Get Mystery Box with random crypto!

የሳዑዲ ኤንባሲና የኢትዮጰያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ | ጄይሉ ቲቪ // Jeilu Tv

የሳዑዲ ኤንባሲና የኢትዮጰያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አደረጉ።

የሳኡዲ ኤምባሲ አምባሳደር ዶ/ር ፈአድ ቢን ኡበይዲላሂ አል ሁሜይዳኒ ፤ ከኢትዮጰያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ፣ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝደንት ሽይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ እንዲሁም ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ በሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ በመገኘት የውይይትና የትውውቅ ፕሮግራም አከናውነዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጋራና በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር በተካሄደበት ፕሮግራም የሳኡዲ መንግስት ለሀገራችን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማገዝ ለሚያከናውነው ድጋፍ እንዲሁም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚያበረክተው አስተዋፅኦ ምስጋና የቀረበ ሲሆን ይህንን በጎ ተግባር በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል መሰራት እንዳለበት የውይይቱ አንኳር ነጥብ ሆኗል።