2022-08-27 18:35:36
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው ልዑካን ቡድን ነጃሺ (አፍሪካ አንድነት) ኢስላማዊ ኮሌጅና መስጂድን ጎበኘ።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ቱፋህ እና ተ/ም/ፕረዚዳንት ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን የተመራው ልዑካን ቡድን ከአፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት የሚገኘውን ነጃሺ (የአፍሪካ አንድነት) መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል ይፋዊ ጉብኝት አደረገ።
የልዑካን ቡድኑ የጠ/ም/ቤቱን አመራሮችና ሥራ አስፈጻሚዎች ጨምሮ ከአዲስ አበባና ኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች እንዲሁም ታዋቂና በጎ አድራጊ ግለሰቦች የተውጣጣ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የጉብኝቱ ዋና ዓላማም ቦታው ያለበትን ሁኔታ በማየት በቅርቡ ለታቀደለት ዓላማ እንዲውል እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማብሰር መሆኑንም የጠ/ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ እ/ጉ/ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ማዕከሉ በሐገራችን የተገኘውን ለውጥ ተከትሎ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ደረጃውን የጠበቀ ኢስላማዊ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ለህዝበ ሙስሊሙ በገቡት ቃል መሠረት 30,000 ካሬ መሬት እንዲሰጥ ማድረጋቸውን ጠቅሰው ለዚህ ተግባራቸውም ላቅ ያለ ምስጋና እንደሚገባቸው በጉብኝቱ ማብቂያ ላይ ተናግረዋል።
ጠ/ም/ቤቱና የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ምክር ቤት በጋራ በአፍሪካ መገለጫ የሆነውን መስጂድና ማዕከል እንደሚገነባ ገልጸው ከአቅም ጋር ተያይዞ ግንባታው ላይካሄድ ይችላል ለሚለው የህዝበ ሙስሊሙ ስጋት በጎ አድራጊዎች ለበጎ ሥራ እየተሽቀዳደሙ መሆናቸውን ያበሰሩት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አያይዘውም የዋናው ግንባታ አርክቴክቸራል ዲዛይን አማራጮች ለሥራ አስፈፃሚ እየቀረቡ ሲሆን የወቅቱን የአጥር ግንባታ በወንድም ኻሊድ የራስ ተነሳሽነት መጀመሩን አስታውቀዋል።
ስለአጥር ግንባታው ወንድም ኻሊድ በበኩሉ የአጥር ግንባታውን እየሠሩ ያሉት ባለሙያዎች በርሱ ፋወንዴሽን ከጎዳና ተነስተው የሰለጠኑ መሆናቸውንና እስከ 1.7 ሚሊየን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን 1.2 ሚሊየኑ በወንድም ኻሊድ ፋውንዴሽን የሚሸፈን ሆኖ ቀሪው 500ሺ ብር የነጃት ቤተሰቦች ኑራ ፍሬሽ መሸፈኑም ተወስቷል።
260 views15:35