Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84 አመት ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል። ሁላችንም ይመለከታል ። ኡበ | Un–rey&una–reiner official👑👑




አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84 አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል።
ሁላችንም ይመለከታል ።
ኡበይዱላህ ኢብን ኡመር አንድ ጊዜ
እንዲህ ብለው ነበር “ጀምዐ ሰላት
በተለይ ኢሻና ሱብሂ አምልጦኝ
አያውቅም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ቤቴ
እንግዳ መጣና ከርሱ ቆይቼ ኢሻ ሶላት
አመለጠኝ፡፡ ከቤት ወጣሁ፤ ጀምዐ
ሶላት ለማግኘት ብዬ በስራ ከተማ ላይ
የሚገኙ መስጂዶች በሙሉ ዞርኩ፤
ሁሉም መስጂዶች ተሰግዶ አልቋል፡፡
ሰዎቹ ባጠቃላይ ሰግደው
ወደቤታቸው ሄደዋል፡፡ እኔም ወደ
ቤቴ ተመለስኩና ማሰብ ጀመርኩ፤
ለራሴ እንዲህ አልኩኝ ‘በሀዲስ
በግለሰብ ከሚሰገደው ሰላት በጀምዐ
ሚሰገደው በ 27 ደረጃ ይበልጣል
ተብሎዋል፤ ስለዚህ 27 ጊዜ ኢሻን
ሰላት ብሰግደው በጀምዐ ከሰገዱት ጋር
እኩል ይሆናል’ ብዬ በማሰብ
ኢሻን ሰላት በቤቴ 27 ጊዜ ሰገድኩና
ተኛሁ፡፡ በዛው ቀን ለሊት በህልሜ
ከፈረሰኞች ጋር ፈረስ ውድድር
ስንወዳደር አየሁ፤ ፈረሴ ጠንካራ
ብትሆንም
እንኳ ሌሎቹ ላይ ልደርስባቸው
አልቻልኩም፤ ወደ ዃላ ቀረሁ፡፡ ፈረሴ
ትደርስባቸው ዘንድ እደበድባት
ጀመርኩ፤ ነገር ግን ምንም ለውጥ
ልታመጣልኝ አልቻለችም፡፡ አንደኛው
ፈረሰኛ ወደኔ በመዞር “ፈረስህን
አታሰቃያት እኛ ላይ ልትደርስብን
አትችልም” አለኝ፡፡ እኔም “ለምን?”
ብዬ
ስጠይቀው “ምክንያቱም እኛ ኢሻን
ሶላት በጀምዐ ነው የሰገድነው፤ አንተ
ግን ብቻህን ሰገድከው” በማለት
መለሰልኝ፡፡ ከዚህ ትልቅ ትምህርት
ወሰድኩ፤ በጣምም አዘንኩ፡፡” ይለናል
ኡበይዱላህ፡፡
ሱብሃነላህ!!
እኛ ስንት ሶላት ይሆን ጀምዐ
ያመለጠን?? ስንቶቻችን ይሆን በዚህ
ምክንያት ተፀፅተን የምናውቅ??
“አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84
አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል”
መባሉን ምናስታውስ ስንቶቻችን
ነን??
ዛሬውኑ እንነይት “ኢንሻ አላህ ካሁን
በሗላ አንድም ሶላት ጀምዐ
አያመልጠኝም” ብለን…ለኔም
ለናንተም ሰደቀቱል ጃሪያ ይሆናልና
መልክቱን
ሼር እናድርገው —
ያረብ በሰላት ላይ ጥንካሬና ብርታት ስጠን ከሰይጣን ተንኮል ጠብቀን።
ዋ!! ፈራሁልሽ ነፍሴ

https://t.me/Islamic_picher