Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ info_tech1 — Ethiopia E
የቴሌግራም ቻናል አርማ info_tech1 — Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @info_tech1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 710
የሰርጥ መግለጫ

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች መርጣችሁ ስለተቀላቀላችሁን ከልብ እናመሰግናለን!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-19 08:43:40
አየር መንገዳችን በህንድ ሰማይ ላይ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ህንድ ሙንባይ ኤርፖርት ሊያርፍ ሲል በነበረበት ቅፅበት የተነሳ ድንቅ ፎቶ ነው ።

መልካም የስራ እና የትምርህት ቀን ተመኘንላችሁ
92 views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 07:01:39 #የድረገጽ_ጥቆማ

በነፃ የቢዝነስ ኮርሶችን መውሰድ ትፈልጋላችሁ

አዎ ከሆነ መልሳችሁ፤ እንደሚከተለው ይቀርባል...

ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ድረገጽ፤ በነፃ የቢዝነስ ኮርሶች የምታገኙበትን ነው፡፡ አለም አቀፍ የንግድ ሴንተር (International Trade Centre)፤ በንግድ ስራ ዙሪያ የተለያዩ ኮርሶችን በኢንተርኔት በነፃ ይሰጣል፡፡ ድርጅቱ አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶችን ለመደገፍ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ ኮርሶችም የሚያተኩሩት:-

- በኤክስፖርት ቢዝነስ ላይ

- በስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ላይ

- ዲጂታል ማርኬቲንግ እና የመሳሰሉት ከንግድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

ኮርሶቹ በአብዛኛው ከሁለት እሰከ አራት ሳምንት (በሳምንት 2 ሰአታት) የሚወስዱ ናቸው።

ለመመዝገብም የሚያስፈልግን የራሳችን የኢ-ሜል አድራሻ ሲሆን ትምህርቱም ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት የሚሰጥ ነው፡፡

በዚህ ድረገጽ ላይ የሚገኙ ኮርሶች አብዛኛዎቹ ለንግድ ስራ የሚሆኑ ስለሆነ የራሳችንን ቢዝነስ ለመክፈት የምንፈልግ ከሆነ፣ የቢዝነስ ድርጅቶች ውስጥ የምንሰራ ወይም የቢዝነስ ትምህርት የምንማር ከሆነ በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡

ድረገጽ ላይ የሚሰጡትን ኮርሶች ለመውሰድ የሚያስፈልገን ነገሮች:-

1. ድረገጹ ላይ ለመመዝገብ የራሳችን የኢሜል አድራሻ ማዘጋጀት እና

2. ከተመዘገብን በኋላ የምንፈልገውን ኮርስ ከድረገጹ ላይ መርጠን፤ መመዝገብ እና መማር፡፡

ኮርሶቹን በራሳችን ፍጥነት እዛው ኢንተርኔት ላይ ማንበብ እና መማር እንችላለን፡፡ ኮርሱን ከጨረስን በኋላ መማራችንን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከድረገጹ ላይ ማውረድ እንችላለን። ከታች ሊንኩን በመንካት ድረገጹን ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

https://learning.intracen.org

ምንጭ:- Wede Sera ወደ ስራ


Join for more

@info_tech1
@info_tech1
102 viewsedited  04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 06:44:39 TrueCaller Pro v9.14.7

Category: #Utility
Hack:
Premium Unlocked
Feedback: 7.916.749 4.5
Price: Free

#share
#አዲስ ቁጥር ሲደወልላችሁ የቁጥሩን ባለቤት የሚነግራችሁ አፕ እንዴት ይሰራል???
#True_caller android app
የሚሰራበት ሃሳብ በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ነው።

አፑን መጀመሪያ ስትጭኑት የሚጠይቃችሁ ዋናው ከስልካችሁ የሚፈልገው ፈቃድ phone book or contact list ለማንበብ ነው ልክ ፈቃድዱን ሥትሰጡት ስልካችሁ ላይ ያለውን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ ከነ ስማቸው ወደራሱ central database server (ማእከላዊ መረጃ ማጠርቀሚያ ሰርቨር) በመላክ ይመዘግበዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ይህን አፕ በጫኑት ቁጥር ስልካቸው ላይ ያሉትን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ ወደ መረጃ ማጠራቀሚያው ይልከዋል።
ከዛ አዲስ ቁጥር ሲደወልላችሁ ወዲያውኑ ስልክ ቁጥሩን ከራሱ database ይፈልገዋል እና ያለውን መረጃ ያመጣላችኋል።

