Get Mystery Box with random crypto!

‹‹እሱ ብቻ አደለም ችግሩ በአንቺ ደረጃ ያሉ ሰዎች እርቴፌሻል ህይወትና ነው ያላቸው..እያንዳን | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

‹‹እሱ ብቻ አደለም ችግሩ በአንቺ ደረጃ ያሉ ሰዎች እርቴፌሻል ህይወትና ነው ያላቸው..እያንዳንዷን በእለት ውሎቸው የሚከውኗቸው ነገሮችን እቅድ በሚል ስም መጀመሪያ በወረቀት ላይ እስክሪፒቱን ይጻፍና ከዛ ሳያዛንፉ ሲተውኑ ይውላሉ.. ንግረግራቸው በተመረጠና የሆነ ውጤት እንዲያመጣ በተሰላ መንገድ የሚነገር…አለባበሳቸው የሆነ መልዕክት የሚያስተላልፍ …አበላላቸው.አጠጣጣቸው..ሁለነገራቸው አርቴፊሻል ነው..እና ባለሽበት ተውኩሽ››..
‹‹በነፈስ ማፍቀር እንዲህ ለመተው ቀላል ነው እንዴ?››ሞጋች ጥያቄ ጠየቀችው፡
‹‹አዎ ..አልከበደኝም.፡፡ምክንያቱም እኔ ማስባትን አይነት እንደሆንሽና የሆነ በደን በተከበበ የአራዊት ማጎራት በቅርብ በሚሰማበት.፤የወፎች ዝማሬ መንፈስን በሚያድስበት፤ ፎፎቴ ከተራራው አናት ከሚከነበልበት፤ ልዩና ንፅህ ቦታ ልክ እንደሄዋን በቅጠል እፍረትስጋዋን ብቻ ሸፍና ከእንጨት ተጠርቦ የተሰራና በሀረግ የተጠቀለ ጫማ አድርጋ፤ ፀጉሯና ከወዲህ ወዲያ ንፋስ እየተበተነባት፤ ከበለስ ግንድ ላይ የበሰለውን ስትቀነጥስ በምናቤ እያየውና እየጎመዣው እችለዋለው፡››
‹‹ስለገኘኸን እና እንዲህ ስለሆነ ቅር ብሎሀል?››አለችው ቅር በተሰኘ የስጋት ድምፅ
‹‹አላለኝም ..ምክንያቱም የዛን ጊዜ ስለአንቺ የወሰድኩት ግምቴ ላይ ግማሽ ሰህተትም ነበረበት››
‹‹እንዴት?››
‹‹…አንቺን ፍጽም አርቴፊሸል ሴት እንደሆንሽ መገመቴ የእኔ ስህተት ነበር ፡፡ያንን ስህተን ደግሞ የተረዳውት አሁን ባልሽው ለመጀመሪያ ቀን ሻወር ፍለጋ እቤቴሽ መጥቼ ዘበኛሽ አበሻቅጦ ሲመልሰኝ አንቺ ተቀበለሽ በሳተናገድሺኝ ቀን ነው፡፡በአንቺ ቦታ እና ደረጃ ያለች ሴት የፈለገ በውስጧ ብትፈልግ እንኳን እንደእኔ አይነት ሰውን ወደቤቷ አታስገባም…››
‹‹እና የመጀመሪያውን ፈተና በመጀመሪያው ቀን አልፍኩ ማለት ነው››
‹‹አዎ…..እስከአሁንም ያልተቀየረ ፅናት ነው ያለሽ….ከልብሽ ለሚፈልቀው እውነት በዓለም ፊት በድፍረት የመቆም ፅናት . ..››
‹‹እሺ ትክክል የሆንከውስ?››
‹‹….አነቺ ተራ ሰው ባለመሆንሽ በዙሪያሽ ብዙ ጣጣ እንዳለ መገመቴ ትክክል ነበርኩ፡፡እንቺ ባትፈልጊም በዙሪያሽ ብዙ ኮተትና እና ግሳንግስ መኖሩን አይቀሬ ነው…ለምሳሌ ልታገቢው ቀለበት ያሰርሽለት ሰው...››
