ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዴት እንደተነሳ ሳታውቅ ስለ ማሪዮን ሂልያርድ ታጫውታት ጀመር ። ፌ አሊስን ይህን ሁሉ የምታዳምጣት በጽሞና ነበር ፤ መገረም የለ፤መጨነቅ የለ ። በጽሞና ፤ «እኔንጃ ፤ ብቻ ስናገረው እንኳ ለራሴም እንግዳ መሆኑ ይታወቀኛል ። ግን…» አለችና ንግግሯን መቀጠል ተሳናት። ለምን ? ቂል የሆነች፤ ልጅ የሆነች መስሎ ተሰማት ። እና በጽሞና እምታዳምጠውን አዲስ ጓደኛዋን ቀና ብላ አይታ ለመቀጠል ሞከረች ። «ግን እየሽ እኔ . . . እንዳልኩሽ ያላባትና ያለናት ስላደግኩ» አሁን አፏ ፈታ እያለ ሄደ ። «ምንም ዘመድ አዝማድ የሚባል ነገር ኖሮኝ አያውቅም ነበር ። እናት ወደሚባለው ነገር ቀረብ ልትል የምትችለው ያው የሕፃናት ማሳደጊያው ዋና ነበረች ። አበምኔቷ ። እሷም ያው እንዶ እናት ሳይሆን ምናልባት እንደ ጋለሞታ አክስት ብትቆጠር ነው ። ስለማሪዮን ግን ያው መቼም ማይክልም ፤ ቤን የሚባለው የሱ ጓደኛም ሆነ ብለው ከነገሩኝ ወይም ድንገት ከምሰማው ብዙ ነገር እየሰማሁም ይህ ሁሉ እያለ ፤ ብንገናኝ ትወደኝ ነበር ፤ በተገናኘን ብቻ ! የሚለዉ ጅል ሐሳብ ልበልሽ ቅዝት ወይስ ሕልም ሁልጊዜ ይታየኝ ነበር ። መቼም ቢሆን ፤ ማሪዮንና እኔ ስምም ሆነን እንኖራለን የሚለውን ሐሳብ አምንበት ነበር» ድንገት ዓይኗ ላይ እንባ ግጥም አለ ። ላለማልቀስ እየታገ ለች ፊቷን ወደ ሌላ አዞረች ። «ምናልባትም እናቴ ትሆናለች ፤ ማለት እንደ እናት ትሆነ ኛለች ብለሽ ታስቢ ነበር ?» ናንሲ በአዎንታ ራቧሷን ነቀነቀች ። «እብደት አይደለም ይኸ ታዲያ ? » «በፍጹም ። በፍጹም እብደት አይደለም ። ያለ ነገር ነው። ያለ እናት አደግሽ ።ማይክልን ወደድሽ ። የማይክልን እናት እንደ እናትሽ ለማየት ፤እናትሽ ለማድረግ ተመኘሽ። ያለ ነው። ምናልባት በዚህ ምክንያት ይሆን ፤ በመጨረሻ በውል መልክ ስትስማሙ በማሪዮን በጣም የተማረርሽባት ፤ አንችንም በጣም የከፋሽ ?» «አዎ ። አየሽ እንዲያ ባለ ሁኔታ ቃል ስታስገባኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ምን ያህል እንደምትጠላኝ አረጋገጠችልኝ» «እኔ ደሞ እንዲያ አይመስለኝም ። የሆነ ነገር ያላት ይመስለኛል ። ያ ባይሆን ይህን ሁሉ ነገር አታደርግልሽም ነበር ።ያ ሁሉ ገንዘብ ከፍላ አካልሽ እንዲመለስ ማድረጓ በጣም ስለምትጠላሽ አይመስለኝም» ይህን ሁሉ ምቾት ትተን አለች በልቧ ፌ አሊሰን ። «ግን ውሉን አስቢው። ይህን ሁሉ ያደረገችልኝ እኮ ማይክልን እንድተውላት ነው ። ከማይክል ጋር ግንኙነት ብፈጥር… እኔ ፈልጌ ዉሉ ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል፡፡ ተቀብለሽ ከሱም ፊት ከኔም ፊት ጥፊ እንደማለት ነዉ ያኔ ስታነጋግረኝ ገባኝ ። ማሪዮን መቼም ቢሆን ልትቀበለኝ አትፈልግም ፤ ብዬ አሰብኩ ። ይህ ሐሳብ እንደተሰማኝ የሆንኩትን ልነግርሽ አልችልም ። በሕይወቴ ውስጥ ካጋጠሙኝ አስከፊ ነገሮች አንዱ ነበር» ይህን ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ። እንደገና መናገር ስትጀምር ድምጺ ለስለስ ብሎ ነበር ። «ግን ችግርም ፣ ስቃይም መከፋትም ለኔ ኦዲስ አይደሉም ። ደጋግመው ደርሰውብኝ ደጋግሜ አሳልፌአቸዋለሁ» «ወላጆችሽ ሲሞቱ ነፍስ ታውቂ ነበር ?» «ይህን ያህል የጐላ ትዝታ የለኝም» የምታስታውሰውን ያህል ነገረቻት ። ቀጥላም ፤ «ትዝ የሚለኝ የሚመስለኝ ምናልባት ብቻን መቅረት አለ አይደል እንደዚያ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር መሰለኝ» አለች ። «ልክ አሁን እንደሚሰማሽ ዓይነት ስሜት?» ግምት ነበር ። ቢሆንም ባዶ ግምትም አልነበረም። «ምናልባት ሳይሆን አይቀርም ። የት እገባ ብሎ ማሰብ ። ልክ ሳይሆን አይቀርም ። ከዚህ በኋላ የት ነው እምገባ ? ማነው አይዞሽ የሚለኝ ? የሚል ስጋት ። አሁንም አልፎ አልፎ የዚህ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል» «ምናልባት ማይክል ? ማይክል ይፈልገኛል ፤ አይጥለኝም ብለሽ ትገግምቻልሽ ? » «አዎ ፡፤ አንዳንዴ እንደሱ አስባለሁ። የለም አንዳንዴ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ።» «በሌላ ጊዜስ ? ማለት ሁሌም አላልሽም» «እሁን አሁን መጠራጠር ጀምሬአለሁ ። በፈት በፊት አየሽ ሳይመጣ ሲቀር ጊዜ ፊቴን ማየት ፈርቶ ነው ፤ ተሳቆ ነው እል ነበር ። አሁን አሁን ግን ስለሕክምናው ያውቃል ። ስለዚህ ምን ደረሰች ፤ እንዴት ነው ብሎ መጠየቅ ነበረበት ። ታዲያ እንዴት እንዲህ እልም ሊል በቃ ? እላለሁ» «የግምት መልስ ሰጥተሽዋል ለጥያቄሽ ? » «አዎ ። ግን በቂ መልስ የምትይው አይደለም ። አንዳንዴ ማሪዮን ያሳመነችው ይመስለኛል ። የሱ ዓይነቱን መልካም ስም ከሌለው ቤተሰብ የወጣች ሴት ጋር ማጋባት ለሙያህ ደግ አይደለም ብላ አሳምናው ይሆን እላለሁ ። ማሪዮን ቀላል ሰው እንዳትመስልሽ !» «እሱ እንዲህ ዓይነቱን ሐሳብ ይቀበላል ትያለሽ ? » «በፊት እንኳ ርግጠኛ ነኝ አይቀበልም ። አያምንበትም ፤ ነበር ... አሁን ግን እንጃ፤ምን ይታወቃል?» «ሌላ ቢያገባ... ቢተውሽ ምን ያህል የምትጐጂ ይመስልሻል?» ናንሲ ኩምትር ስትል ታየች ። መልስ አልሰጠችም ። ግን መላ አካሏ መልሱን ሰጥቷል ። «የሆንሽውን ሲሰማ ደንግጦ ወይም እንዲያ ሆና ላያት አልፈልግም ብሎ እንደሆነስ ያልመጣው ? አየሽ ናንሲ ፤ አንዳንድ ወንዶች እኛ የምንፈልገውን ያህል ጠንካሮች አይደሉም» « ይሆን ይሆናል » «ታዲያ. . . በኋላ ከዳንሽ ከተስተካከልሽ በኋላ ቢመጣ ቅር አትሰኝበትም ?›› «ምናልባት ቅር ይለኝ ይሆናል ። ምኑም ግልጽ ሆኖ አይታወቀኝም ። አስባለሁ ፤ አስባለሁ ። ግን መልስ የለም» «መልሱን መፈለግም አያሻም ። መቆየት ይመልሰዋል ጊዜ ይመልሰዋል ። ዋናው ነገር ግን ስሜትሽን መሸሽ የለብሽም ። ስሜትሽን በትክክል ለመረዳት መሞከር አለብሽ በቂ ነው ።ለመሆኑ ስላንቺ የሚሰማሽ ምንድነው ? ማለት ፊትሽ እንግዳ ነው እንግዳ ነሽ ለራስሽም ። ይህን ስታስቢ ትቅበጠበጫለሽ ? ትፈሪያለሽ ? ትደሰቻለሽ ? ትናደጃለሽ ?» «ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ» አለች ። ሁለቱም ሳቁ «ግን አብዛኛውን ጊዜ በጣም እፈራለሁ ፤ እጨነቃለሁ ። አብሮ የኖረ ነነር ቀላል አይደለም ። ሀያ ሁለት ዓመት ሙሉ እኔ ያልኩት ሌላ ሲሆን አስቢው ፤ አያበሳጭም ብለሽ ነው?» «እንዲያ ዓይነት ስሜት ተሰምቶሽ ያውቃል?» «አንዳንዴ. . . ግን አብዛኛውን ጊዜ ደፍሬ አላስብም ስለዚህ ጉዳይ» «ብዙ ጊዜ እምታስቢው ስለምንድነው ?›› «እውነት ንገሪኝ ነው እምትይኝ ? » «አዎና» ‹‹ማይክልን ። አንዳንድ ጊዜ ፒተር በሐሳቤ ይገባል ። አብዛኛውን ጊዜ ግን ስለማይክል ነው እማስበው» «ፒተርን ማፍቀር እየጀመርሽ ይመስልሻል !» ይቀጥላል...... ሀሳብ አስተያየታችሁን @Tsiyon_awit አድርሱኝ ቻናላችንን ይቀላቀሉ @itsmetsiyearsemalj @itsmetsiyearsemalj 710 viewsTsi , 17:45