Get Mystery Box with random crypto!

እናት በየቀኑ ልጇን ትመታ ነበር፤ሊያውም በሰዎች ፊት፤ልጅ ግን አንድም ቀን አልቅሶ፣ ሸሽቶ፣ስሞታ | Un–rey&una–reiner official👑👑

እናት በየቀኑ ልጇን ትመታ ነበር፤ሊያውም በሰዎች ፊት፤ልጅ ግን አንድም ቀን አልቅሶ፣ ሸሽቶ፣ስሞታ እንኳን አቅርቦ አያውቅም፤ልጅ ከፍ እያለ እያደገ ቢሄድም እናት ግን ልክ እንደ ልጅነቱ መምታቷን አላቆመችም ...
ከእለታት አንድ ቀን ግን ልክ ወትሮው ስትመታው በጣም አምርሮ አለቀሰ፤እናትም ትታው ሄደች፤በሁኔታው የተገረሙት የአካባቢው ሰዎች"ከዚህ ቀደም ስትመታህ አልቅሰህ የማታውቀውን ዛሬ እንደተለመደው መታህ ለምን አለቀስክ?! በማለት ሲጠይቁት፣ልጅም
"የእናቴ ጉልበት መድከሙን እያስተዋልኩ፣ከጀነት በሮች መሀከል አንዱ የጀነት በር ሊዘጋብኝ ተቃርቦ እያየሁ እንዴት አላልቅስ! በማለት በመራር የሀዘን ስሜት መለሰላቸው።
___
ያ ረብ
የወላጆቻችንን ደስታ አትንፈገን፤ከቀልባቸው አንተው ጠብቀን፤በህይወት ያሉትን ከዓፊያ ጋር ረዥም እድሜ ለግስልን፤ያለፉትን በሰፊው እዝነትህ አከናንብልን!!!
ኣሚን ያ ረብ!!!!