አስራሩ ባጨሩ ሲገለጽ: ሰጥቶ መቀበል እንደማለት ነው ። እናንተ ስልካችሁ ላይ ያሉትን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ እንዲወስድ ትፈቅዱለታላችሁ እሱ ደሞ የማታውቁት ስልክ ሲደወልላችሁ የስልኩ ባለቤት ማን እንደሆነ ይነግራችኋል።

ሌላኛው Facebook ን በመጠቀም አፑ ሌላ የsignup (መመዝገቢያ መንገድ አለው) ይህም በፌስቡክ signup ማድረግ ነው። በፌስቡክ login ስትሉ የፌአቡክ አካውንታችሁን መረጃ የማንበብ አቅም አለው ይህም የፌስቡክ ጓደኞቻችሁን እንዲያነብ ፈቃድ ይኖረዋል አልዚህ በተመሳሳይ መንገድ የጓደኞቻችሁን ስልክ፣ ፎቶ ስም እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን መሰብሰብ ይችላል።

mame computer technology

@info_tech1
73 viewsedited  03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 21:03:29 10 ነፃ ሶፍትዌር ማውረጃ ድረ-ገፆች

1) www.FileHippo.com
2) www.Ninite.com
3) www.Cnet.com
4) www.Softpedia.com
5) www.MajorGeeks.com
6) www.FilePuma.com
7) www.DownloadCrew.com
8) www.FileHorse.com
9) www.SnapFiles.com
10) www.DonationCoder.com

mame computer technology


For more join us
https://t.me/info_tech1
https://t.me/info_tech1
112 views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 20:19:16 የጊዜ ትርጉምና አስፈላጊነት

“ጊዜ ከሁሉ ነገር በላይ እጅግ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ በተበላሸ ሁኔታ የምንጠቀምበት ነገር ነው” - William Penn

• የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀው፤
• የአንድን ወር ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ካለወሩ የተወለደን ሕጻን የወለደችን ሴት ጠይቃት፤
• የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በየሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቀው፤
• የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ የወሳኝ ፈተናን ውጤት ነገ ለመስማት የሚጠብቅን ተማሪ ጠይቀው፤
• የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸው፤
• የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ አውቶቡስ ለትንሽ ያመለጠውን ሰው ጠይቀው፤
• የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰው ጠይቀው፤
• የአንድን ሚሊ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀው፡፡
- Unknown Source

ሰው ለምንም ነገር የሚከፍለው በገንዘብ ሳይሆን በጊዜ ነው፡፡ ይህ እውነት ቀድሞውኑ ገንዘቡን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣው “ጊዜ” የተባለው ነገር የመሆኑን እውነታ ጠቋሚ ነው፡፡ ጊዜ በአለም ላይ ውድ ከተባሉ ነገሮች ቀደምተኛውን ስፍራ የያዘ ጉዳይ ነው፡፡ ጊዜውን ያባከነ ሰው ሕይወቱን ያባከነ ሰው ነው፡፡

ጊዜን በአግባቡ ባለመጠቀም ምክንያት ሰዎች ገንዘብን ይከስራሉ፣ ወዳጅነትን ያበላሻሉ፣ ከዚያም አልፎ፣ አንዳንድ ጊዜ፣ በሞትና በሕይወት መካከል የሚወስን ገጠመኝ ውስጥ ራሳቸውን ይጨምራሉ፡፡

የጊዜ አጠቃቀማችን ሁኔታ ተጽእኖው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ጊዜ አንድና አንድ በመሆኑ ነው - ጊዜ አንዴ ካለፈ በፍጹም ተመልሶ አይመጣም፡፡ ጊዜ በብዙ እድሎች የተሞላ ሃብት ነው፡፡ ጊዜ እንዲሁ ሲያልፍና ሲባክን ከዚያው ጋር አስገራሚ እድሎችና ሌሎች ውብ ነገሮች አብረው ያልፋሉ፡፡


