Get Mystery Box with random crypto!

ከሙሉነት ጥቂቱን...4 (Team Huda) : #የማህበራዊ_ህይዎት_አመላካች የኛ ነቢ ሙሉ ናቸው ስ | 🍂ISLAMIC TEAM🍂

ከሙሉነት ጥቂቱን...4
(Team Huda)
:
#የማህበራዊ_ህይዎት_አመላካች
የኛ ነቢ ሙሉ ናቸው ስንል የምናወጣባቸው አይብ ስለሌለ ነው። በምላሳቸው የወጣን በተግባር ለመከወን የሚቀድማቸው አልነበረም። ማህበራዊ ህይዎት...መተዛዘንና መተሳሰብ ካስማዎቹ ናቸው። ይህ የሚታየው ደግሞ 'የኔ' ከምንለው ስብስብ ውጪ ካለ ሰው ጋር ባለን መስተጋብር ነው። ከኔ ሀይማኖት...ብሔር...ቀለም...ሌላም ሌላም።
የኛ ረሱል አይሁድን ጀናዛ ቁመው አላሳለፉምን? ሲነገራቸውስ <ፍጡራንን ለፈጣሪያቸው ስትል ውደድ> የሚል ዘመን አይሽሬ አብረቅራቂ መርህን አልነገሩምን?

ደግሞ ሰሃባዎች ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም ቢጠናባቸው... እነሱን እንዲረግሙላቸው ወደ ነብያችን ያቀናሉ። ብለው ያሏቸው ግን ከሳቸው ሙሉነት የሚጠበቅ...ለኛዋ ነፍስ የሚከብደውን ነው... <እኔ ለእርግማን አልመጣሁም ለእዝነት እንጂ። ጌታዬ ሆይ እነርሱ አያውቁምና አቅናቸው።>

ከዚህ ጣፍጭ ባህር አንድ እናክል:
የምናውቀው አብደላህ ኢብን ኡበይ ሙናፊቅ ነበር። መሪያቸውም ጭምር። ያጠፋውን የመፅሀፍ ገፆች ላይ አናጣውም። በተቃራኒው ልጁ እጅግ ታሚኝና ዓቢድ ነበር። አብደሏህ በሚሞትበት ወቅት ልጅዬው ነብያችን ጋር መጥቶ ቀሚሳቸውን ጠየቀ-ለአባቱ መገነዣነት። የልጁን ቀልብ ላለመስበር ...የተወዳጅ ባለቤታቸውን የእናታችን ዓኢሻን ስም ያጎደፈውን ሰው እንዲገነዝበት ሳያቅማሙ ሰጡ። ዓጂብ!!

@islllllaamic