‹‹ሄኖክ ..እሱ ምን ሆነ?››
‹‹ያፈቅርሻል አውቃለው….ግን ካንቺ በላይ ንብረትሽንና ዝናሽን ነው የሚያፈቅረው..ያንንም የማሳጣው ስለመሰለው ሊያስገድለኝ አራት ሰው ቀጥሯል…››
‹‹እንዴ !!!አንተ ይሄንን እንዴት ልታውቅ ቻልክ..?››
‹‹ይሄንንም አልነግርሽም…ደግሞ ቤተሰብ የለኝም እንጂ ጓደኞች የሉኝም አላልኩሽም… በመጀመሪያ እኔን መስሎቸው ለገደሉትና ከዚህ አለም መከራ ለገላገሉት ሰው 1 ሚሊየን ብር ከፍሎቸው ከስሯል…አሁንም ሁለተኛ ስመምነት በስድስት መቶ ሺ ተስማምተው ቅድመ ክፍያ 150 ሺ ብር ከፍሏቸዋል.ከአንቺ ከመገናኘቴ በፊተአግኝተው ሊገድለኝ መከራቸውን እየበሉ ነው ››
‹‹ምንድነው የምታወራው…?››
‹‹ከፈለግሽ ግድያውን የመራውን ግለሰብ ስም ..የተጻፈለትን ቼክ እና ቼኩን የመነዘረበትን የባንክ ቅርንጫፍ ሁሉ ልነግርሽ እችላለው..ከዛ አንቺ ደግሞ ባለሽ ተፅዕኖ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችያለሽ፡፡እናም ደግሞ ትዕዛዙን ሲያስተላልፍ ገዳዩ ቀድቶታል….እኔ ደግመ ሞባይሉን በሆነ መንገድ ተቀብየዋለው..ከፈለግሽው ጃኬቴ ኪሴ ውሰጥ አለልሽ..››
ከመኝታዋ ተስፈንጥራ ተነሳች….ጃኬቱ ወደተንጠለጠለበት የልብስ መስቀያ አመራች…ደልደል ያለ ሰውነቷንና የሚገለባበጥ መቀመጫዋን በተኛበት በስስት እያየ ነው…እጇን በጃኬቱ ኪስ ውስጥ ከተተች..ለመጀመሪ ጊዜ እጇ ላይ የገባላትን አወጣች...አብረቅራቂና ስል ጩቤ ነው.አገላብጣ አያችው..አይኗን ወደቢላል ላከች…መልሳ እጇን ወደጃኬቱ ኪስ ሰደች…አሁንም ያገኘችውን ነገር ይዛ ወጣች...በግምት 10 ሜትር የሚረዝም ጠንካራና መካከለኛ ውፍረት ያለው ሲባጎ ገመድ ነው…ዝግንን አላት…፡፡ይህን ጩቤም ሆነ በእጇ የያዘችውን ገምድ ታውቀዋለች…ቢላል በጠፋ ቀን ጥሎላት በሄደው ስዕል ላይ ጩቤው እሷ የታረደችበት አይነት ሲሆን ገመዱ ደግሞ እሱ የተሰቀለበት ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ነው››
‹‹ምንድነው ይሄ››አለችው ሁለቱንም እጇን ወድሱ እየዘረጋች
‹‹አጥር ዘልዬ ጣሪያቸሁን ቀድጄ እኮ ነው እዚህ ስርሽ የተገኘው…ይሄን ሁሉ ደግሞ ባዶ እጄ ብቻ ላደርገው አልችልም…በዛ ላይ..››
‹‹በዛ ላይ ምን?››
‹‹ተይው …ስልኩ በደረት ኪስ ውስጥ መሰለኝ ያለው ››.
የያዘችውን ጩቤና ገመድ ጠረጳዛው ላይ አስቀመጠችና ወደጠቆማት ኪስ እጇን ሰደደች .. .ዘመናዊ ሳምሰንግ ስልክ አገኘች፣ይዛ ወደአልጋው ተመለሰች… .ከፍቶ እንዲያሰማት አቀበለችው..
