Get Mystery Box with random crypto!

'የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?' ብፁዕ አ | JUSTIN APOLOGETICS]

"የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ



የሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ እንዲሁም የምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ምሽት የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሻሸመኔ አብያተክርስቲያናትን በመሥበር ምእመናንን በግፍ በማሠርና በመደብደብ ከየአካባቢው ባመጧቸው ቡድኖች አብያተክርስቲያናት ተቆጣጥረዋል ሲሉ ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በስልክ ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ "የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?" ያሉ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሰጡትን መግለጫ ምእመናን እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
በ13 ወረዳዎች ሊቃነ ካህናት በግፍ መታሠራቸውን ገልጸዋል።
የብፁዕነታቸውን መልእክት በዩቲዩብ ገጻችን ይከታተሉ።

ምንጭ: EOTC TV