Get Mystery Box with random crypto!

«እቢሮ ጠረጴዛህ ላይ ስጦታ ቢጤ አስቀምጩልሀለሁ» ስትለው፤ « አስፈላጊ አልነበረም » አለ ። ከል | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

«እቢሮ ጠረጴዛህ ላይ ስጦታ ቢጤ አስቀምጩልሀለሁ» ስትለው፤ « አስፈላጊ አልነበረም » አለ ። ከልቡ ነበር ። ካሁን በኋላ ለሱ ምንም ምን ነገር አያስፈልገውም ። ልቡን ሊያፈካ የሚችል ምንም ዓይነት ስጦታ አይኖርም ። ቤን ይህን ተረድቶለታል ። ስለዚህም የልደት ስጦታ አልገዛለትም ። «ለኔ የልደት ቀንሀ ነው ማይክል። የሆነውም ቢሆን ላንተ የተወለድክበት ቀን ልዩ መሆኑን አትዘንጋ። በል መሥሪያ ቤት እንገናኝ » ብላ ወጣች ።

እናቱ ወደ ሥራ ከሔደች በኋላ እዚያው ምግብ ቤት ተቀምጦ ለረጅም ጊዜ ቆየ ። የውጭውን ትዕይንት እየተመለከተ

የሱ መኖሪያ ሌላ ነው ። መኖሪያውን በሚገባ ያውቀዋል ግን ያ አፓርታማ የሚገኘው ቦስተን ውስጥ ነው። ቢሆንም የተቻለውን ያህል ይፈልጋል ተመሳሳዩን እስኪያገኝ ። ዛሬም ልቡ አላመነም ። ዛሬም ተስፋ ያደርጋል ። ምንም እንኳ ከንቱ ተስፋ የሞኝ ተስፋ ቢሆንም ውስጡ ግን አልቆረጠም ።

«ሃይ፤ ሱ! ሚስተር ሄልያርድ አለ›› ቤን እቭሪ እማይክል ቢሮ ሲገባ ደስ ብሎት ነበር። አሰልቺው የስራ ሰዓት ወደ መገባደዱ ትቃርቦ ስለነበር ደስ ብሎታል ። ቀኑን በሙሉ ወዲያ ወዲህ ሲዋከብ ነው የሚውለው ። ማረፍ ቀርቶ ቂጡ መሬት ሊነካ የሚችልበት ጊዜ የለውም ። «አዎ ፣ ልታነጋግረው እንደምትፈልግ ልንገረው ? » አለች ሱ ፈግግ እያለች ።

በአለባበስ የተሸፈነው መልካም ቅርጽ አይኑን ሳበው። ማሪዮን ሂሊያርድ ሽቅርቅር ነኝ ባይ ፀሐፊዎችን አትቀበልም ፤ ለሌላ ሠራትኛ ቀርቶ ለልጅዋ እንኳን አለ በሃሳቡ ። ቀጥሎም ወይስ በተለይ ለልጅዋ ይሆን? ቤን ይህን ኢያሰበ «ልንገረው ?» ላለችው እንገቱን በአሉታ እየነቀነቀ «የለም ። አንችን ማድከምም አያስፈልግም ። እኔው ዝም ብዬ እገባለሁ» አላት ። የማይክልን ቢሮ በር አንኳኳ ። «እዚህ ቤት ! ሰው የለም ?» አለ እንደቀልድ ። ምንም መልስ አልነበረም ። እንደገና አንኳኳ ። አሁንም መልስ እልነበረም ።«ርግጠኛ ነሽ… ውስጥ አለ » እለ ቤን ፀሐፊዋን ዞር ብሎ እየተመለከተ ።
«እርግጠኛ ነኝ» ፤
«ነው?» አለና እንደገና አንኳኳ ። በዚህ ጊዜ የሻከረ ድምፅ «ይግቡ» አለ ከውሰጥ ። ቤን በሩን ቆስ ብሎ ገፋ አድርጐ ገባ ።
«ምን ሆንክ ? ተኝተህ ነበር ወይስ ምን ? » ማይክል ቀና ብሎ እየውና ፣ «ያማ መታደል ነበር ። መተኛት ፅድቅ አይደለም እንዴ እስቲ ይኽን ጉድ ተመልከትልኝ» አለ ። ጠረጴዛው ላይ የተከመረው ፋይል ብዛት መጠን አልነበረውም ። ያን ሁሉ ስራ የተመለከተው ቤን በልቡ ይህን ስራ ለማጠናቀቅ አስር ሰዎች ዓመት ይፈጅባቸዋል ሲል አሰበ። «ተቀመጣ ፤ ቤን» አለ ማይክል ።
«እሺ አመሰግናለሁ ፤ አለቃዬ» አለ ቤን ። ሁሌም እንደዚህ እያለ ያሾፍበታል ።
«ዝጋ እንግዲህ ! ደሞ ምንድነው የተሸከምከው ? አንተም ሌላ ተጨማሪ ስራ ይዘህብኝ መጣህ ልበል ?» አለ ማይክል ። «ደሞ ሌላ ተጨማሪ ስራ በተለይ ስለዚያ ጣጠኛ የገበያ ማዕከልና ስለ ካንሳስ ስቲው ገበያ ይዘህብኝ መጥተህ እንዳይሆን ! ራሴን ሊያዞረኝ ምንም አልቀረውም ለራሱ »
«ግን ያን ያህል አልጠላኸውም ። እንዲያውም ትወደዋለህ ። ማይክ ፤ እስኪ ንገረኝ በመጨረሻ ያየኸው ፊልም ምንድነው? ዘ ብሪጅ ኦን ዘ-ሪቨር ክዌያ ወይስ ፋንታሲያ ? ለምንድንው ከዚህ ጐረኖህ አንዳንዴ ወጣ የማትለው?» አለ ቤን።

« እንግዲህ ፋታ ሳገኝ መሞከሬ አይቀርም » አለ ማይክ «በነገራችን ላይ የምን ፋይል ነው የያዝከው ?» «አትጨነቅ ። ማስመሰያ ነው ። ላጫውትህ ፈለኩና ይህን?! ተሸክሜ መጣሁ » «ዝም ብለህ ብትመጣ የሚከለክልህ ነገር አለ?» «አይ እንዲያው ነው ። አንዳንዴ እናትህ ስነስርዓት አጥባቂውን የትምህርት ቤት ሞግዚት እንዳልሆነች እየተረሳኝ…» «እሉን ባለመሆኗ እግዜር ምስጋና ይግባው....» ይበሉ እንጂ ሁለቱም ያውቃሉ ፣ማሪዮን ከዚያ ከሚያሙት ሞግዚት ብትብስ እንጂ እንደማትሻል ።

ከዚህ በኋላ ባለፈው የዓመት ፈቃዱን ስላሳለፈበት ሁኔታ ጠየቀው ማይክል ፤ ቤንን ። «ታስብልኛለህ አደለም ?» አለ ቤን። « ለምን አላስብልህሀም ? » «ልክ ነህ» አለ ቤን ትንሽ ካሰበ በኋላ ትክዝ ብሎ «አምንሃለሁ ፤ ለኔ ታስብልኛለህ ። ለራስህ ግን ግድ የለህም» ሁለቱም ዝም አሉ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj