Get Mystery Box with random crypto!

ነፍስ ስታፈቅር ምዕራፍ -22 ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ /// ሁለቱም ነጭ ፎጣ ከወገባቸው በታች አገል | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

ነፍስ ስታፈቅር
ምዕራፍ -22

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ
///
ሁለቱም ነጭ ፎጣ ከወገባቸው በታች አገልድመው ጣጣቸውን ጨርሰው ከሻወር ወጡ..አልጋው ጠርዝ ላይ ጎን ለጎን ተቀመጡ..
‹‹እርቦሀል?›› አለችው::
‹‹በጣም….መቼ ምግብ እንደበለው አላስታውስም››መለሰላት፡፡
‹‹እንግዲያው እንብላ .እኔም እራቴን እስክጠግብ የበላው ቢሆንም አሁን ሆዴ ውስጥ አውሬ እንደታሰረ እየቧጠጠኝ ነው›››አለችና ከመቀመጫዋ በመነሳት ምግብና መጠጥ የተደረደረበትን አነስተኛ ጠረጳዛ ቢላል ወደ ተቀመጠበት ቦታ እያስጠጋች፡፡
‹‹ቡዙ ኃይል ስላወጣሽ ነዋ….››
‹‹ቀላል ኃይል…ሙጥጥ ነው ያደረከኝ.››
///
ቀላል ጫወታ እየተጫወቱና እየተጎራረሱ ምግብን በሉ…ከሚጠጠውም ጠጡ.
//
‹‹አሁን ብንተኛ ምን ይመስልሀል.?››.
‹‹ደስ ይለኛል››
‹‹ቢጃማ ልስጥሀ?››
‹‹…አንቺን ማረብሽሽ ከሆነ…እንዲሁ ብተኛ ደስ ይለኛል››
‹‹ግድ የለህም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መረበሽ እራሱ የራሱ የሆነ ጣፋጭ ጣእም አለው.››
‹‹እንግዲያው አጣጥሚው …››.አለና ያገለደመውን ፎጣ ከላዩ ላይ ተርትሮ አነሳና ጠረጵዛ ላይ አስቀመጠ…መለመላውን ወደ አልጋው ወጣ ….ገልጦ ከውስጥ ገባ….እሷም ልክ እንደእሱ አደረገች…አዎ ይህቺን ቀን በተደጋጋሚ በህልሟ አይታታለች….ህልሟ ህልም ሆኖ ይቀራል የሚል ጠንካራ ጥርጣሬ ነበራት….አሁን ግን ይሄው ባላሰበችው ተአምራዊ መንገድ ህልሟን እየኖረችው ነው..…የነፋሷን ጌታ በስጋዋ እቅፍ ከታ..በትንፋሹ ውስጧን እያሞቀች ….በሙቀቱ እየቀለጠች…በደስታ ስካር ላይ ነቸ….ይህ ተአምር ነው፡፡ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች…እጆቹን በአንገቷ ስር አሸግሮ አቀፋታ አንዱን እግሯን አነሰችና እግሮቹ ላይ ጫነች..አንደኛው እጇን ደረቱ ላይ አሳረፈችና የደረቱን ጸጉሮች ማፍተልተል ጀመረች…..