የሶስት ደቂቃ ቆይታ ያለውና ሌላ ደግሞ የ5 ደቂቃ ቆይታ ያለው የስልክ ልውውጥ ነው…እሷን እየተከታተሏት መሆኑን..ቢላል እንዲገደል የተሰጠ ትዕዛዝ..የልጁ በስህተት መገደል….ሁሉን በግልፅ ያሰርዳል፡፡
‹‹ወይኔ ምኗ ጅል ኖሬያለው…ወደስልኬ ላክልኝ፡፡››
‹‹አረ እኔ ምን ያደርግልኛል.ስልኩን እኮ ለአንቺ ነው ያመጣውት..ከፈለገሺው ማለቴ ነው፡፡››
‹‹አረ በጣም ነው የምፈልገው…..በል አሁን ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሆነ እኮ… ትንሽ እንተኛና ምን እንደምናደርግ ሲነጋ እናወራለን››
‹እሺ እንዳልሽ….››
ማብራን ተንጠራርታ አጠፋችና እቅፉ ውስጥ ተሸጎጠች…ለተወሰነ ጊዜ እንቅልፍ እንዲወስዳት በመፈለግ ተገለባበጠች ..ግን ሊወስዳት አልቻለም‹ቢላሌ›በለሆሳሳ ድምፅ ተጣራች፡
‹‹አቤት የእኔ ፍቅር››
‹‹ብንጋባ ምን ይመስልሀል?››
‹‹እየቃዠሽ ነው እንዴ?››
‹‹አይ እውቴን ነው….››
‹‹እብድ አግብተሸ አንዴት እንዴት ልትሆኚ ነው..?በዛ ላይ ከእብድ መውለድ አለ…ነው ወይስ አሁን ጤና ስለሆንኩ ሁልጊዜ እንደዚሁ የሚቀጥል መሰለሽ›
‹‹ግድ የለህም ..ከእኔ ጋር ከተጋባህ ለዘላለም ጤነኛ ትሆናለህ…ባትሆንም ደግሞ ከጎኔ እስካለህ ድረሰ ግድ የለኝም…››
‹‹አይ ሚሆን አይመስለኝም…..ቅድም እኮ ነገርኩሽ .አንቺ ብዙ ጣጣ ያለብሽ የአደባባይ ሴት ነሽ›
‹‹ለአንተ ስል ሁሉን ነገር ተዋለው.በእዕምሮህ ያለችውን አይነት ሴት ሆንልሀለው…እልም ያለ ገጠር እንገበለን በደን የተሸፈነ ፤እንስሳት የሚተረማመሱበት፤ ወፎች የሚደንሱበት ፤የሰው ግርግር የሌለበት አንድ አነስተኛ ገነት መሳይ ደሴት እንገዛና እዛ እንኖራለን….›
‹‹ወይ .ለዚህ እኮ ነው በነፍሴ የማፈቅርሽ..እና ደግሞ በጣም ነው ያስጎመዠሺኝ ….ግን ሌላ ሁለት ችግር አለ››
‹‹ምንና ምን?››
‹‹አንደኛው የአባትሽ ጉዳይ ነው…ጋብቻሽን በተመለከተ ስለተፈራረምሽው ውል አውቀለው››
‹‹አሱን ለእኔ ተወው የሆነ መፍትሄ አገኝለታለው…ሁለተኛውን ችግር ንገረኝ››
‹‹ሁለተኛው እረሴው ነኝ…እስከዛው ካልገደልኩሽ….›
‹‹ከገደልከኝማ ተገላገልን …ሁሉ ነገረ እዛ ላይ ይገባደዳል››
‹‹እንደዛ ከሆነ እሺ…ምን አልባት ልንጋባ እንችላለን…አሁን ደህ እደሪ››
‹‹ደህና አደርልኝ.››
‹‹ጭኑ መካከል አስገባትና ቅልፍልፍ ብለው ተኙ…ሁለቱም በደቂቃዎች ውስጥ ነበር ጭልጥ ያለ ሰላማዊ እንቅልፍ የወሰዳቸው፡፡


ይቀጥላል ....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj