Get Mystery Box with random crypto!

የፀጉር መነቃቀል የአንድ ጤናማ ሰው ፀጉር እድሜውን ሲጨርስ በራሱ ግዜ ይነቃቀላል። | Romeo & Juliet ❤️ ✔

የፀጉር መነቃቀል

የአንድ ጤናማ ሰው ፀጉር እድሜውን ሲጨርስ በራሱ ግዜ ይነቃቀላል።

አንድ ጤናማ ሰው ላይ በቀን ከ 60 እስከ 90 የሚደርሱ የፀጉር ዘለላዎች እድሜያቸውን ጨርሰው በራሳቸው ይረግፋሉ።

ከልክ ያለፈ የፀጉር መነቃቀል መኖሩን ለማወቅ አውራጣትን እና ጠቋሚ ጣትን ብቻ በመጠቀም፣ በግምት ከ 20 እስከ 60 የሚደርሱ የፀጉር ዘለላዎችን በመያዝ በመለስተኛ ጉልበት መሳብ

ይህ በሚደረግበት ግዜ፣ በጣት ከተያዙት የፀጉር ዘለላዎች መሀል 10 በመቶ እና ከዛ በላይ የተነቀሉ ከሆነ ፣

ማለትም 20 የፀጉር ዘለላ ይዛችሁ፣ ሁለት እና ከዛ በላይ ፀጉር ከተነቀለ፣ ጤናማ ያልሆነ የፀጉር መነቃቀል እንዳለ ያመላክታል

ጤናማ ያልሆነ የፀጉር መነቃቀል ብዙ ምክኒያቶች አሉት። ለምሳሌ፣

የምግብ እጥረት፣ በተለይ የ Vitamin B7, Vitamin D, እና የ Zink እጥረት ካለ።
በበሽታ ምክኒያት የሚመጣ የሰውነት ጫና፣ ወይም የአልጋ ቁራኛ ከመሆን ጋር ተያይዞ።
የደም ማነስ
ከወሊድ በኋላ
ፀጉርን ያለልክ በመጎተት
የራስ ቅል ላይ የሚደርሱ የፈንገስ እና የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች
ላሽ፣ ራሰ በርሀነት፣ እና የራስ ቅል ላይ የሚደርሱ የተለያዩ የቆዳ በሽታዎች ለፀጉር መነቃቀል እና መመለጥ ዋና ዋና ምክኒያቶች ናቸው።

የፀጉር መነቃቀልን እና መመለጥን ለማከም መጀመሪያ ምክኒያቱን ማወቅ ግዴታ ነው።

ለምሳሌ፣ በደም ማነስ ምክኒያት የመጣ የፀጉር መነቃቀል ካለ፣ ለደም ማነስ ህክምና በማረግ ብቻ የፀጉር መነቃቀልን መመለስ ይቻላል።

ታዲያ፣ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ፣ ፀጉርን ያሳድጋሉ ተብለው በቤት ውስጥ የሚሰሩ፣ የሮዝመሪ ዘይት፣ የዱባ ፍሬ ዘይት፣ የሽንኩርት እና የሩዝ ውሀ የመሳሰሉት፣ ምንያህል እውነተኛ ናቸው?

ለየትኛው አይነት የፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል ነው የሚጠቅሙት?

ሰፋ ያለ መረጃ youtube ላይ አስቀምጫለው