Get Mystery Box with random crypto!

«ተዘጋጅተሻል ?» ‹‹ይመስለኛል » ናንሲ ማክአሊስተር የመጀመሪያው ኦፕራሲዮን ሊደረግላት ነው። ካ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

«ተዘጋጅተሻል ?»
‹‹ይመስለኛል »
ናንሲ ማክአሊስተር የመጀመሪያው ኦፕራሲዮን ሊደረግላት ነው። ካንገቷ በላይ ምንም ስሜት አይሰማትም ። በዓይኖቿ ያለችበትን ባታይ ኖሮ ፊቷ ለመኖሩ ርግጠኛ ባልሆነች ነበር ። የአፕራሲዮን ማድረጊያው ክፍል መብራት ስለሚያብረቀርቅ አይኗን በደንብ መግለጥ እያስቸገራት ነው ። ዓይኗን ማጨንቆር ይኖርባት ነበር ። ይህን እንኳን ማድረግ አልተቻላትም ። የሚታያት የፒተር ፊት ብቻ ነው ። ኦፕራሲዮን የሚያደርገ ሀኪም የሚለብሰውን ልብስ ለብሷል ። አፉንም ተሸፍኗል ዓይኖቹ ፤ ፍቅርን የሚረጩ ዓይኖቹ ያበራሉ ።

ፒተር ግሬግሰን ናንሲ ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ አላረፈም። ኦፕራሲዮን ከመጀመሩ በፊት ቀዶ ህክምናውን የሚያካሔድ በትን ዘዴ ሲቀይስ ፤ ሲነድፍ ፤አጠናክሮ ንድፉን ሲያወጣ! ሲለካ ሲዘጋጅና ሲያጫውታት ሰባት ሳምንት አለፈ ።፡ ይሀን ሁሉ የሚያደርገው ደግሞ ፊቷን በተለያየ ጊዜ ራጅ አንስቶ ነበርና ከራጁ ያገኘውን ምስል እንደመነሻ በማድረግ የጐደለውን በማየት፣፤ የሚሟላውን በማጥናት ነበር ። የናንሲን ፊት እንደገና ለማነጽ ፎቶ ግራፉን ማግኘት ይፈልግ ይሆናል። ሆኖም የተገኘው አንድ ፎቶ ግራፍ ብቻ ነበር «ይኸውም እሷና ማይክል ርሄት በትለርና ስካርለት ኦሀራን ሆነው በባዛር ላይ የተነሱት ፎቶግራፍ ብቻ ። እሱም በደንብ አልወጣም ። ያም ሆነ ያ እሱም አያስፈልገውም ። ለመነሻ ያህልም ቢሆን ያቀደው ፊት አለ ።

«ነቃ ነቃ ማለት አለብሽ ። ትንሽ ሰመመን...ኖ... መተኛት የለብሽም ። ያ እንዳይሆን ደግሞ አነጋግሪኝ» አለ፡፡ እንቅልፍ ሲጫናት ሽፋሏ ሲሰበር ስላየ። በልቡ ደግሞ ያለዚያ ደምሽ ያንቅሻል ሲል ጨመረ ። ይህን ግን አልነገራትም ። ሊነግራትም አልፈለገም ።
«እማሆይ አግኒስ ሜሪን መሆን እንደምትፈልጊ አሁንም ርግጠኛ ነሽ ? » አላት ፤ እንዳትተኛ ለማድረግ ።
‹‹እንዴ...ሃ!ሃ!ሃ!... ቃል ፣ቃል አይደለም እንዴ» አለች ።

ሶስት ሰዓት የፈጀው ኦፕራሲዮን ሲከናወን በዚህ ሁኔታ እየተቀላለዱ አሳለፉት ። ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ እጁ አንዴም አላረፈም ። ናንሲ የእጁን እንቅስቃሴ ስታይ ልክ የባሌ ተውኔት ዳንስ እንደማየት ሆኖ ነበር የተሰማት ።
«በዚህ ሁኔታ ከጥቂት ሣምንታት በኋላ አዲሱን አፓርታማ እንከራይና ትገቢያለሽ ... እስኪ አስቢው ፣ደስ የሚል ነገር አይመስልሽም? . . . እንዴ እንቅልፍ መተኛትሽ ነው እንዴ! የአዲሱ አፓርታማ አቀማመጥ እንዴት ቢሆን ይሻል ይመስልሻል ? እመኝታ ቤትሽ ሆኖ በመስኮት የሳንፍራንሲስኮን ወደብ የሚያሳይ ቢሆን ይስማማሻል ? »
« አዎና ለምን አይስማማኝም››
«አዎና ብቻ ነው እምትይው ? በጣም፣ በጣም... ምናምን አይባልም ! የለም ፤ የለም ይህ ከሆስፒታሉ ላይ ሆነሽ የሚታይሽ ነገር አእምሮሽን እያሻገተው ሳይሆን አይቀርም »
«ውሸት ነው ። በጣም ነው የሚያስደስተኝ እንዲያውም»
«ደግ እንግዲያ ። አንድ ቀን አብረን ወጣ እንልና ከዚህ በጣም የተሻለ ቤት እንመርጣለን »
‹‹ጥሩ» አለች እንቅልፍ በተጫነው ድምፅ ። እንቅልፍ በተጫጫነው ድምፅ ብትናገርም ደስ መሰኘቷ ይታወቅ ነበ
«እንዴት ነው አሁን መተኛት አልችልም ማለት ነው?›› አለች ።
«ልዕልት ሆይ እንሆ የመኝታ ጊዜ ተቃርቧል ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወዴ መኝታ ቤትዎ እናደርስዎታለን ። ከዚያም ልዕልትነትዎ የፈቀደውን ያህል ሊተኛ ይችላል »
« መልካም »
« አሃ! ሳሰለችሽ ነበር ማለት ነው የቆየሁት !» ይህን ያለበት የቀልድ ኩርፊያ ድምፅ አሳቃት ።
«እሺ ፍቅሬ... አሁን ሁሉም ዝግጁ ነው » አለና ረዳቱን ተመለከተ ። በጥቅሻ አመለካከት ። ይህን ያየችው ነርስ ናንሲን መርፌ ወጋቻት ። ይህ ሲደረግ ፒተር አላየም ። ወደናንሲ ጠጋ ብሎ ዓይን ዓይኗን ያይ ነበር ። እሱ ፤ የሷን ፤እሷም የሱን ዓይን በሚገባ ያውቃሉ ። መግባባታቸውን የሚያዩት በዓይኖቻቸው ውስጥ ነበር ።
«ዛሬ ለየት ያለቀን መሆኑን ታውቂያለሽ ?» አላት
« አዎ» አለችው ።
«አረ?... እንዴት ልታውቂ ቻልሽ ? » ምክንያቱም አለች በልቧ ፣ ምክንያቱም ዛሬ የማይክል ልደት ነው ። ማይክል ዛሬ ልክ ሃያ አምስት ዓመት ይሆነዋል ። አሁን በዚህ ሰዓት ምን እያደረገ ይሆን?

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj