#አይዞሽ ከመንገድ ዳር ቆመሽ~ሰዉ ቢያዝንልኝ ብለሽ ፣ ስለደረሰብሽ ~አዝነሽ ታነቢያለሽ ። እንባሽ ቁልቁለቱን~ተጣድፎ ይወርዳል ፣ ጊዜም ሰመረለት~ አልቃሾች ይወዳል ። የኔ እናት ተለምዶ ቢሆንም~መሳቅና ማልቀስ ፣ አንቺ ግን እንባሽን~ገታ አድርጊዉ ቀነስ ፣ በምድር የለምና~የሚልልሽ ሀይ ባይ ፣ ፈገግታ እያበዛሽ~ሁሌም ተመስገን በይ ። ቢከፋ ቢገድም~መሳቁ ይበጃል ፣ ጊዜ ያነገሰዉ~በጊዜዉ ያረጃል ፣ እስከዚያዉ ጠንክሪ~ አይዞሽ የኔ ስስት ፣ ትስቃለች እንጂ~አታለቅስም ንግስት ። ታገል ነኝ https://telegram.me/afkarish 202 viewsmadi@, 04:37