Get Mystery Box with random crypto!

#ቃል #ዳንኤላ_ስቴል ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ ምዕራፍ አስራ አምስት (15) «ፒተርን ማፍቀር | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

#ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ አምስት (15)

«ፒተርን ማፍቀር እየጀመርሽ ይመስልሻል !»
«አይ ! አይመስለኝም ። ፒተርን እንዳባቴ ነው እማየው። አየሽ እንደማላውቀው አባቴ ። ስጦታ ሲሰጠኝ ሲያሞላቅቀኝ አባቴ ነው እሚመስለኝ ። ፍቅር ከማይክል ጋር ነው»
«እሱንም ስንቆይ እናያለን» አለችና ፌ አሊሰን ሰዓቷን አየች ። «ያምላክ ያለህ |! ስንት ሰዓት እንደሆነ ታውቂያለሽ ? » አለች ። ናንሲ ሰዓቷን አየች ። በጊዜው ያን ያህል መክነፍ በጣም ተደነቀች ። « ፒተር እንዳለው እውነትም የምትገርሚ ልዩ ዓይነት ሰው ነሽ ! ምን አድርገሸ ነው እንዲህ ጊዜውን ያስረሳሽኝ ፌ? እውነትም ልዩ ሰው ነሽ!»
«በመስማማታችን ደስ ይለኛል ። እንዲያውም ፒተር በተወሰነ ጊዜ ዘወትር መገናኘት እንዳለብን ነው የሚያስበው ምን ይመሰልሻል ናንሲ?»
«በጣም ደስ ይለኛል»
«ግን በየጊዜው ይህን ያህል አብረን ልንቆይ እንችላለን ማለት አይቻልም ። ጊዜ ላይኖረን ይችላል ። ስለዚህ በሳምንት ሦስት ቀን ብንገናኝ ምን ይመስልሻል ? በተረፈ ግን እንደጓደኛ በትርፍ ጊዜ መገናኘት ይቻላል። ይስማማሻል? »
«በጣም በጣም ይስማማኛል» ተጨባብጠው እንደተለያዩ ናንሲ ከሁለት ቀን በኋላ ሊገናኙ የወሰዱት ቀጠሮ ሩቅ መስሎ ታያት የራሷ ስሜት ራሷን አስገረማት ።

••••••••••••••

ናንሲ በክፍል ማሞቂያው ምድጃ አጠገብ በሚገኝ ምቹ ወንበረር ላይ ተዝናንታ ተቀመጠችና በረጅሙ እየተነፈሰች ራሷን ወንበሩ የራሰ መከዳ ላይ አሳረፈች ። ከፌ ጋር ባደረጉት ቀጠሮ መስረት፣ ነበር የመጣችው ። የቀጠሮው ሰዓት ገና አምስት ደቂቃ ያህል ቢቀረውም እሷ ግን ከዚያች ሴት ጋር ለመጨዋወት ቸኩላለች ። ወዲያው እሌላኛው ክፍል ውስጥ ቀጭ፣፤ ቋ የሚለው የፌ ኮቴ ተሰማት ። ናንሲ የተቀመጠችው ፌ የአዕምሮ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በምታነጋግርበት በምትመረምርበትና ህክምና በምታደርግበት ክፍል ነበር ። የፌን ኮቴ እንደሰማች በደስታ ፈገግ ብላ ትስተካክላ ተቀመጠች ። ሁሉም ነገር ፌ እንደለመደችውና እንደምትፈልገው እንዲሆንላት ለማድረግ አስባበታለች ።
« እንደምን አደርሽ ፤ የንጋት ወፍ ። ይኸ ቀይ ልብስ እንዴት አድርጎ ተስማምቶሻል እባክሽ !» ፌ ይህን ብላ እበሩ ላይ እንደቆመች ፈገግ አለች ። ቀጥላም «ቀዩን ውብ ልብስ እንተወውና እስኪ አዲሱን ፊትሽን አሳይኝ » አለች ። ይህን ብላ ናንሲ ወዳለችበት ቀስ እያለች ተጠጋች ። ከፋሻ የተገለጠውን ፤ ከፊት አጥንቷ በታች የሚገኘውን ጉንጫን ካየች በኋላ እንኳን ደስ አለን የሚል ፈገግታ እፊቷ ላይ ነጋ። አይኖቻቸው ግጥምጥም አሉ ።
« እንዴት ነው ? ጥሩ ነው ? » እለች ናንሲ።
«ናንሲ ፤ በጣም ቆንጅዬ ልጅ ሆንሽኮ ። ቆንጅዬ… በቃ አለች ፌ። ናንሲ እመነቻት ። ምክንያቱም የፌ ፊት በናንሲ መዳን ደስ መሰኘቷን ፤ በፒተር ስራ መደነቋን ቁልጭ እድርጉ ይናገር ነበር ።