https://t.me/info_tech1
72 views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 07:25:37 የተዘጉ ስልኮች መክፈት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው?
Network ሰጪ ድርጅቶች በመላው አለም ላይ ይገኛሉ። በሀገራችንም ethio telecom ይገኛል። በሌሎች ሀገራት ደግሞ ከ አንድ በላይ network አቅራቢ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት በመንግስት ስር ሳይሆን በግል ተቋማት ስር ስለሆኑ ነው።ለዚህም ጎሮቤታችን Kenya ጥሩ ማሳያ ናት። ከአንድ በላይ የመኖሩ ጥቅም ህዝቡ የተሻለ አማራጭ ያገኛል ድርጅቶቹም የተሻለ ነገር ለማቅረብ ፉክክር ዉስጥ ይገባሉ። አንድ አንድ network ሰጪ ድርጅቶች ደግሞ አለም አቀፍ እውቅና አላቸው።
ለምሳሌ T-mobile, verizon, orange, vodafone.....
እነዚህ ድርጅቶች ከሚፎካክሩቸው መንገዶች አንዱ ደንበኞችን ለመሳብ ሲሉ የስልክ ቀፎዎችን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ። ይህን የሚያደርጉት ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዛቸዉ ቁጥር ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ነው። ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ የስልክ ቀፎዎች ከተገዙበት የnetwork ሰጪ ተቋማት ውጪ ያሉ sim cardoችን አይቀበሉም ይህም ምክንያቱ በ security code ስለሚቆለፉ ነው። እንደዚህ አይነት ስልኮች ሀገር ስለቀየሩ ሳይሆን እንቢ የሚሉት ከተገዙበት የ network ሰጪ ድርጅት ዉጪ ባሉ network ሰጪ ድርጅቶች sim card ስለማይሰሩ ነው።
የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ።
Sim not valid, wrong sim,unknown sim, phone restricted, contact service provider.....
ከ network ሰጪ ድርጅቶች የተገዛ ስልክ ለመክፈት ሁለት መንገድ አለ።
1. Computer , flasher box, እና flasher file በመጠቀም መክፈት ይቻላል።
ይህ ዘዴ አሁን ላይ ethio telecome የሚዘጋቸውን ስልኮችንም ይመለከታል ነገር ግን በዚህ Method ለመክፈት Computer, flasher box እና flasher file ያስፈልገናል።
ስለ Computer ማብራራት አያስፈገኝም ነገር ግን በዚህ Method ትንሽ አሸጋሪ የሚሆነው Universal flasher box ማግኘት ነው ይሄ box የተለያዩ ጥቅሞች ሲኖሩት ከዚህም ውስጥ በስልኩ ሞዴል የራሱን flasher file ከ Google ላይ በማወረድ ከስልኮቻችን ጋር በማገናኘት የትኛውንም ስልክ ማስተካከል እንችላለን ከ hardware ውጪ ምንም አይነት ችግሮችን እንድናስተካክል ያስችለናል።
ይህ universal flasher Box orginale ስልኮችን IMEI create በማድረግ አሁን ላይ ላለው ethio telecome ለሚዘጋቸው ስልኮች ፍቱን መድሃኒት ሲሆን የ flasher box ዋጋ በ Ethiopia 4326birr አከባቢ ሲሆን የተወሰኑ ሞባይል ቤቶች በ addis abeba እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
ለምሳሌ ለመጠቆም ያህል መርካቶ ይርጋ ሃይሌ building ላይ በኛ በኩልም ይህን flasher box ማግኘት ይችላሉ።
2. ለ ድርጅቱ መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም ማስከፈት ሲሆን:-
ለምሳሌ iphone በ icloud የተዘጉ ስልኮችን መጥቀስ ይቻላል እንደዚህ አይነት ስልኮች የ e-commerce እንዲሁም credit card ይጠይቃሉ። ይሄ አገልግሎት ደግሞ እኛ ሀገር ስለሌለ ያለው አማራጭ ውጭ ሀገር በምናቀው ሰው ማስከፈት ነው። ይህ ማለት ድህረ ገፁ ላይ ግብተን የስልኩን ሞዴል ስናስገባ ክፍያ ይጠይቀናል ክፍያውም የሚከናወነው በ ማስተር ካርድ ስለሆነ ክፍያውን ውጪ ሃገር ማስተር ካርድ ባለው ሰው ከባላንሱ ላይ እንዲፈፅምልን በማድረግ ክፍያው ከተፈጸመላቸው ድርጅቱ ኮዱን በሚያስገባው Email አድሬስ ስለሚልክልን ወድያውኑ መክፈት ይቻላል።
በ icloud የተዘጉ ስልኮች በማስተር ካርድ በ አሁን ጊዜ የሚያስከፈለው 104$ ዶላር ነው ለዚህም ነው በአዲስ አበባ በተለያዩ የ ሞባይል ቤቶች በተለይ መርካቶ ላይ ከ200$ ዶላር በላይ የሚጠይቁት ጥቅማቸውን በማሰብ ማለት ነው። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለባችሁ ውጪ ሃገር ላይ የ ማስተር ካርድ ቪዛ ኮዱን አስገብቶ ክፍያውን ሊፈፅምላችሁ እና በ Email የሚላክለትን Code ሊልክላችሁ የሚችል ወዳጅ ከሌላችሁ ምንም አይነት አማራጭ የላችሁም ከ200$ ዶላር በላይ ከፍለን ከማስከፈት ውጪ ስልኩን መጠቀም አንችልም።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ይሄ መንገድ ስላካችንን በመጀመሪያ ሩት ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለ ሩት ከዚህ በፊት Post ላይ ማብራሪያ ስለሰጠን ከዛ ላይ ገብተው ያንብቡ። ሩት የሆነ ቀፎ ካለን እንደሚከተለው በማድረግ imei መቀየር እንችላለን ።
ይህን ዘዴ ለመጠቀም ሁለት ፕሮግራሞች እንጠቀማለን የመጀመሪያው:-
1.Mobileuncle MTK IMEI Write Tool የሚለውን ሶፍትዌር ኮምፒውተራችን ላይ ዳውንሎድ እናደርጋለን ከዛ በዚፕ ያለውን ፕሮግራም ስንከፍት የሚያመጣልን ዊንዶው ላይ Y ብልን ፅፈን enter እንጫናለን ከዛ የሞባይላችንን imei እንፅፍና
create IMEI .BAK ብለን አዲስ የተፈጠረውን imei.bak ፋይል ወደ ሜሞሪ ካርድ እንልከዋለን።
ሜሞሪ ካርዱን ቀፎ ውስጥ ካስገባን በኋላ...
2.ይህን አፕሊኬሽን ቀፏችን ላይ እንጭናለን mobileuncle_MTK_toolv2.9.9.apk
3.ከዛ የጫነውን አፕሊኬሽን ስንከፍት ሩት ኣክሰስ ጥያቄ ሲጠይቅ grant ብለን ፍቃድ እንሰጠዋለን።
ከዛ IMEI backup and restore የሚለውን ከፍተን ,restore IMEI.bak. ስንል ቅድም ሜሞሪ ላይ ያስቀመጥነውን ፋይል ወደ ቀፏችን ይፅፍልናል።
ሲጨርስ ቀፏችንን Restart አድርገን መደወያው ላይ *#06# አስገብተን በትክክል መፃፉን እናረጋግጣለን።
ነገር ግን ሚሞሪ የማይወስዱ ስልኮች እና የተወሰኑ ሞባይሎች ለምሳሌ iphone...etc በmobile Uncle tools ImEI backup restore የሚለው not supported ካላችሁ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርንው በ method one የሚከፈቱ ስለሆኑ የግድ Flasher box መግዛት ይጠበቅባችኋል።

