Get Mystery Box with random crypto!

#ቃል #ዳንኤላ_ስቴል ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ ምዕራፍ አስራ ሁለት (12) «አረ?... እንዴ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

#ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ ሁለት (12)

«አረ?... እንዴት ልታውቂ ቻልሽ ? » ምክንያቱም አለች በልቧ ፣ ምክንያቱም ዛሬ የማይክል ልደት ነው ። ማይክል ዛሬ ልክ ሃያ አምስት ዓመት ይሆነዋል ። አሁን በዚህ ሰዓት ምን እያደረገ ይሆን?
ይህን በልቧ ብላ በአፏ ግን «እንዲሁ አውቀዋለሁ» አለችው ። «ደግ። ሆኖም መልሱ እላጠገበኝም። ስለዚህ እኔ ልንገርሽ። ይህ ቀን የተለየ ቀን የሚሆንበት ዋና ምክንያት የመጀመሪያ ቀን በመሆኑ ነው። የቀዶ ህክምና ሥራችን መጀመሪያ አንችን ለመፍጠር በምናደርገው አስደናቂ ጉዞ የመጀመሪያው ርምጃችን በመሆኑ ነው። ምን ይመስልሻል ?» ይሀን ብሎ ፈገግ አለ። ዓይኖቿ በእንቅልፍ ተሸበቡ የተወጋችው የእንቅልፍ መርፌ ሠራ ማለት ነው።

«መልካም ልደት አለቃዬ»
‹‹እንደሱ ብለህ አትጥራኝ አላልኩም ፤ አንተ ወፈፌ። የክርስቶስ ያለህ። ምን መሰልክ ቤን? ለማኝ»
«አመሰግናለሁ ስለመልካም አስተያየትህ» አለ ቤን አቭሪ። ይህን ብሎ አንዲት ፀሐፊ ደግፋው በክራንች እየተረዳ ወደ ማይክል ቢሮ ገባ። ፀሐፊዋ ደጋግፋ አስቀምጣው ወጣች።
«እንዴት ያለ ቆንጆ ቢሮ ሰጡህ እባከህ። የኔም እንደዚህ ያማረ ይሆን ይሆን?» አለ ቤን።
«ከፈለክ ይህን ራሱን መውሰድ ትችላለህ ። እኔን እንደሆነ ገና ሳይጀመር ስልችት ብሎኛል» አለ ማይክል።

‹‹እሱም የሚከፋ ሃሳብ አይደለም ። አዲስ ነገር ቢኖር...» አለ ቤን። ቤንና ማይክል ሁለት ጊዜ ያህል መገናኘታቸው ነው። ቤን ከቦስተን ወደ ኒውዮርክ ከመጣ ጀምሮ ገና ያላነሱት ነገር አለ። የሚሸሹት ነገር አለ። ሁለቱም ሊያነሱት ይፈልጋሉ። ግን ይሸሻሉ። ስለናንሲ ማውራት ሁለቱም ይፈልጋሉ። ሀዘናቸውን ሊወጡ ይሻሉ። ግን አልቻሉም ዳርዳር ማለት ብቻ።
«ሐኪሙ ከሣምንት በኋላ ማለት በሚቀጥለው ሳምንት ስራህን መጀመር ትችላለህ ብሎኛል» አለ ቤን አቭሪ፡፡ ማይክል ይህን ሲሰማ ስቆ ‹‹ቤን በቃኮ አለቀልህ… የወጣለት ጅል ሆንክ » እለ ።
« አንተሳ፤ ጤነኛ?»