ፌ ደግሞ እንዲያ ስትል ከልቧ ነበር ። ለግላጋ አንገቷ ከቅርጸ መልካም ትከሻዋ ላይ እንደ ባህር ሸንበቆ ተመዞ ፤ ልስልስ ጉንጯ ፤ ገርና ሳሙኝ የሚል አፏ ተገልጦ ያየ ሰው ቢደነቅ የማያስገርም ነገር ሊሆን እይችልም ። ሁሉም ከናንሲ የተፈጥሮ ጠባይ ጋር የሰመረ አካል ሆኖ ታያት ፤ ለፌ ። የፒትር ሁልቆ መስፈርት የሌለው የንድፍና የጥገና ፤ የሞዴል መቅረፅ ሥራ ፤በከንቱ እንዳልነበረ ግልፅ ሆኖ የታያት ፌ

« አስቀናሽን ፣ ዕውነት ቀናሁ ። እኔም እንዳንች ብሆን እንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰለሽ ! » አለች ። ይህን የሰማችው ናንሲ በሳቅ እየተፍለቀለቀች ወደ ኋላዋ ተለጠጠች ። ከጉንጪ በላይ ያለው ፊቷ ገና በፋሻ እንደታሰረ ሲሆን ፤ ባደረገችው ጥቁር ቡናማ ዘናጭ ባርኔጣ ጥላ ደብዘዝ ብሏል ። ይህን ባርኔጣ የገዛችው ከአሥራ አምስት ቀን በፊት ሲሆን በቀይ ቀሚስ ላይ ከሰበሰችው ቡና ዓይነት ሱፍ ኮትና ካደረገችው ቡናማ ቡት ጫማ ጋር ይሄዳል ። ናንሲ ድሮም ቅርጸ መልካም ልጅ ነች ። አዲሱ ፊቷ ሲጨመር ወንድን ሁሉ በያለበት የምትጥል ሴት ትሆናለች ስትል አሰበች ፤ ፌ ናንሲም ቢሆን ይህ ሊሰማት ጀምሯል ። ፒተር ቃሉን ለመጠበቅ የሚችል ሰው እንደሆነ አምናለችና ።

« ፌ በጣም ደስ ይለኛል ። አንዳንድ ጊዜማ ደስታ የሰራ አካላቴን ውጥር እስኪል ስለሚሞላው ጩሂ ! ጩሂና እፎጥ በይ ይለኛል » አለች ናንሲ።
«እንደሱ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል ስላልሺኝ ደስ አለኝ ናንሲ ። ግን ይኽ ሌላ መሆኑስ ? ያልለመድሽው ገፅታ መሆኑስ ፣ ትንሽ አያስጨንቅሽም ?»
« የለም የፈራሁትን ያህል እይደለም ። ግን ሙሉ ፊቴን ስላላየሁት ሙሉውን ሳይ ምን እንደሚሰማኝ እንጃ ብቻ አየሽ ዱሮውንም ያን የአፌን ቅርፅ አልወደውም ነበር ብቻ ሲሆን ይታያል »
«ናንሲ… አንድ ነገር አለ››
« ምን? ምን ነገር»
« አየሽ ናንሲነትሽን ቀስ በቅስ እንድትረሺ ያስፈልጋል ግድ የለበትም ። አንች እንደተቻለሽ ። ስለዚህ ናንሲን ለመርሳት ናንሲን በደንብ ማስታወስ ያሻ ይሆናል ። ለምሳሌ እንበል የዱሮ አካሄድሽን ትወጂው ነበር ? » ይህ ነገር ለናንሲ ፈፅሞ አዲስ ነበር ፤ ተነስቶ ተወሰቶ የማያውቅ ።

« እኔ እንጃ ፣ ስላረማመዴ አስቤ እማውቅ ኢይመስለኝም » አለች ።« ለወያፊቱ በደንብ ታስቢበታለሽ። ድምፅሽን መስማት ትወጂ ነበር ? ለምሳሌ ድምፅሽን ለመገራት የዜማ አለማማጅ ቢቀጠርልሽ ምን ትያለሽ ? አየሽ በጣም ቆንጆ ድምፅ አለሽኮ ። ለምን መሰለሽ እንዲህ እምልሽ ? ከዚህ በፊት ያልሆንሽው ግን ልትሆኝው የምትችይውን ነገር እንድትለማመጅ ብናደርግስ ለማለት ነው ። ያን ስትሆኝ ያው አዲስ ሰው ሆንሽ ማለት ነውኮ ። ፒተር የተቻለውን እያደረገ ነው ። እኛስ ለምን አንሞክርም ? »