▬▬▬▬▬ Share ▬▬▬▬
95 views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 07:19:23
84 views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 16:52:13
የማንሰማው የለ ዘንድሮ

ሰይጣንን ኣሸንፌ ቀበቶ ተሸለምኩ ያለው ናይጄርያዊ ሰባኪ

ናይጄሪያዊው ነብይ ኦዱሜጄ በአለም አቀፍ የመንፈሳዊ ጦርነት ሻምፒዮና ሰይጣንን ማሸነፉን ገልፆ የተሸለመውን ቀበቶ ለህዝቡ አሳይቷል። ነብዩ እንዳለው ብቻውን ወደ ገሃነም ሄዶ ሰይጣንን በር ዘግቶ ተፋልሞ በድል እንደተመለሰ ገልፇል።

ዳኛው ማን ነበር የሚለውን ማንም ሊጠይቀኝ አይገባም ማለቱን የናይጄሪያ ዜና አውታሮች ዘግበውታል። በቀላል ይሁን ከባድ ሚዛን የሚለው ጉዳይ መልስ አላገኘም።

sheger press


ማስተዋሉን ይስጠን
96 views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 14:12:18 Urgent vacancy announcement

Position #pharmacist

Work experience #three year and above

Salary Negosable

Place of work #A.A

Call #0911193231



https://t.me/job_vacancy5
https://t.me/job_vacancy5
85 views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 10:14:09
Be fast share for your friends and apply this vacancy #Today and #tomorrow left


https://t.me/job_vacancy5
https://t.me/job_vacancy5
85 views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