Get Mystery Box with random crypto!

'በራስ መተማመን' . በአንድ ወቅት፣ በሙስሊሙ አለም አንድ የዳኝነትን ሹመት የተሰጠው መሃይም ሰው | 🍂ISLAMIC TEAM🍂

'በራስ መተማመን'
.
በአንድ ወቅት፣ በሙስሊሙ አለም አንድ የዳኝነትን ሹመት የተሰጠው
መሃይም ሰው ነበር። እና አንድ ቀን ሁለት ሰዎች ተጣሉና ለፍርድ ወደዚህ
ሰው ይመጣሉ። በመጀመሪያ ከሳሹ ክሱን ለዳኛው አቀረበለት። የተናገረው ሁሉ ዳኛውን አሳምኖት ነበርና አምኖ ተቀበለው። “ማሻ አላህ! ሐሳብህ ጥሩ ነው። ወላሂ አንተስ እውነትም ተበድለሃል። እውነቱ ያለው አንተ ጋር ነው!” አለው።

አሁን ተከሳሹ ተራ ደረሰውና ራሱን ለመከላከል፣ ንጽህናውን ለማረጋገጥና
ክሱን ውድቅ ለማድረግ ንግግሩን አቀረበ። አሁንም የዚህ ሰዉየ ንግግር
ዳኛውን አሳመነው። ሃሳቡ ተዋጠለት። ስለዚህ ለዚህኛውም ሰውየ፣ “ትክክል
ነህ፣ ሀቁ ያለው ካንተ ጋ ነው።” አለው።
እውነቱ ያለው ከተበዳዩ ወይም ከበዳዩ ሆኖ ሳለ ለሁለቱም ፍርድ ሰጠ።

ይህን የፍርድ ሂደት ከመጋረጃው ጀርባ ሆና ትክታተል የነበረችው የዳኛው
ሚስት፦ “አንቱ ሰውየ! ምን አይነት ፍርድ ነው የምትሰጡት፣ የመጀመሪያውን አንተ ነህ ትክክል አልኩ፣ ሁለተኛውንም እንደዛው። ይህ እዴት ይሆናል?” አለች። ሰውየውም፣ “ወላሂ፣ አንችም ትክክል ነሽ። የተናገርሽው በጣም ልክ ነው።” አላት።

ግፍ የተሰራበትም ትክክል ነው፣ በዳዩም ትክክል ነው፣ ፍርዱን የነቀፈችውም
ሴት ትክክል ናት። ሌላም አራተኛ ሰው መጥቶ ቢናገር ትክክል ነው። እንዲህ
አይነቱ ሰው እንግዲህ በራሱ ውሳኔ የማይተማመን እና በሰዎች ሃሳብ ብቻ
የሚመራ ሰው ይባላል። በራሱ ሀሳብ የማይመራ እና የራሱ ጠንካራ እምነት
የሌለው ሰው እንዲህ ነው። በሰው ሀሳብ ይመራል፣ ወደነፈሰበት ይነፍሳል።
ዝም ብሎ ማንኛውንም ሰው በጭፍን መከተል ስኬታማ አያደርግም፣ በራስ
መተማመንንም ይገድላል።

በራሱ የሚተማመን ሰው በሰዎች አስተያየትም ሆነ አመለካከት በቀላሉ
አይሸወድም፣ የራሱ የሆነ ጠንቃራ አመለካከት አለው። የሰዎችን ጭብጨባና ማዳመቂያ አይፈልግም። እያንዳንዱን ርምጃ በራሱ ተነሳሽነት ነው የሚወስደው። የሚያደርገው ነገር በሙሉ ትክክል ለመሆኑ ደግሞ የሰዎችን ማረጋገጫና ይሁንታ አይፈልግም፤ ምክንያቱም የሚያደርገውን ያውቃል።
ያመነበትን ነገር ያለ ምንም መሸማቀቅና እፍረት ይሰራል፣ መናገር ያለበትን ይናገራል። ሰዎች ያዘዙትን ነገር ሁሉ እሽ ብሎ አይቀበልም፣ “አይሆንም፣ የራሴ የምሰራው ስራ አለኝ፣ እንደዚህ አላደርግም።” ብሎ የሰዎችን ሃሳብ
ውድቅ ማድረግ ይችላል። “ኖ” ማለቱን ይችልበታል።

በራሱ የሚተማመን ሰው ራሱን ያውቃል። ስለራሱ ጥሩ ግንዛቤ አለው። ጥንካሬውንና ደካማ ጎኑን ለይቶ ያውቃል። ስለራሱም በጎ ምልከታ አለው። ራሱን ይወዳል፣ ራሱን ያከብራል። ለመሻሻል ይጥራል። ተጨባጭ ግቦችን ያስቀምጣል፣ ተጨባጭ ውጤቶችን ይጠብቃል። እንዲሁም የሰዎችን ትችት
በቀላሉ ተቋቁሞ ያልፋል። በራሱ የሚተማመን ሰው እንግዲህ እንዲህ ነው። የሚያወራውንም ሆነ የሚሰራውን ነገር ያውቃል።

በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች፣ ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ ከፍ ያለ ነው።
እንደዚህ አይነት ሰዎች ህይወትን በደስታ ይኖራሉ። ሁሌም ለህይወት ጥሩ የተነሳስሽነት ስሜትም አላቸው። በራስ መተማመን የሌለው ሰው ደግሞ በተቃራኒው ነው። ለራሱ ክብር የሌለው ወይም በራሱ የማይተማመን ሰው
በሌሎችም ዘንድ ዋጋ እንደሌለው ያስባል።
.
.

@islllllaamic