‹‹ግን ይሄን ሁሉ ቀናት የት ሄደህ ነበር?››ካገኘችው ደቂቃ ጀምሮ ለመጠየቅ ፈልጋ ግን ደግሞ እስኪረጋጋ በሚል የማዘን ስሜት አፍናው የነበረውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹እንዲህ በነፍሴ ጭምር ስጨናነቅ የምሄድበት ቦታ››
‹‹እኮ ያ ቦታ የት ነው?››
‹‹እሱን አሁን አልነግርሽም››
‹‹እሺ እንዳሰብከው መሄድህ ጠቀመህ?››
‹‹አንቺ ምን ይመስልሻል?››
‹‹እሱማ እንደማይህ በጣም ጠቅሞሀል….ካሰብኩት በላይ ተረጋግተህል…. ፍፅም ጤነኛ ሆነህ ነው የመጣሀው››
‹‹ፍፅም ጤነኛ አልሽ..ፍፅም ጤነኛ እና ፍፅም በሽተኛ የሚባል ሰው የለም…ሁላቸንም ጤነኝነት እና በሸተኝነትን በደባልነት አዝለን ነው የምንዞረው …. ልዩነቱ የመጠን ጉዳይ ነው.እንዳልሺው ግን መሄዴ ጠቅሞኛል….ቢያንስ እስከዛሬ አንቺን አልገደልኩሸም…››
‹‹ለእኔ ግን ዝም ብለህ አድራሻህ ሳታሳውቅ እንደዛ ጠፍተህ በፍለጋ ከምታሰቃየኝ ..ብትገድለኝ ይሻለኝ ነበር››
‹‹አዎ እኔም ለብዙ ቀን በነገሩ ላይ ካሰላሰልኩበት ቡኃላ‹ ….እስከመቼ ገና ለገና ልገድላት እችላለው በሚል ስጋት ከእሷም ሆነ ከእናቴ እሸሻለው…?ወደእሷው ተመለሼ እውነታውን መጋፈጥ አልብኝ..ደግሞ እጣፈንታን ይጋፈጡታል እናጂ ሸሽተው አያመለልጡትም › ብዬ ወሰንኩ እናም እንደምታይው መጣው..››
‹‹ከግድያ ወሬ እንውጠና ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ?››
‹‹ያንቺው ነኝ.. .እንደፈለግሽ››
‹‹ስለቤተሰቦችህ››
‹‹ስለቤተሰቦችህ ምን.?››
‹‹ፕሮፌሰር ወላጅ እናትህ እንዳልሆነች አውቄያለው››
‹‹ለእኔ ግን እንዳዛ አይሰማኝም›
‹‹እሱ ጥሩ ነው…ግን ስለወላጆችህ ምን ታውቃለህ?››
‹‹ምነው አንቺ ስለቤተሰቦቼ የምታውቂው ነገር አለእንዴ ?››
‹‹በፍጽም››
‹‹እንግዲህ እኔም ምንም አላውቅም…እናት፤ አባተ የለኝም፡፡ልጅነቴ ትዝ አይለኝም፡፡የሞለ ህፃናት ቆይታዬ እንዴት እንደነበር አላውቅም…ትምህር ቤት የት ሀገር እንደተማርኩ እንኳን አላውቅም፡፡.ከአስተማሪዎቼ መካከል አንዱ እንኳን ትዝ አይለኝም…ግን እንደተማርክ አውቃለው… በከፍተኛ ደረጃ እውቅ የተባሉ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተምሬያለው….የት ? እኔ እንጃ……ስለ እነዚህ ነገሮች ምንም የማስታውሰው ነገር የለውም..ከልጅነቴ ጀምሬ ለረጅም አመት የሆነ ግዙፍ ዋርካ ስር በጥላው ተመስጬ በመተኛት ወጣትነቴን ካጋመስኩ ቡኃላ ድንገት የነቃውና ስነቃ ደግሞ የፕሮፌሰሯሮ እጅ ላይ እራሴን ያገኘው ነው የሚመስለኝ፡፡አዎ ያንን ብቻ ነው በግልፅ የማስታውሰው፡፡
‹‹ስለእኔ ምን ታስባለህ?››ሌላ ጥያቄ
‹‹ስለአንቺ ምን?››
‹‹እንዴት ልታፈቅረኝ ቻልክ….?መቼስ እንደሌላው ገንዘቤ ላንተ ትርጉም እንደማይሰጥህ አምናለው…መልኬ …?ንግግሬ… ?ምኔ..?
