመን
ሕገ ወጥ ቡድኑ የሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ታግዞ ከሰበረ በኋላ በርካታ ምእመናን ወደ አልታወቀ ቦታ እየታፈሱ እየተወሰዱ መሆኑን የከተማው ዓይን እማኞች ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አድርሰውናል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን አሳልፈን አንሰጥም ባለው ምእመን ላይ የከተማው ሚሊሻ፣ፖሊስና ልዩ ኃይል በቅንጅት ተኩስ በመክፈትም በርካታ ምእመናን እንዳቆሰሉና የቆሰሉትን ሳይቀር ወደ ፖሊስ ጣቢያ እያስገቡም ይገኛሉ።

እንደመረጃ ሰጭዎቻችን ከሆነ በአይሱዙ መኪና ካህናትና ምእመናንን ከየቤቱ እያሰሱ በማፈስ ወደ አልታወቀ ቦታ እየወሰዷቸው ነው ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ምእመናን በኃይል ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ በመደረጉ ተበታትነው እየተሳደዱ ይገኛሉ ያሉት መረጃ ሰጫችን ይህንንም መረጃ "ዛፍ ላይ ወጥቼ ነው ምደውልላችሁ" በማለት ያለውን የደኅንነት ስጋት ገልጸውልናል።

የከተማው ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያናቸውን አሳልፈው እንደማይሰጡ ሲታወቅ ሕገ ወጥ ቡድኑ ደጋፊዎች የሌላ ቤተ እምነት ተከታዮችን በማስተባበር መስቀል ሲያስሩና ነጠላ ሲያለብሱ እንደነበር የዓይን እማኛችን ተናግረዋል።