«ነኝና ! » አለና ፊቱ ድንገት ቅጭም ብሎ ወዲያው ፈካ አለ ቢያንስ የሚታይ የተሰበረ ነገር የለም ብሎ። ከዚያም «ስንት ጊዜ ልንገርህ? ቢያንስ ሶስት ሳምንት ማረፍ ትችላለህ… ካሁን በኋላ
ነውኮ የምልህ ! አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ ከዚያ በላይ....» በደንብ ካየው በኋላ
«እንዲያውስ ለምን ወደ አውሮፓ አትሄዱም ፤ አንተና እህትህ?» አለው።
«ምን ልሠራ? በአካለ ስንኩል ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጩ የሴቶችን ኋላና የዋና ልብስ እያየሁ ልጎመዥ? ይልቅስ አሁን እውነቴን ነው ስራ መጀመር እፈልጋለሁ»
«ደግ! እንደሁኔታው እናደርጋለን» ሁለቱም ዝም አሉ ፤ድንገት። ከዚያም ማይክል ቀና ብሎ
ምርር ባለ አተያይ ቤንን ከተመለከተወ- በኋላ ፤ « ከዚያስ ?» አለው ። «ከዚያ ስትል ምን ማለትህ ነው ማይክል ?» አለ ቤን። «ከዚያስ ማለቴ ነዋ! ስራ ጀመርን። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደፊት ለሚመጣው ሃምሣ ዓመት ያህል ስንለፋ፣፤ ስንባዝን እንኖራለን ። ኖረንስ ምን እናደርጋለን ? ማለት የመልፋት የመባዘን ጥቅሙ ምንድነው? ሰራህ፤ ለፋህ፤ ተከበርክ… እና ምን ይጠበስ››
«ደህና ደህናውን እያሳሰበህ ነውና ጃል !ምን ነካህና እንዲህ ምርር አልህ? በጧቱ ጣትህን በር ቀረጠፈህ?»
«የለም ቤን ፤ ቀልድ ይቁም ። በስላሴ ፤ ላፍታ ያህል ቁም ነገር እንነጋገር። እና ምን ይጠበስ?!»
‹‹ምንም የማውቀው ነገር የለም ። እኔም አደጋው ከደረሰብን ጊዜ ጀምሮ የዚህ አይነቱ ሀሳብ፣ የዚህ አይነቱ ጥያቄ አእምሮዬን እየኮረኮረ ሲያስቸግረኝ ነው የሰነበተው።»

«ምን… ምን መልስ አገኘህለት?»
«እንጃ፤ ማይክ ። እንጃ ። ርግጠኛ አይደለሁም ። እንዲያውም መምጣቴ ደግ ሆነ መሰለኝ ። ምናልባት ሞትን ቀምሼ በመዳኔ ህይወትን ይበልጥ እንድወዳት እያደረገኝ ይሆናል» አለና ሀዘን ፊቱን ሲሰብረው ታዬ። ፀጥታ ሆነ። ሁለቱም ተዋጡ። ማይክል አይኑን ጨፈነ። ከዚያም ተነስቶ ወደ ቤን ሄደ ። እፊቱ ተንበረከከ ። ፊት ለፊት እየተያዩ አለቀሱ ። እንባቸው በፊታቸው ላይ ተረጨ። እጅ ለእጅ ተጨባብጥው እርስ በርስ ተፅናኑ ። የአስር ዓመት ጓደኝነት ፤ የአስር ዓመት ፅኑ መግባባት ፤ ፅኑ ፍቅር።
«አመሰግናለሁ ቤን ፤ እግዜር ይስጥልኝ » አለ ማይክል።
«ማይክ ስማ!» አለ ቤን እንባውን እየጠረገና ተንኮል እፊቱ ላይ እየነጋ ። «ስማ ፤ ዛሬ የልደት ቀንህ አይደለም? ለምን አንወጣምና አንቀማምስም ? » ማይክም ፈገግ አለና ቤንን አየው። ተስማማ፤ በአንገት እንቅስቃሴ ። ከዚያም ሰአቱን አዬ። «አስራ አንድ ሰዓት መሆኑ ነው ። ስብሰባም የለብኝም ።
እንሂድ» አለና ቤንን ደግፎ አነሳው ። ተደጋግፈው ወጡ ። ደግፎ መኪና ውስጥ አስገባው። ከግማሽ ሰአት በኋላ ወዶ ሞቅታ አለም በመጋለብ ላይ ነበሩ።

ጧት እንደምንም ብሎ ተነሳ ። ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነበር እቤቱ የደረሰው። ወደ መኝታ ክፍሉ ያስገባው ዘበኛ ነበር። ሰራተኛዋ ለቁርስ ስትቀሰቅሰው አልጋው ላይ አልነበረም ። እወለሉ ላይ ተኝቶ ነበር ያገኘችው ። እንደምንም ብሎ ወደ ምግብ ቤት ሄደ ። ማሪዮን ቀድማ ለባብሳ ጋዜጣ ስታነብ አገኛት ። ለቁርስ የቀረበውን ነገር ሲያይ አቅለሸለሸው ። ራሱን ይወቅረዋል ። «ትናንት እንዴት ነበር ? » አለች ማሪዮን ። «ከቤን ጋር ነበር ያመሸሁት » «አብራችሁ እንደወጣችሁማ ጸሐፊህ ነገረችኝ ። የዚህ ዓይነት ነገር ባይለምድብህ መልካም ነው ።» እኮ ለምን ? አለ በሀሳቡ ። «ምኑ ? መጠጣቱ ?»
«ሰዓት ከመድረሱ በፊት ቢሮ ጥሎ መውጣት ማለቴ ነበር ። መጠጣቱም ቢሆን በርታ የሚያሰኝ አይደለም ። ወደ ቤት ስትገባ አምሮብህ እንደገባህ ነው »

‹‹እንጃ ትዝ አይለኝም » አለ ፤ፉት ያለው ቡና ሽቅብ እየተናነቀቅው ። «ሌላ የዘነጋኸው ነገር ትናንት ለራት ጋብዤህ ነበር።ግን አልመጣህም ። እኔና ሌሎች እንግዶች አሥር ሆነን ስንጠብቅህ ነው ያመሸነው»
«አላወቅኩም ። ራት ጋብዤሀለሁ ስትይኝ ሁለታችን ብቻ የምንገና መስሎኝ ነበር »
« እና… እኔስ ብሆን ፤ እኔ መጠበቅ ነበረብኝ ?»
« እንደሱ ማለቴ ሳይሆን ዘነጋሁት ። ተረጂልኝ እንጂ ችግሬን ማሚ ። የትናንቱ የልደት በዓል ለኔ በአል አልነበረም እኮ ደስ ብሎኝ ላከብረው እችላለሁ?»
« በቃ ተወው ። ይቅርታ›› አለች ። ትበል እንጂ ያ ቀን ለሱ ለምን መልካም እንዳልሆነ የተገነዘበች አትመስልም፡፡ ‹‹ነገርን ነገር ያመጣዋል ቤት ተከራይቼ ፤ ለብቻዬ መኖር እፈልጋለሁ»
‹‹በመገረም ቀና ብላ አየችውና ፤ « ለምን ? » አለች «ምክንያቱም ሃያ አምስት ዓመት ሞላኝ ። ሠራተኛ ነኝ። ዘላለም አብሬሽ መኖር የለብኝም »
«ምንም ነገር በግዴታ ማድረግ የለብህም » አለች። በልቧ ስለ ቤን አቭሪ ጓደኝነት ማሰላሰል እየጀመረች። «የለም ነገሩን በክፉ እንድትተረጉሚው አይደለም ። ሆኖም እንተወው ። ራስ ምታት እንደወፍጮ እየወቀረኝ ነው » «የዞረ ድምር መሆኑ ነዋ » አለችና ተነሳች ፤ ሰዓቷን እያየች «ቢሮ እንገናኝ ። በሰዓቱ ግባ ። ደሞ ስብሰባ አለ እንዳትረሳ። የሀውስተንን ጉዳይ በሚመለከት ስብሰባ መኖሩ ተነግሮህ የለ! እንዴት ነው ልትገኝ ትችላለህ ? »
«እችላለሁ .... እና ስለቤቱ ጉዳይ ... እሚከፋሽ ከሆነ ይቅርታ ። ግን ወስኜ ጨርሻለሁ። ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል። » ኮስተር ብላ ካጤነችው በኋላ « ይሆናል ማይክል ። ምናልባት ጊዜው ይሆናል ። በነገራችን ላይ መልካም የልደት በዓል ይሁንልህ » ብላ ግንባሩን ሳመችው። መልካም ምኞቷን በፈገግታ ተቀብሎ ራስ ምታቱ እየወቀረው