‹‹ከዚህ በፊት የነገርኩሽ መስሎኝ..›
‹‹ለእኔ?››
‹‹አዎ ለአንቺ…የማፈቅረው ነፍስሽን ነው ብየሽ ነበር››
‹‹አዎ አስታውሳለው….እሱ ግን አገላለፅ እኮ ነው…ነፍስ ተጨባጭና ተዳሳሽ አይደለችም››
‹‹ፍቅርም ተጨባጭና ተዳሳሽ ቁስ አይደለም..ግን ግልፅ ለማድረግ በነፍሴ ነው ያፈቀርኩሽ ሰል ላስረዳሽ የፈለኩት ያወቅኩሽ ወይም ያፈቀርኩሽ በአካል ያገኘውሽ ቀን እንዳልሆነ ለመግለፅ ፈልጌ ነው››
ወደምትፈልገው መስመር እየገባላት ሰለሆን በአድናቆት ከደረቱ ቀና በማለት ተንከባላይ አይኖቹን በፍቅርና በጉጉት እያች‹‹ይበልጥ አብራራልኝ.››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እብድ ባልሆን ኖሮ ይሄንን ማስረዳት ይከብደኝ ነበር…ግን ምንም አይነት ወጣ ያለ ነገር ብናገር ወይም ያልሆነ ነገር ብሰራ እብድ ስለሆነ ነው ስለሚባል ብዙም አያስገረምም. .እኔ አንቺን ከማግኘቴ በፊት፤ እቤትሽ ከመምጣቴ በፊት፤ ከፕሮፌሰሯ እናቴ ከመገናኜቴም በፊት፤ ምን አልባትም ከመወለዴም በፊት ይመስለኛል የማውቅሽ…..አማዬ አልነገረችሸም እንዴ አንቺን ከማግኘቴ በፊት ገና ሆስፒታል በሰንሰለት ታስሬ ስታከም እራሱ ያንቺን ስዕል እየሳልኩ አሳያት ነበር…እሷ እንደውም ወላጅ እናቴ ወይም እህቴን የምስል ይመስላት ነበር…አሁን ነው ነገሩ የገባት….››
‹‹ስለዚህ መጀመሪያ እቤቴ መጥተህ ሻወር ፈልጋለው ብለህ ያስደመምከኝ ሆነ ብለህ ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹በፍጽም …ለምን እንደዛ አልሽ..?››
‹‹በወቅቱ ሰታየኝ ብዙም የተለየ ነገር አላሳየህማ…የዛን ቀን በአካል ያገኘኸኝ የመጀመሪያ ቀን ቢሆን ኖሮ ያሰታውቅብህ ነበር.››
‹‹እውነትሽን ነው….በአካል ሳይሽ ያ የመጀመሪያ ቀኔ አልነበረም…ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬ አመት አካባቢ ስለካማፓኒሽ በቲቪ መግለጫ ስትሰጪ ነበር ያየሁሽ..
‹‹እና ምን አደረክ?››
‹‹ምንም አላደረኩም….በወቅቱ ሰውነትን በጠቅላላ የሚነዝር የደስታ ስሜት ነበር የተሰማኝ….ሙሉ እብድ እንዳልሆንኩ ያወቅኩት የዛን ቀን ነው…..ምክንያቱም ተጨባጭ ነገሮችንም በአዕምሮዬ አለማለው ማለት ነው የሚለውን የአንቺ የሆነ ቦታ በአካል እውን ሆኖ መገኘት ማረጋገጨ ሆነኝ .ይሁን እንጂ እኔ በነፍሴ አፍቅሬያት በእየእለቱ እያለምኳት የነበረችው ሴት ተራና ንፅህ የመንደር ሴት እንድትሆን ነበር ፍላጎቴ…ከተቻለ ጭልጥ ያለ ገጠር የምትኖር .
‹‹አና እኔ ንፅህ አይደለውም ማለት ነው.?.››