Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ከበድ ያለና የተጠቀለለ አራት ማዕዘን ነገር ይዞ መጣ ። ገና ስታየው መፈንደቋ ጨመረ ። ምን | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

አንድ ከበድ ያለና የተጠቀለለ አራት ማዕዘን ነገር ይዞ መጣ ። ገና ስታየው መፈንደቋ ጨመረ ። ምን ይሆን ? ትልቅ ነገር መሆን አለበት ። ጭኗ ላይ አስቀመጠላት ። ልክ ነው የገመትኩት ፡ ልክ ነው ! ስትል አሰበች ። «ምንድነው ፒተር ? የሆነ እንደ ድንጋይ የሚከብድ ነገር» አለች ። «እንደ ድንጋይ አልሺኝ ? አልተሳሳትሽም ። በየሱቁ ዞሬ በገበያ ላይ ያገኘሁትን የመጨረሻውን ትልቅ የከበረ ድንጋይ ነው ገዝቼ ያመጣሁልሽ» አላት ። ይህን ነበር የገመተችው ። ፈታችው ። ከገመተችው ፤ ካሰበችው ውጭ ነበር የዛሬው ስጦታ ።« ሆኖም ልክ ነው።ካሰበችውም የሚበልጥ ታላቅ ስጦታ ሆኖ አገኘችው ። «ፒተር ! አምላኬ ፤ ምን ዓይነት ስጦታ ነው ይሄ ? በፍጹም ልቀበልህ አል...»
« ትችያለሽ እንጂ ! መቀበል አለብሽ ። ሆኖም ይሀን ስጦታ በነፃ ልሰጥሽ አልፈልግም ። ብዙ ስራ ፤ ቆንጆ ሥራ ሠርተሽ እንድታሳይኝ እፈልጋለሁ » ካሜራ ነበር ስጦታው ። ፤ ይህ ደግሞ ቀላል ነገር አልነበረም ። ፒተር ይህን ስጦታ ብዙ አስቦበት ፤አውጥቶ አውርዶ ነበር የገዛው። ምክንያቱ ለፒተርም ለናንሲም ግልጽ ነው ። ። እንግዲህ ናንሲ የስዕል ሥራዋን እንደገና ለመጀመር ሐሳቧ እምቢ እንዳላት ሁለቱም ያውቃሉ ። ሥዕል ሞክሪ ስትባል በመጀመሪያ በእጅዋ ስታመካኝ ቆየች ። አሁን የእጅዋ ሕክምና ሲያልቅና ሲፈታ ምን ምክንያት ልትፈጥር ትችላለች ? ለናንሲ ይህ ጭንቅ ነበር ። ለፒተር ደግሞ መፍትሔ የሚፈለግለት ጉዳይ ነበር ። መፍትሔ ይኸው ካሜራ ። ሥዕል ለመሳል ስላልፈለገች ፤ ነርሶች ያመጡአቸው የዱሮ ሥዕሎቿ እንኳ ለጉዞ እንደተቀረቀቡ ናቸው ። ልታያቸው አልፈለገችም ። አሁን በቃ ። ፎቶግራፍ ታነሳለች ።

«በነገራችን ላይ ካሜራው መመሪያ አለው ። እኔ ላነበው ብሞክር ምኑም አልገባህ አለኝ ። ከዚህ ካሜራ አሠራር ይልቅ የሕክምና ሙያ ትምህርት ቀለል ሳይል አይቀርም ። ላንቺ ግን ይገባሻል ብዬ ነው » አለና ሰጣት ። ተቀበለችውና ገልበጥ ገልበጥ አደረገችው። ላንድ ካሜራ ይህን ያህል መመሪያ ! ካሜራው በጣም የተራቀቀ መሆን አለበት። ገልበጥ ፤ ገልበጥ ። ትንሽ አነበበች ። ተመሰጠች ። በኋላ ማስረዳት ቀጠለትች ካሜራውን ይዛ ። «አየህ… እየው ፤ እዚህ ላይ ጠቅ ስታደርገው. . . ይታይሃል ? » እያለች ፤ «ይህን ስተነካው ደሞ...» እያለች ። «ታዲያ ይህ ስጦታ በሕይወቴ ከተሰጡኝ ስጦታዎች ሁሉ የላቀና ያማረ ነው» አለች ። ሆኖም ማይክል እባዛሩ ላይ አሸንፎ ከሰጠኝ ያንገት ጌጥ ሌላ ብላ በልቧ ጨመረች ። ይህን ሐሳብ ግን ልትገፋበት አልደፈረችም ። ይህ ሀሳብ በፊቷ ላይ ሲዳምን ፒተር አይቷል ። ብዙ ጊዜ ይጠብቀዋል ። እንድ የተጐዳችበት ነገር . . . ያለፈ ሕይወቷ ቁስል...

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj