ሃሳቡ ቦግ ብሎ የታያትን ያህል በደስታ በራች፤ ናንሲ ። ‹‹ማለት ፒያኖ ብለማመድ ፤ አካሄዴን ብቅይር፣፤ አዲስ ሰዉ ሌላ ሰው ሆንኩ ማለት ነው ፤ አደል ? ከዚያ በኋላ እኮ ብፈልግ ስሜንም መቀየር እችላለሁ ?! » አለች ናንሲ ። «ያን ያህልም መቻኮል የለብንም ስም እስከመለወጥ ማለቴ ነው ። አንደኛሽን ራስሸን ያጣሽ መስሎ እንዲሰማሽ አያስፈልግም ። ራስሽን ማጣትሽ ሳይሆን መጨመርሽ ፤ ማደግሽ መሆኑን ማወቅ አለብሽ ። እስኪ እናስብበትና እንሞክረው ። ድንቅ ነገር ሳይገጥመን አይቅርም » አለች የአዕምሮ ህክምና ሊቋ ፌ « « በመጀመሪያ ድምፄን… ሌላ ድምፅ እፈልጋለሁ» አለች ናንሲ እየሳቀች ። « እንደዚህ ዓይነት ድምፅ » አለች ድምጸን ቀነስ ወፈር አድርጋ ። ፌ ሳቀችእና « እሱን ድምፅ በደንብ ከተለማመድሽው ፒተር ሥራ ሊበዛበት ነው ማለት ነው » አለች። «እንዴት? » አለች ናንሲ በዚያው ጐርነን ባለው ድምፅ። «ጺም መሥራት ግድ ይሆንበታላ !» « እንዲህ ነው ። እንኳን ነገርሺኝ !» ሁለቱም አንዴ በሳቅ መንከትከት ጀመሩ ። ተነስታ እንደትንሽ ልጅ መቅበጥበጥ ጀመረች ። ናንሲን እንዲያ ስትሆን ስታያት ፌ ሁልጊዜም ይገርማታል ። ሀያ ሶስት አመቷ ነው ። ናንሲ ግን ሃያ ሶስት ዘመን ቀርቶ ረጅም ዘመን የኖረም ሰው ቢሆን ያላየውን ብዙ ነገር እያየች ነው፡፡ እየሆነች ነው ። ውስጧ ግን ትንሽ ልጅ ናት ። ይኸው ስትቀብጥ ስትቅበጠበጥ ! « ግን አንድ ነገር አለ ፤ ናንሲ›› « ምን ነገር ?» «ለምን ኦዲስ አንችን መፍጠር እንዳለብን ማወቅ አለብሽ ። ምክንያቱን ካወቅሽው ፤ ችግሩን ከተረዳሽው ነገሩ ቀላል ይሆናል ። እናትና አባትሽን አታውቂያቸውም ፤ እደለም ? ይኽ ደግሞ ምን እንደሚያስከትል ማወቅ አለብሽ ። እናትና አባት እኛ ራሳችንን ለመሆናችን ምስክር ናቸው ። ከየት መጣሁ ? እናትና አባቴ ወለዱኝ ። እውን ይሆናል ነገሩ ። ያ ጥያቄ ላንች ክፍት ቦታ ቢጤ ነው ። እሱን የምትሸሺ መምሰል የለበትም ። ሌላ ሰው ልችሆኝ እንደምትፈልጊ መሆን ነው ያለበት ። ያኔ መንገዱ ቀላል ይሆናል » አለች ፌ ። ናንሲ ምንም ምን ሳትል ጸጥ ብላ ተቀመጠች ። ይህን ያየችው ፌ በፍቅር ፈገግ ብላ ከተመለከተቻት በኋላ ወደኋላዋ ተለጥጣ ተዝናንታ ተቀመጠች። ክፍሉ ምቾት የሚሰጥና መከፋትን ባንድ ጊዜ ከአዕምሮ ውስጥ እንደሚደመስስ ሆኖ የተዘጋጀ ይመስላል ። የግድግዳው ቀለም ፣ የዕቃዎቹ ዓይነት ፤ የዕቃዎቹ አቀማመጥ፤ ሁሉ ነገር የመንፈስ ሰላም የሚለግስ ነው ። « እሺ እንግዲህ አሁን ያልኩሽን ቀስ እያልሽ አስቢበት። ለጊዜው ሌላ ነገር አለ ፤ ልንነጋገርበት የሚገባ። የእረፍት ጉዳይ፤ ያመትባል ጉዳይ » « የመጪው አመትባል ምን እንዲሆን ? » «ዘመን መለወጫ መምጣቱን ስታስቢ ምን ይሰማሻል ? ይጨንቅሻል ? ፍርሃት ፍርሃት ይልሻል ?›› «አይለኝም» «ይከፋሻል ? » ‹‹በፍጹም » «ደግ ናንሲ ። እኔ ከምገምትና ብዙ ከምሳሳት የሚሰማሽን አንች ብትነግሪኝስ ?» «ምን እንደሚሰማኝ ለማወቅ ነው እምትፈልጊው ?» አለች፡፡ « በእርግጥ ማወቅ ትፈልጊያለሽ ?» ከተቀመጠችበት ተነሥታ እንዴ በክፍሉ ውስጥ በፍጥነት ወዲያ ደርሳ ወዲህ ከተመለሰች በኋላ ፣ «ምን እንደተሰማኝ ልንገርሽ ? » አለች «የተጣልኩ ፤እንደሽንት ተከፍዬ የተደፋሁ ይመስለኛል ፤ ስለዚህ ብሽቅ እላለሁ » «እንደሽንት ? » «አዎ ! ሽንቶ የደፋኝ መስሎ ይሰማኛል ፤ አናዶኛል ፤ አበሳጭቶኛል ፤ አብግኖኛል » «ማን?›› «ማይክል….. ይቀጥላል...... ሀሳብ አስተያየታችሁን @Tsiyon_awit አድርሱኝ ቻናላችንን ይቀላቀሉ @itsmetsiyearsemalj @itsmetsiyearsemalj 308 viewsTsi , 18:28